www.maledatimes.com “የቀድሞው ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊን አልተካም “ሃይለማርያም ደሳለኝ (ማለዳ ታይምስ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“የቀድሞው ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊን አልተካም “ሃይለማርያም ደሳለኝ (ማለዳ ታይምስ)

By   /   September 16, 2012  /   Comments Off on “የቀድሞው ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊን አልተካም “ሃይለማርያም ደሳለኝ (ማለዳ ታይምስ)

    Print       Email
0 0
Read Time:15 Minute, 51 Second

በሃገሪቱ ላይ የተተኪ  ስልጣን ተዋረድ በዛሬው እለት በምርጫ ሲጠናቀቅ እስከዛሬ ድረስ ግን በስልጣን ውክልና የሌለው አካል ሲገዛ : በሞተ ሰው ስም ሃገሪቱ ግዞት እንዳደረገች ተደርጎ በመላው ሃገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር እየተባለ ሲጠሩ እና ምክትል የነበሩትን ም/ጠቅላይ ሚንስትሩን ቦታም ሳይሰጣቸው መክረሙ ይታወሳል ለዚህም ምርጫ ዋነኛው እና ትልቁ ነገር ከውሳኔ ለመድረስ የሚያስችላቸውን ትልቅ አጀንዳ ከግቡ ለማድረስ አለመቻላቸው እና የወያኔ ኢሃአዴግ ቅድመ ዝግጅት ሊያደርግ የሚችል አካል አለመሆኑን እና ዝግጅትም አድርጎ እንደማያውቅ የሚያሳይ ጉልህ መንገድ ነው ።በሌላም በኩል የህገ መንግስቱ በግልጽ አለመቀመጥ ከመጨረሻው ውሳኔ ለመድረስ አለመቻል ያስቻለ ዋነኛው መሰናክል ነው ።በሌላም በኩል እስካሁን ድረስ ያልበረደው በውስጣቸው የተፈጠረው አለመግባባት እና ሽኩቻቸውን ግልጽ ላለማውጣት ማን ይመረጣል የሚለው ዋነኛ ሃሳብ የሁሉም ሰው የጭንቅ ቀን ሆኖባቸው መክረሙ ደግሞ የፈጠረው ክፍተት ነው ። በአሁኑ ሰአት ግልጽነት የጎደለው የሽግግር መንግስት እና የመተካካት ምርጫ ዛሬም ድረስ አስገራሚ ሆኖአል ።በአሁኑ ሰአት ሃይለማርያም ደሳለኝ መመረጣቸውን አስመልክቶ የተለያዩ ግለሰቦች ውስጣዊ ደስታቸውን ቢገልጹም እውነት የወያኔ አስተዳደራዊ ቁንጮ በመሆን እሳቸውን ወደ ሚመራበት መንበር ሊጓዝ እንደሚችል ማን ያውቃል ።ቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትሩ ይመሩት የነበሩትን የስልጣን  ቦታዎች እሳቸው ተረክበው ይመራሉ የሚለው እሳቤ ግን እዚህ ላይ እንደሚያከትም የታወቀ ነው ።ከመከላከያ ሚንስትሩ ጀምሮ የውስጥ ደህንነት ጉዳይ እና ሌሎችም የሚንስትር መስሪያ ቤቶችን ማስተዳደር ብሎም  ሆነ መምራት እንዳይችሉ ለማንኮላሸት ተብሎ የታቀደው እቅድ መላ ምቱን ዛሬ የሚመታው ሁሉንም በህወሃት እጅ ስር እንዲወድቅ  የማድረግ ዝግጅት ማድረጋቸው እና ውስጥ ለውስጥ የተደረገው  ሴራ መሆኑን መረዳት አለብን ።   

በእርግጥም የአሁኑ አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር  ባለፈው በሰጡት መግለጫ “የቀድሞው ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊን አልተካም “ብለው ግልጹን ነግረውናል አዎ እሳቸውን በአካልም ሆነ በመንፈስም አይተኩም  መለስ ዜናዊ ማለት ከምንም በላይ የተፈጥሮ ጸጋ ካደለቻቸው ብልሃት ጋር ስናያቸው ወርቃማ ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ለተንኮል እና ተንኮል ለማሴር እንደሆነ እስከ 1997 አ.ም ድረስ ከተከናወኑት ክስተቶች መረዳት ይቻላል ። ብዙ ጥፋቶቻቸው ግን በቻይና መንገድ ስራ ታጥፎ ለቀብራቸው ለቅሶ ዋለላቸው ። ሆኖም ግን አንድ እና አንድ ደግሞ አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር በተሻለ ሁኔታ  የቤተክርስቲያን ሰው ወይንም እግዚአብሄርን አገልጋይ የሆኑ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ከመሆናቸውም በላይ ለእምነታቸው እና ለአምላክ የተገዙ ናቸው ::ፊንላንድ  በአካል ሄደው ትምህርታቸውን አጠናቀው መመለሳቸውን ሰምተናል በሌላ በኩል ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትር በርቀት ትምህርት ተከታትለው መያዛቸውን እና በተለዪም ከሆላንድ የያዙትን ማስተርሳቸው ነዋይ ገ/አብ ይረዷቸው የነበረ ሲሆን አለም ሰገድ ፣አረጋሽ ፣ተወልደ፣ገብሩ አስራት  የተመረቁት ሲሆኑ  በሆላንድ ኢምባሲ በተዘጋጀው ከፍተኛ የምረቃ ዝግጅት  አቶ መለስ እንዳይገኙ የተደረገው ተሃድሶ በሚል እሳቤ እቤታቸው ተወጣጥረው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት እንዴት ነበር የሚለውን ሂደት ሲያጠኑ መክረማቸው የሚታወቅ ነው  ፣ አንድ ነገር ልንረሳ የማይገባን ነገር ግን የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትሩ ጊዜ ሲያገኙ የሚያገላብጧቸው መጽሃፍቶች የትየለሌ ናቸው ።እንዲሆኖ ሳለ የዛሬው ጠ/ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ  ከአርባምንጭ ዩንቨርሲቲ ብዙ ምሁራኖችን ማፍራታቸውን እራሱ የረሱት ይመስላል ዛሬም ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን አለተካም  አልችልም ብለው ሲሉ ተደምጠዋል በእርሳቸው ያለው መተማመንም  ባዶ እንደሆነ ያሳያል።  ይህንን ሁሉ ሃተታ ላነሳ የቻልኩበት ምክንያት ህወሃት ለእርሳቸው ሊሰጣቸው የሚችለው ቦታ ውስን መሆኑንም ሊገልጹ ፈልገው ይሆን ወይስ እንዴት ነው የሚለውንም ውስጣዊ ህብረ ቃል ቦታውን ስለማይሰጡኝ የምሰራው ስራ የለኝም ከእኔ ምንም አትጠብቁ ማለታቸውንም ልብ እንበል።እንዲህ ከሆነ ዘንዳ ሃገሪቱን ማን ይሆን ከላይ ሆኖ የሚመራት ? ከተመረጡት ሁለቱ አመራር አካላት ውጭ የመገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ ሶስተኛውን ተመራጭ ሊገልጹ አልፈለጉም አልገለጹምም ለምን ይሆን ሚስጥራቸው ምንድን ነው ? ለምንስ በሚስጥር ሊያዝ ቻለ?እስካሁን የተሰጠው መላምት የህወሃት የበላይነት እንዳይታወቅ እና ማን እንደተመረጠ ላለመናገር የተወሰነበት ውሳኔ ምን ይሆን ተብሎ ህዝቡ ጉጉት እንዲኖረው የተደረገ ዘዴ ነው ወይስ የህወሃት ሚስጥራዊ ህይወት ።

በሃገሪቱ  የሕገ መንግሥቱ ከወጣ በኋላ ሌሎች ተከታታይ ወይም ተጓዳኝ የሆኑ መመርያዎችን፣ ደንቦችንና ማስፈጸሚያ ሕጐችን በማውጣት ያንን ነገር የበለጠ ማዳበርና ውጤታማ ማድረግ የሚቻልበት ዕድል አልተከናወነም ያልተከናወነበትም ዋነኛውም ጉዳይ የህወሃት ውስጣዊ ጥቅም የመሟላት እና አለመሟላት ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሥልጣን በሚመለከት አንቀጽ 75 እና 76 ላይ የተጠቀሰ ነገር አለ፡፡ አንቀጽ 76 የጠቅላይ ሚኒስትሩን የሥራ ዝርዝር ኃላፊነትና ድርሻውን ይጠቅሳል፡፡ አንቀጽ 75 ደግሞ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሚናና ለማን ተጠሪ እንደሚሆን፣ ምን ሥራ እንደሚሠራ ነው የሚዘረዝረው፡፡   ክፍተቱ የሚታየው በአንቀጽ 75 ንዑስ አንቀጽ 2(ለ) ላይ ነው ይህንን አንቀጽ በግልጽ አለመስቀመጥ የተፈለገበት ዋነኛ ምክንያት ጠቅላይ ሚንስትሩ ለራሳቸው ስልጣን በሚያመቻቸው መልኩ አገሪቷን እንደፈለጋቸው ለመምራት እንዲያስችላቸው ያደረጉት ትልቁ ስልታቸው ነበር ፡፡ይህ ከሆነ ዘንድ ይህ ህገመንግስት ከአሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር በኩል ለሚመሩትስ የስልጣን ዟር ጋር አብሮ ሌሄድ ይችል ይሆናል ወይስ ህገ መንግስቱ አዋጁን ይቀይራል? ይህም ሆኖ  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተክቶ እንደሚሠራ ይናገራል፡፡      

              ይህ አንቀጽ በውስጡ የጐደለው ነገር የመተካትንና የአተካክ ሒደትን ነው እንጂ የመተካትን ሚና አይደለም፡፡ ተክቶ የመሥራትን ሚና አላጐደለም፡፡ ነገር ግን በዝርዝር መቼ? እንዴት ምን ምን ዓይነት ችግሮች ሲከሰቱ የሥልጣን ሚናው እስከምን ድረስ እንደሚሆን በሚገልጽ መልኩ አልተቀመጠም፡፡ አንዳንድ መንግሥታት እንደዚህ ዓይነት ቀውስ ሲያጋጥማቸው እንዴት አድርገው መተካት እንዳለባቸው ያስቀምጣሉ፡፡ ለምሳሌ ጦርነት ቢቀሰቀስ፣ ያልተጠበቀ አደጋ ቢከሰት እንዴት አድርገው መተካካት እንደሚችሉ ዝርዝር ነገሮች ይኖራቸዋል፡፡ ከተሞክሮ ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ ከዚህ በፊት የደረሰባቸውን ምክንያት አድርገው ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙ አገሮች መተካካትን በሚመለከት ግልጽ የሆነ ሕግ አላቸው፡፡ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጤንነት እክል ምክንያት መሥራት የማይችሉበት ሁኔታ ቢፈጠር ተክቶ ይሠራል የተባለው ሰው እስከምን ቀን ድረስ ሊሠራ ይችላል? ምን ምን መሠረታዊ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሥራዎች ነው መፈጸምና ማስፈጸም የሚችለው? የሚሉትን ጥያቄዎች አይመልስም፡፡ እነዚህ ባለመቀመጣቸው ሕገ መንግሥቱ ላይ ክፍተት አሳይቷል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ባለው ህገ መንግስት መተዳደራችንን ምን ይሉት ይሆን ? የህገ መንግስቱ ክፍተት ይሞላ ይሆን ወይስ በጎደለ ሙላ ጨዋታው አሁንም እንደጎደለ ይቀራል?ወደፊት የምናየው ይሆናል። ብዙ አወዛጋቢ ነገሮች ያሉት ሲሆን ከሚንስትሩ እስከ ተተባባቂው ሚንስትር ያለውም ሂደት የሃገሪቱን እጣ ፈንታ ወደ አዘቅት ውስጥ የሚከት መሆኑን ብንረዳው ፣ከወደፊቱ ውድቀት ሊያድናት የሚችል የፖለቲለካ ስትራቴጂ በተነደፈላት ጥሩ በነበር ።  

“ሃይለማርያም ደሳለኝ ና አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ሊቀመንበር

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 16, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 16, 2012 @ 8:20 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar