www.maledatimes.com በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዝርፊያ እየተከናወነ ይገኛል። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዝርፊያ እየተከናወነ ይገኛል።

By   /   September 21, 2012  /   Comments Off on በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዝርፊያ እየተከናወነ ይገኛል።

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 31 Second

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዝርፊያ እየተከናወነ ይገኛል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረሩ ብዙ ተጓዦች ካስጫኗቸው ሻንጣዎቻቸው ውስጥ ጠቃሚ (ውድ) ቁሳቁሶችን መሰረቃቸውን እየተነገረ ነው ።በተለይም ተጓዥች ከአውሮጳ እና አሜሪካ የሚያደርጉ ከሆነ ከፍተኛ የብርበራ እና ምዝበራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ በአዲስ አበባ በዛሬ እለት የደረሱ አንባቢያኖቻችን ጠቁመዋል። በተለይም ከሮም ጣሊያን (ሊዮናርዶ ዳቪንቺ አለም አቀፍ አየአር ጣቢያ) ተነስቶ ዛሬ ንጋት ላይ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር መንገድ የደረሰው የበረራ ቁጥር ETH-703 ላይ በተስፈሩ የውጭ እና የአገሩ ዜጎች ላይ የደረሰው ዝርፊያ በድርጅቱ አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ወቀሳን አሥሰንዝሮአል ። በተመሳሳይ በረራ በትላንትናው እለት ከሰሜን አሜሪካ ያደረገው አውሮፕላን ላይ ይህ ድርጊት መፈጸሙ ጠንካራ እና ሆን ተብሎ የታቀደ ነው ሲሉ ይገልጻሉ ።ለዚህም ተጠያቂዎቹ በስሩ የሚገኙት የወያኔ ደህንነቶች በስልጣናቸው አይተው የህዝቡን ገንዘብ መበዝበር ከጀመሩ የሰነበቱ ቢሆንም በዚህ ወቅት ግን እየተከናወነ ያለው ዝርፊያ በትክክለኛ አላማ ተደርጎ የተሰራ ዘረፋ ነው ሲሉ ተጓዦች ምሬታቸውን ገልጸዋል። ከአየር መንገዱ እቃ የተወሰደባቸ ሰዎች ምንምን እንደተወሰደባቸው ሲያመለክቱ ክአመራር አባላቱ ምንም ምላሽ ሊሰጣቸው ባለመቻላቸው  ለዚህ ምዝበራ ተጠያቂ የምናደርገው ማንን ነው ?ይህ ጥርስ የሌለው አንበሳ መሆን ነው ።በበረራው ሰአት ከተዘረፉት መካከል አይፎን ፣አፕል ኮምፒዩተ ር፣ ቶሺባ ላፕቶፕ፣ ኤች ቲ ሲ እና የተለያዩ አገር ብዛት ያላቸው የብር ኖቶች  መሆናቸውን ተሳፋሪዎቹ ጠቁመዋል። ይህ ደግሞ የድርጅቱን ህልውና አደጋ ላይ ሊጥለው ይችላል ሲሉ አስተያየታቸውን ተሳፋሪዎቹ ሰጥተዋል። በተለይም ቱሪስቶችን ጭምር ልርዝርፊያ የሚያደርገው ይህ ዝርፊያ ለወደፊቱ የሃገሪቱን ገጽታ ከማበላሸቱም በላይ ዳግመኛ የሚከለክል አስነዋሪ ድርጊት ነው ሲሉ አክለዋል።

በአየር መንገዱ የስልክ ጥሪ አድርገን ስለ ጉዳዩ  ለማጣራት ያደረግነው ጥረት በጆሮአችን ላይ ስልክ በመዝጋት ለማነጋገር ባለመቻላቸው አለመሳካቱን የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ይገልጻል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 21, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 21, 2012 @ 6:10 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar