www.maledatimes.com ምነዋኢትዬጵያ….? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  POEMS  >  Current Article

ምነዋኢትዬጵያ….?

By   /   October 4, 2012  /   Comments Off on ምነዋኢትዬጵያ….?

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 18 Second

 

እንደ ይሁዳ ከዱ፣ ልጆችሽ ሸፈጡ

እንደ ኤሳው ሆኑ፣ ቡክርናቸውን ሸጡ

በመታመን ፋንታ፣ ኑፋቄን መረጡ።

እንደ ባህር አሸዋእንደ ሰማይ ከዋከብት

ምነዋ ኢትዬጵያበዛብሽ ጠላት?… 

አፈርሽ ‘’ሰለሰ’’፣ ሜዳሽ ‘’አሜክላ’’ እሾክ አበቀለ

ተራራ ሸለቆሽ ‘’ጃርት’’ ተራባበትተራብቶም ፏለለ፤

ባላና ማገርሽ፣ ምሰሶሽ ተማሰ

ዞብ አምባሽ ተናደ፣ ወንዝሽ ደፈረሰ

ደም እንደ ጎርፍ ውሀ፣ በገላሽ ፈሰሰ

ውጭ ውስጥሽ ነቀዘ፣ ቤት አጉራሽ ፈረሰ

ምነዋ ኢትዬጵያምፅአት ለአንች ደገስ?                                     

የሚታመን ጠፋ፣ ለሰው ልጅ ያደረ

ውሸት ገኖ ናኘ፣ በቀየሽ ከበረ

ዘብጥያ ወረደ፣ እውነትም ታሰረ

ታሪክ ተረትተረት፣ ብስራት ተበሰረ፤

የውርጃ ‘’አደፍ’’ ቅሪት፣ ጭንጋፍ አሳድገሽ

‘’ቃልቻ ዘርጎጥን’’፣ ደም ተጠማልሽ

ጉድ ውልዶ ‘’አነበረ’’፣ ግዜ ማህፀንሽ

        ምነዋ እናት ምድር… ያልታየ ታየብሽ?

 እንደ ይሁዳ ከዱ፣ ልጆችሽ ሸፈጡ

እንደ ኤሳው ሆኑ፣ ቡክርናቸውን ሸጡ

በመታመን ፋንታ፣ ኑፋቄን መረጡ።

እንደ ባህር አሸዋእንደ ሰማይ ከዋከብት

ምነዋ ኢትዬጵያበዛብሽ ጠላት?… 

በቆብ ደፊ ‘’ሻሻም፣ ቀሳሽ መሳይ፣ ኮከብ ቆጣሪ ‘’

በቀን ሰባኪ፣ ማታ ጎፈሬ አበጣሪ

በደብተራ፣ ረጅም ተላባሽ፣ ካባ ተሞሻሪ

በዘንግ ተውረግራጊ ፣ ወገብ አሳሪ፤

ማህደረ ቅርስ ‘’ፅባወተመምበርሽ’’ ታምሶ

በዛር ፈረስ ደመ ነውጠኛ፣ መቅደስሽ ‘ረክሶ፤

የአምላክ ጻድቅሰማአታትሽ ማደሪያ

ተቸበቸበቸበ ወ’ቶ ባደባባይ ደርቶ በገብያ

ታበዩ በእግዚአብሔር….  ምነዋ ኢትዮጵያ…? 

አንድ ቀን ለተለበሰ ‘’ጥቁር ካባ’’፣ ለተደፋ ‘’ጥቁር ቆብ’’

በሚሉ ከ’ኔ ወዲያ የለም ልሂቅ፣ አዋቂ፣ ለሀገር የሚያስብ

በሚመስላቸው እነሱ ብቻ የሆኑ ህዝብ፤

እየተራበ ያጠገባቸውንእየታረዘ ያለበሳቸውን

ሳይማር ያስትማራቸውንሳይከፍሉት የከፍላቸውን

እየናቁት ያከበራቸውንእየሞተ ያኖራቸውን

በረሱት ፣ በከዱት፣ የገዛ ማንነት ወገናቸውን፤

በ’ነ ከረባት ….. ማ’ረጋቸው

በ’ነ ሆድ ….. አምላካቸው፤

በነሰለጠን ባይ፣ ደንቁረው አደንቋሪ ውስጠ ‘’አንኮላዎች’’

ያልሆኑትን ለመሆን፣ በመስሎ ፣ ህሊና ቢስ ሸፍጠኞች

በጥራዝ ነጠቅ ‘’ርዕዬት አለም’’ ሰባኪዎች

ያዩትን ያላዩትን ናፋቂ፣ በብልጭልጭ ኰተት ጎታች ተሸካሚዎች

የሀገር ርዕይ በሌላቸው፣ በቅዥታም፣ ተቀጥላ ጅራቶች፤

ተገዘገዝሽ!… ተቦረቦርሽ!… ተከፋፈልሽ!…

እንደ ቅርጫ ስጋ ገነጣጠሉሽቸበቸቡሽ!

ምነዋ ኢትዮጵያ …………………..?

ምነዋ ኢትዮጵያ ……………………?

ባጠባሽ ተነከስሽ፣ ባጎረስሽ – ተበላሽ

አመድ አፋሽ ሆነ፣ የዚህ ዘመን እጅሽ።

እንደ ይሁዳ ከዱ፣ ልጆችሽ ሸፈጡ

እንደ ኤሳው ሆኑ፣ ቡክርናቸውን ሸጡ

በመታመን ፋንታ፣ ኑፋቄን መረጡ።

እንደ ባህር አሸዋእንደ ሰማይ ከዋከብት

ምነዋ ኢትዬጵያበዛብሽ ጠላት?… 

ወግ ነው ሲዳሩ እንዲሉ፣ ‘’ተማሪ’’ ነኝ በሚሉ

ይይዙትን አ’ተው፣ ይጨብጡትን በዋለሉ

በመማሪያ የብእር ደም ብልቃጥ፣ ውሀ በሞሉ፤

በኮሌጅዩኒቨርስቲው፣ በየትምህርት ቤት

የሚማሩት፣ የሚያገኙት የእውቀታቸው አይነት

የአድማሳቸው ልእልና፣ የ’ርካታቸው ጥማት

የወጣትነት ህይወታቸው፣ የጥበባቸው እድገት፤

አባትን ሳያውቁ፣ አያትን መጠየቅ

ሱሪ በአንገት ማጥለቅ፣ በጎጥ እድር መድረቅ፤

ዲስኮ …ጫት …ሀሽሽ ‘’ፓሪ’’ መንጎድ

ምነዋ እናት ሀገር …. ምነው ጠፋ ትውልድ።

 እንደ ይሁዳ፣ ከዱ ልጆችሽ ሸፈጡ

እንደ ኤሳው ሆኑ፣ ቡክርናቸውን ሸጡ

በመታመን ፋንታ፣ ኑፋቄን መረጡ።

እንደ ባህር አሸዋእንደ ሰማይ ከዋከብት

ምነዋ ኢትዬጵያበዛብሽ ጠላት?… 

ርሀብእርዛት፣ ሰቆቃና ስደት

ስም መጠሪያሽ ሲሆን፣ አንች ባለሽበት፤

እርስ በርስ መባላት፣ ትውልድን ሲጨርስ

የፍትህ ያለህ ባይ፣  ዓለምን ሲያዳርስ፤

ወገኑንወገኑ፣ ገሎ ሲፎክር

ሀውልት ሲገነባ ፣በአንች ምድር አፈር

ምፃ’ተኛ ‘ሲኮን’፣ በገዛ ሀገር፤

ጥቂቶች ሲስቁ ፣ ብዙሀን ሲያለቅስ

ኃጢአት ተትረፍርፎ፣ ፅዋው ሞልቶ ሲፍስ

ዘመን አልፎ ዘመን፣ ዛሬም ደም ስናፈስ

ምነዋ ኢትዩጵያ…………………?

ምነዋ እናት ምድር… ዝም አለ የአ’ች ነፍስ?

ፍርድ ስጭ ዝም አትበይ፣ ተይ አትታበይ

ዋጋ ይከፈለው፣ በዳይ ተባዳይ

ይቅርም አባብይን፣ ወደፊት እ’ድናይ።…

የነፃ ህዝብ መልኩ ሰንደቅ አላማቸው

ባላደራ እናት ነሽ ቅርስ ያ’ርነታቸው።

አለሁ ካልሽ አለው፣ በይ መስክሪ በራስሽ

ከአንገቱ ተቃንቶ፣ ማየት የሚሽ ይይሽ።… 

‘’ያላያ ኢትዩጵያ… የለሽም – እያለሽ

 የጀመረሽ ምፅአት፣ ፍፁም ይጨርስሽ

ፀሀይ ከጨረቃ፣ ይጨላልሙብሽ

ከዋከብት ይርገፋ፣ ሰማይ ይደፋብሽ

እሳት ገሞራ፣ ይንደድ በላይሽ፤

ከምድር ገፅ ላይ ጠፍቶ ‘ምስልነትሸ’

ሲኦል ውረጅና ከነ-ግሳግስሽ

ዓለም ታሪክ ይፃፍ፣ እፎይ ይበልልሽ።’’

                                   —–//——   

ከፊልጶስ

/በመጨረሻወቹ ስንኞች ምን ለማለት እንደፈለኩ ፣ ወድ ኢትዮጵያዊያን  እንደምትረዱልኝ እምነቴ ነው።/

ለአስተያየት በኢሜል፡ philiposmw@gmail.com

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

አንድዬ

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar