www.maledatimes.com በችካጎ የሚገኘው በወያኔ መንግስት የሚመርው የሰበካ ጉባኤ ዲያቆናትን ማባረር ጀመረ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በችካጎ የሚገኘው በወያኔ መንግስት የሚመርው የሰበካ ጉባኤ ዲያቆናትን ማባረር ጀመረ

By   /   November 20, 2016  /   Comments Off on በችካጎ የሚገኘው በወያኔ መንግስት የሚመርው የሰበካ ጉባኤ ዲያቆናትን ማባረር ጀመረ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 39 Second

በዛሬው እለተ ሰንበ በተከናወነ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ በቅዱስ ሲኖዶስ የሚመራው የሰበካ ጉባኤ ዲያቆናትን ማባረር ጀመረ ። በዛሬ እለት ሰበካ ጉባኤው ባደረገው የመዋያያ ፕሮግራም ላይ መንግስትን በሃሳባቸው የተቃወሙ ዲያቆናትን ማባረር መጀመራቸው እና ከመንግስት ወገን ሆነው መስራት እየሰሩ እንደሆነ እና የአባይ ግድብ በቅዱስ ሲኖዶሱ እና ግድቡን በሚመለከታቸው አካላት የሚገደብ መሆኑን ባሰፈሩት የማባረሪያ ቅጽ ደብዳቤ ላይ ገልጸዋል ። ከተባረሩት ዲያቆናት መካከል አንዱ ዲያቆን በረከት ገብሬ መሆኑን የደረሰን መረጃ ሲያመለክት ከማባረሪያ ማስረጃ ወረቀቱ ጋር አባሪ ለተባረረው ዲያቆን እንደ ተሰጠው ተገልጦአል።

ይሄው የደበረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ለዘመናት በአንድነት ሲመራ የነበረውን እና ህዝብን በአንድ ላይ አንድ ህዝብ አድርጎ ይዞ ከነበረው የመድሃኒአለም ቤተ ክርስቲያን በፖለቲካዊ ይዘት እና በግለሰባዊ ጥቅም ምክንያት የቤተክርስቲያኑን አላማ በማዛባት ህብረተሰቦችን አስተሳሰባቸውን በመለወጥ እንዲበታተኑ ማድረጋቸው የሚዘነጋ አይደለም ፣ስለዚህ ዛሬም ላይ ገሃድ የወጣን ተንኮላቸውን በግላጭ ማሳየት ጀምረዋል ።  እንደ አንድ የህዝብ ልጅ በሲኖዶሱ መግለጫ ከጥቅምት 12 እና 13 በተደረገው ስብሰባ ላይ መንግስት ላይ ያደረገውን ጫና አስመልክቶ ፣መግለጽ ስላለባቸው ስላደረጉ ፣እና በመስከረም 21 በተደረገው ትምህርት እና በእሬቻ በአል ላይ የተደረጉትን ትምህርት እና ሰዎች በሰበአዊነታቸው መከባበር እና ሰላማዊ መሆን አለባቸው ፣መንግስት በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚያደርገውን አፈና ማቆም እንዳለበት ቢታመንም በሰላም እና በእግዚአብሄር መንግስት ቀናኢነትን መታሰብ ሲገባው መንግስትን ወግኖ ፖለቲካዊ አካሂያድ ሃሳብን በማስቀየስ ህብረተሰብን መወንጀል ተገቢ ባይሆንም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጥርስ መናከስ እንደተጀመረ ገልጦአል ።

በተለይም በእሬቻ በአል ላይ በተገደሉት ወገኖች ህዝባችን በሃዘን ቆዝሞ ሳለ እነርሱ ግን በአሸንዳ በአል አሸሸ ገዳሜ እያሉ በከበሩ ሲዘሉ የነበሩት ወገኖች ዛሬ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ገብተው ህዝባችንን ሰላሙን እና ክርስትናውን ማጥፋት የቅድስና ትምህሩን ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጋር ማስኬድ ጀምረዋል ሲል ዲያቆን በረከት ለማለዳ ታይምስ እና ለዘ ሃበሻ አዘጋጆች ገልጦአል ።

በቤተክርስቲያናት ውስጥም ሆነ በማንኛውም ቦታ የሰው ልጅ ሰበአዊ መብቱ የሚከበረት እንጂ በአንድ ዘር እና ፖለቲካ ተጠፍሮ የህዝብ መብት የሚነፈግበት እንዳልሆነም ጠቅለል አድርጎ ይገልጣል ።

በዚህ መሰረት የዲያቆን በረከት ገብሬን ሃሳብ ለማለዳ ታይምስ እና ለዘ ሃበሻ መገናኛ ብዙሃን ያቀረበውን ሃሳብ እንዲህ ጠቅለል አድርገን ከማገጃ ቅጹ ጋር አባሪ አድርገን አቅርበናል።

የዛሬ የሰንበት ውሎ የቅዱስ ሲኖዶስ አቋምና_~_~
•~•ተግዳሮታችን ከእግድ ደብዳቤ ጋር•~•
እንደሚታወቀው፣ በመላው የአገራችን ክፍል መንግስት በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍና በደል ተከትሎ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በጥብቅ ሲያወግዙት ተመልክተናል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስም ከጥቅምት 13-16/2009ዓ.ም በነበረው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የ35ኛውን የመንበረ ፓትርያርክ ሰበካ መንፈሳዊ አጠቃላይ ጉባኤ የጋራ መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ አንዳንድ ማሻሻያዎችን በማድረግ የ2009 ዓ.ም. የበጀት ዓመት የሥራ መመሪያ እንዲኾን ባጸደቀበት 12 በሚሆኑ የአቋም መግለጫዎች ላይ መንግሥት እና ተቃዋሚዎች የሀገር ችግሮችን በጋራ ውይይት እንዲፈቱ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። ይኸውም፦ አገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ለአያሌ ዘመናት ተዋደውና ተከባብረው የኖሩባትና አሁንም የሚኖሩባት በአርኣያነት ልትጠቀስ የሚገባት ብቸኛ አገር መሆኗን በአቋሙ ያስገነዘበው ቅዱስ ሲኖዶስ በአሁኑ ጊዜ ግን፦
➡️የሰዎች ሕይወት እየጠፋ መኾኑን፣
➡️ የአገር ሀብትና ንብረት እየወደመ መታየቱን፣
➡️ ከኖሩበትና ተወልደው ካደጉበት ቀዬ የሕዝቦች ፍልሰት ተባብሶ መታየቱ፤
➡️በዚህም ሳቢያ በሰላማዊው ኅብረተሰብ ዘንድ ከፍተኛ ስጋት እየሰፈነ መምጣቱን አብራርቷል፡፡
በመኾኑም በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ከህዝብ ለሚጠየቀው የማንነት ጥያቄ መንግሥትም፣ ለሚያስተዳድራቸው ዜጎች እንደ ቤት ሓላፊና እንደ መሪ ጥያቄዎቹን በአግባቡ በመፈተሽና በማጥናት ለአገርና ለወገን የሚጠቅም ምላሽ እንዲሰጥባቸው፣ ለሕዝቡ የገባውንም ቃል በተግባር አውሎ በሥራ እንዲተረጉም ምልዓተ ጉባኤው በመግለጫው አሳስቧል፡፡
የሀገር ጉዳይ የጋራና የእኛው ለእኛው ጉዳይ በመሆኑ፣ የሀገሪቱ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ከመንግሥት ጋራ በሰላማዊ መንገድ ተቀራርበው በክብ ጠረጴዛ የጋራ ውይይት በማካሔድ ችግሮችን እንዲፈቱም ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
አያይዞም ቤተ ክርስቲያን ዕለት በዕለት ከምታከናውነው መንፈሳዊ ግልጋሎት ባልተናነሰ፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት፤ መላው ካህናትና አገልጋዮች፣ በዕለተ ሰንበት፣ በማታ ጉባኤ፣ በወርኃዊና በዓመታዊ በዓላት ሁሉ ሕዝበ ክርስቲያኑ ለአገሩ ሰላምና አንድነት ተባብሮ እንዲቆም በየጉባኤያቱ እንዲያስተምሩ መመሪያ አስተላልፏል።
እንግዲህ የእኛስ ተግዳሮት ምን ነበር? ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት ስላለው ወቅታዊ የአገራችን አሳሳቢ ጉዳይ፣ እደግመዋለው “የአገራችን አሳሳቢ ጉዳይ” መንግስትን በማውገዝና፣ ልዩነትና ጥላቻን በማስወገድ ወደ አንድነት በመምጣት ተቻችለንና ተዋደን መኖር እንዳለብን በተሰጠው የወንጌል አገልግሎት፣ ጉዳዩ የጋራችን ሆኖ ሳለ ጥቂት የመንግስት ደጋፊ የሆኑ ግለሰቦች ስላልተዋጠላቸውና ካሁን ካሁን ምን ያለበት ዝላይ አይችልም እንዲሉ በቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ ከፋፋይ፣ ጎጠኛ፣ እንዲሁም ፖለቲከኛ የሚል ታፔላ ለጥፎ አንድን ግለሰብ ብቻ ለማጥቃት ሆን ተብሎ የተሰራ ሴራ መስሎ እስኪታይ ድረስ የእግድ ደብዳቤ መጻፍ ምን የሚሉት ጨዋታ ነው። ጉዳዩ ስህተት አሊያም ወንጀል መስሎ ከታየ የመጀመሪያው ከፋፋይ ወንጀለኛ ቅዱስ ሲኖዶስ ሊሆን ነው ማለት ነው? መልሱን ለእናንተው ትቼዋለው።
“እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል” እንዲሉ፣ ለህሊና መኖር ማለት ለእውነት መቆም ነው፣ እውነትን ይዞ ሽንፈት ፈጽሞ የማይታሰብ ጉዳይ ነው፣ ውቅያኖስ ውስጥ ጠልቃ ብትገባም ውቅያኖሱ ሞልቶ ይፈሳል እንጂ እውነት እንደሆነ ምንጊዜም በልባችን አለች። ከእናንተም ቢሆን ይህ ያልተሰውረ የገሀድ ምስጢር ነው። አዎን መንግስት ህዝብን ጨቁኗል፣ ብሄርን ከብሄር አለያይቷል፣ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንንም በአስተዳደራዊ ጉዳዮቿ ላይ ጣልቃ እየገባ የፖለቲካ ማራመጃ ሰገነት አድርጏታል፣ ኢትዮጵያዊነት ስሜትና ባህልን ከትውልዱ ልብ ሰርፆ እንዳይገባ ማንነታችንን ሁሉ በምዕራባውያን ክፉ ልማድ ለውጦታል። ይሔ ነው እውነታው፣ ለነገሩ ምኑ ይገባችሁና ነው፣ ወገን ሲያልቅ፣ ህዝብ በአደባባይ ሲረሸን ግድ ያልሰጣችሁ እናንተን እንደ ሰው ቆጥሬ ለእናንተው ቦታ መስጠቴ እኔው እንጂ ሞኙ … ኤዲያ!።
በረከት ገብሬ
እሁድ ህዳር11-2009ዓ.ም%e1%89%a0%e1%88%a8%e1%8a%a8%e1%89%b52 %e1%89%a0%e1%88%a8%e1%8a%a8%e1%89%b53 %e1%89%a0%e1%88%a8%e1%8a%a8%e1%89%b54 %e1%89%a0%e1%88%a8%e1%8a%ad%e1%89%b51

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on November 20, 2016
  • By:
  • Last Modified: November 20, 2016 @ 7:58 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar