www.maledatimes.com *በዝንብ የተወረረች ከተማ* [በረከት ገብሬ] - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

*በዝንብ የተወረረች ከተማ* [በረከት ገብሬ]

By   /   November 20, 2016  /   Comments Off on *በዝንብ የተወረረች ከተማ* [በረከት ገብሬ]

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 17 Second

~_~_~_~•_~_~_~_~•_~_~_~_~
የዝንብ ብልሐቷ ምንድነው ብትሉኝ ሌላ የሰራውን መብላቷ፣ ሰነፎች ሰዎችም እንዲሁ ናቸው፣ ሌላው በደከመው፣ ሌላው በለፋበት፣ ላቡንና ደሙን ገብሮ ባፈራው ሀብት ላይ ጉብ ብሎ የሰራውን መብላት ይወዳሉና።
እርጎን አግባብነት በሌለው ስፍራ ከፍተው ቢተዉት ዝንብና ድመት ይጫወቱበታል፣ አገርም እውነተኛ መሪ ያጣች እንደሆነ የማንም መጫወቻ ሆና ወደ ምድረ-በዳነት ትለወጣለች። ከጸሐይ በታች የሚደከም ድካም ሁሉ ትርፉ ምንድነው? ዘመን ይሔዳል ዘመን ይተካል፣ ትውልድ ሲሻገር አዲስ ትውልድ ይመጣል፣ ገደብ የለሽ ስልጣን እንደሌለ ሁሉ አንዱ ሲሔድ ሌላው ይነግሳል። ለዚህም ማሳያው ዋናው ቁምነገሩ የእግዚአብሔር እጅ በተፈጥሮ ምን ያስተምረናል ነው? (ኢዮ.12፥7) ፀሐይ ትወጣለች ፀሐይ ትጠልቃለች፣ ነፋስ አንዴ ወደ ደቡብ አንዴ ወደ ሰሜን ይዞራል፣ ዘወትር (ጊዜም) በዙረቱ ይዞራል፣ ነፋስም በዙረቱ ይመላለሳል፣ ፈሳሾች አፍላጋት ወደፍሳሻቸው ወደ ባህር ይመላለሳሉ ባህሩ ግን አይሞላም። ተፈጥሮ እንዲህ ናት፣ ህሊናን በሚያደክም በማይመረመር ምስጢር (መክ.፩፥፰) አንዴ ወደ ቀኝ አንዴ ወደ ግራ፣ አንዴ ወደ ፊት አንዴ ወደ ኇላ ፣ እኛ ባላሰብነውና ባልጠበቅነው መልኩ ብዙ ነገሮችን ታሳየናለች።
እኛ ግን ከተፈጥሮ ብዙ ነገር መማር ስንችል በራሳችን ዛቢያ በመዞር፣ ከማስተዋል ዓለም እርቀን ብዙ መጏዝ አቅቶን ባለንበት እንዳለን አለን። ዛሬ አደጉ የምንላቸው እንደነ አሜሪካ፣ ቻይና ያሉ ታላላቅ አገራት ትላንት ምንም ያልነበሩ፣ በጥቂት ማህበረሰብ እንቅስቃሴ እንደ አገር ሳይሆን በዝቅተኛ ገቢ እንደምትተዳደር የቀበሌ አውራጃ እጅግ ደሃ የሚባሉ ህዝቦች የሚኖሩባቸው አገራት ነበሩ። እኛሳ—-? እኛማ የ3000ሺህ ዓመት የእድገት ስልጣኔ፣ የጀግንነት ታሪክ ያለን፣ ለጠላት ያልተንበረከክን፣ ለባዕዳን ያልተገዛን፣ ተከብረንና ተፈርተን የኖርን የጥቁሮች ኩራት ሰንደቅ፣ ታላቅ ህዝቦች ነበርን። ነገር ግን ምን ያደርጋል ሁሉ በነበር ቀረ እንጂ፣ እንኳንስ የመቶ ዓመት ታሪክ ቀርቶ የሁለት፣ የሦስት አስርት ዓመታት ታሪክ ባለቤት የሆን እስከማንመስል ድረስ “የታሪክ መጨረሻ – የመጨረሻ ትውልድ” ተብለን በዓለም መድረክ የዜና አውታር ማሰራጫ እርዕስ መሆናችን እጅግ ያሳዝናል።
ዓለም ወደ አንድ መንደር (globalization) እየመጣ ባለበት ጊዜ፣ ከጊዜ እኩል እየሮጠ፣ ባይልለትም ከተፈጥሮ በላይ በልጦ ለመጏዝ እየጣረ፣ ከምድር አልፎ ጠፈር ላይ ለመኖር እሩቅ እያሰበ አይምሮውን እያሰፋ ባለበት ሰአት፣ እኛ ግን ተመልሰን ከአዲስ አዲስ እህጉር የምንፈጥር ይመስል ዘር ቆጠራ፣ ብሔር፣ ቀለም፣ ጎሳ እየለየን በቋንቋ ተከፋፍለን እንደ ባቢሎናውያን ተለያይተን ቁጭ። በሰፊው ዓለም ላይ እራስን በነገድ፣ በመደብ አስቀምጦ መኖር ይሄ ነው ጠባብነት።
አንበሳ ሲያረጅ እንዲሉ….! አንበሶች ሆነን ተፈጥረን ምድራችንን ከጅቦች እንዳላስጣልን፣ ዛሬ የታላቅነት የእድሜ ጅረት ለእርጅና ዳረገን መሰል ዝንቦች ከየትም ተሰባስበው አገሬን ሊያረክሱ (የዝንብ ብልሐቷ ምንድነው ቢሉ ሌላ የሰራውን መብላቷ፣ ሰነፎች ሰዎችም ሌላ የሰራውን መብላት ይወዳሉና) እምዬ ኢትዮጵያን በፈረሰ ጭንቅላት ሊያፈርሷት ተነሱ።
እ-ህ! ጋናውያን አንድ አባባል አላቸው “ወንዙን ካቋረጥክ ብቻ ነው አዞ አፍንጫው ያበጠ፣ ጥርሱ የተሳለ መሆኑን የምታውቀው” ይላሉ፣ ምን ለማለት ፈልጌ ነው፦ ይህ ጉዳይ እንዲሁ በንቀት የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም የነገ መዘዙ ከባድ ነው፣ ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ በዚህ አጣብቂኝ ወራት ውስጥ ከሀብትም በላይ ሀብት፣ ከገንዘብም በላይ ገንዘብ የሆነችን፣ ተመን የማይወጣላትን አገር ለማፈራረስ፣ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲባል አገርንና ህዝብን ለማጥፋት፣ ወገንን ከወገን ለማባላት የሀሰት ወሬን ከሚነዙ ከዘመናችን ሃሳዊ ሰባኪያን እራሳችንንና ማህበረሰባችንን በምንችለው አቅም ሁሉ ጸሐፊ የለ ገጣሚ፣ ካህን የለ አካሚ፣ ብስለትና ማስተዋል በተሞላበት መልኩ ልንጠብቅ ያስፈልጋል። አሊያማ ከጠበበው ጋር አብሮ መጥበብ የምንናፍቃትን የነጻነት ምድር ሳናይ፣ በሩቅ እንደተሳለምናት በናባው ተራራ ስር እናሸልባለን ልክ እንደ ሙሴ።
ይቆየን
—፦፦፦፦፦፦፦፦፦—
በረከት ገብሬ
ህዳር 10-2009ዓ.ም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on November 20, 2016
  • By:
  • Last Modified: November 20, 2016 @ 5:33 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar