www.maledatimes.com የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሆስፒታል መግባት ማህበረሰቡን አስደንግጦአል ። በመንግስት ሃይሎች ክፉኛ ድብደባ እንደተፈጸመበት ይጠረጠራል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሆስፒታል መግባት ማህበረሰቡን አስደንግጦአል ። በመንግስት ሃይሎች ክፉኛ ድብደባ እንደተፈጸመበት ይጠረጠራል

By   /   December 27, 2016  /   Comments Off on የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሆስፒታል መግባት ማህበረሰቡን አስደንግጦአል ። በመንግስት ሃይሎች ክፉኛ ድብደባ እንደተፈጸመበት ይጠረጠራል

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 15 Second

(ዘ-ሐበሻ) በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የሚፈጸመው ግፍ ከ ዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ነው:: ዛሬ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ በሶሻል ሚድያ በለቀቀው መረጃው እንዳለው ተመስገን በጠና ታሞ ሆስፒታል ገብቷል::

ዛሬ ታህሳስ 18/09 ዓ.ም “ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እጅግ ታሟል” በሚል ታሪኩ በለቀቀው መረጃ ” በዝዋይ ባቱ ሆስፒታል የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለፁል ዛሬ ታህሳስ 18/09ዓ.ም ተመስገን ታሞ በአንፖላንስ ወደ ሆስፒታሉ እንደመጣ ነው፡፡ የእስር ቤቱ ወታደሮች ወደ ሆስፒታል ይዘውት ሲገቡ ቀደመው በአቅራቢያው የነበረውን ሰው ከቦታው ዙር እንዲሉ ስላደረጉ የተመስገንን የህምም ደረጅ ቀረብ ብሎ ማየት አልተቻለም፡፡ተመሰገን በእስትሬቸር እየገፉ ወደ ሆስፒታል ውስጥ አንደስገቡት ለማወቅ ችለናል፡፡አሁን ከቀኑ 8፡10 ሆናል እስካሁን ተመስገን በዝዋይ ባቱ ሆስፒታል ይገኛል::” ይላል::

ከዚያም አንዳንድ ማህበረሰቦች እንደገለጹት ከ3ሳምንት በላይ ተመስገኝ በቤተሰቦቹ ሳይጎበኝ በመቅረቱ እና ቤተሰቦቹም ሆኑ ወዳጆቹ እርሱንን ባለማግኘታቸው ከፍተኛ ጭንቅ ላይ እንደነበሩ የሚታወስ ነበር ፣ከዚያም አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የማረሚያ ቤት አስተዳዳሪ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የአማርኛ ክፍል በሰጡት  የድምጽ ቃለመጠይቅ ደሳለኝ በዝዋይ እስር ቤት እንደሚገኝ አስታውቀዋል ፣አስከትሎም ወንድሙ በዝዋይ እስር ቤት በመሄድ በእርቀት አግኝቶት እንዳየው እና እግሩን እየጎተተ በከፍተኛ የህመም ስቃይ ይጓዝ እንደነበር በሶሻል ኔትወር መገናኛ መድረክ ላይ ለማህበረስቡ አመልክቶአል ።

ይኅንንም ግንዛቤ በማስገባት የማህበረሰቡ አስተያየት የጋዜጠኛው የተሰናከለ ህይወት በመንግስት ሃይሎች ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰበት ያመላክታል ሲሉ ይገልጣሉ ፣ይህም ድብደባ ካለበት የጤና ጉድለት ጋር ተደማምሮ ዛሬ ሆስፒታል በድብቅ እንዲገባ ተደርጓል ሲሉ ቤተሰቦቹም ይለጻሉ ።

fiteh editor in chief temesgen dessalegn

fiteh editor in chief temesgen dessalegn

የተመስገን ወንድም ጨምሮም “የዛሬን ቀን በተመለከተ የዝዋይ እስር ቤት አስተዳዳሬዎችና የዛሬው የሽፍት መሪ ሻለቃ ንጉሴ እንዲሁም እስከ ዛሬ በተመሰገን ላይ ለደረሰው እና ለሚደርሰው ነገር ሁሉ መንግስት ሀላፊነቱን ይወስዳል፡፡” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on December 27, 2016
  • By:
  • Last Modified: December 27, 2016 @ 12:50 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar