www.maledatimes.com መሳቂያው ፓርላማ! | አቤ ቶኪቻው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

መሳቂያው ፓርላማ! | አቤ ቶኪቻው

By   /   October 20, 2012  /   Comments Off on መሳቂያው ፓርላማ! | አቤ ቶኪቻው

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 54 Second
ያው እንደሚታወቀው የፓርላማ አባላቱ የምክር ቤት ስብሰባ ለማድረግ ሲሄዱ ወረፋ አይጠብቁ እንጂ የሆነ ኮሜዲ ፊልም ለመታደም ሲኒማ ቤት እንደሚገቡ አድርገው እንደሚያስቡት የታወቀ ነው። ይሄ ካልታወቀ ትልቅ የመረጃ ክፍተት አለ ማለት ነው!

በተለይ በአቶ መለስ አስተዳደር ጊዜ አባላቱ በሙሉ ለሳቅ ለጨዋታ ተሰነዳድተው ነበር ምክር ቤት የሚመጡት። (ዛሬ ማን ያጫውተን ዛሬ ማን ያጫውተን….! አረ ማን ያስቀን አረ ማን ያስቀን!) ብለን እናስነካው እንዴ!?

የምር ግን ኢትዮጵያ በየ ነገስታቱ አለቃ ገብረሃናን የመሰሉ አጫዋችች ቤተ መንግስት አካባቢ አይጠፉም ነበር። በመንጌ ጊዜም አቶ ቆምጬ አምባው የአለቃ ገብረሃናን ያህል የኢሰፓ አባላትን እና የዘመኑን ሰው በድርጊታቸው ያዝናኑት ነበር ሲባል ሰምተናል።

በአቶ መለስ ጊዜ ግን ገብረሃናውም፣ ቆምጬ አምባውም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም እርሳቸው ነበሩ! (እዚች ጋ አንድ ማስታወቂያ አለኝ… “አቶ መለስን እስቲ ተዋቸው” ለምትሉኝ ወዳጆቼ በሙሉ እንደዚህ አትብሉኝ! አልተዋቸውም። ጋሽ ሃይሌ እንዳሉትም የሳቸው ነገር የምንተወው አይደለም እየተወሱ እየተዘከሩ ለዘላለም ይኖራሉ! በዚህ ላይ ድርድር የለም) ሳቄ ሳይመጣ ከቅንፍ ልውጣ!

እና አቶ መለስ ከጠቅላይነታቸው በተጨማሪ የምክር ቤቱ አጫዋችም ነበሩ!

ታድያ ለሃያ አንድ አመታት ጨዋታ የለመደ ምክር ቤት ዛሬ ማን ያጫውተው? ዛሬ ማን ያስቀው? አቶ ሃይለማሪያም እንደሆኑ ከአቶ መለስ እስካሁን በቅጡ የኮረጁት ቁጣቸውን ብቻ ነው።

ሰሞኑን የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ “ሀገራችን ኢትዮጵያን እና ህዝቧን እግዚአብሔር በበረከቱ ይጎብኝ” ብለው ሲናገሩ ሙሉ የምክር ቤት አባላቱ ከት ብለው ሲስቁ የሚያሳይ ቪዲዮ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ አይተናል።

በርግጠኝነት የፓርላማ አባላቱን ምን አሳቃችሁ? ብለን ብንጠይቃቸው “…እና ፓርላማ የመጣነው ምን ልናደርግ ነው!?|” ብለው ባይመልሱ ውርድ ከራሴ!

እውነታቸውን ነው ገና ለገና ዛሬ እርሳቸው ሞቱ ተብሎ ፓርላማው ሳይሳቅበት ይዋል እንዴ!?

የሚገርመው ግን “መለስ አልሞቱም” የሚለው ንግግር ያላሳቃቸው ተበካዮቻችን (በቅንፍ የታይፕ ግድፈት አለ የምትሉ እያስተካከላችሁ እንድታነቡ መፈቀዱን እገልፃለሁ!) “እግዚአብሔር ይባርከን!” ሲባል ከት ብለው መሳቃቸው ነው። ይሄኔ ነው መሳቀቅ ያለችው ማን ነበረች!? ለማንኛውም ፓርላማውን መሳቂያ አድርገውት የሄዱት እሳቸው ናቸው እና አዎ መላቀቅ የለም “ዘላለም እንደተዘከሩ” ይኖራሉ!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 20, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 20, 2012 @ 9:54 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar