www.maledatimes.com ለአቶ ሠይፈ ደርቤ የአዲስ ዘመን የፖለቲካና ኤኮኖሚ አምድ ምክትል ዋና አዘጋጅ በአደባባይ የተላከ ደብዳቤ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ለአቶ ሠይፈ ደርቤ የአዲስ ዘመን የፖለቲካና ኤኮኖሚ አምድ ምክትል ዋና አዘጋጅ በአደባባይ የተላከ ደብዳቤ

By   /   October 20, 2012  /   2 Comments

    Print       Email
0 0
Read Time:11 Minute, 27 Second

ከግርማ ሠይፉ ማሩ በአደባባይ የተላከ ደብዳቤ ለአዲስ ዘመን የፖለቲካና ኤኮኖሚ አምድ ምክትል ዋና አዘጋጅ

ለአቶ ሠይፈ ደርቤ የአዲስ ዘመን የፖለቲካና ኤኮኖሚ አምድ ምክትል ዋና አዘጋጅ በአደባባይ የተላከ ደብዳቤ
ከግርማ ሠይፉ ማሩ
በጣም የሚገርመኝ ለመፃፍ የሚፈልጉ ሰዎች ማንበብ ያለመፈለጋቸው እና የተፃፈን ነገር ትተው በጆሮዋቸው የሰሙትን አንገታቸው ላይ ባለው ቅል ነገር (ጭንቅላት ላለማለት) አዛብተው በመተርጎም መከራቸውን ሰለሚያዩ ነው፡፡ ይህንን ከበድ ያለ አረፍተ ነገር ለመስራት የተገደድኩት አዲስ ዘመን የሚበል እድሜ ጠገብ ለእርጅና እንጂ ለአረጋዊነት ያለበቃ ጋዜጣ የፖለቲካና ኢኮኖሚ አምድ ምክትል ዋና አዘጋጅ ነኝ ባይ (ለነገሩ አዲሰ ዘመን ከሠይፈ ደርቤ የተሻለ አዘጋጅ ቢኖረው ነው የሚገርመው) ተመቸኝ ብሎ የዘላበደውን ፅ

ሁፍ በሰዎች ጥቆማ አንብቤ ነው፡፡ እዛች ገፅ ከዚህ በፊት ሰለኔ ብዙ ተፅፎዋል ግን በብዕር ስም ሰለሚፃፍ ቁብ አይሰጠኝም አሁንም እንደዚያው መስሎኝ አልፌው ሳለ አንደ ወዳጄ ደውሎ የጋዜጣው አዘጋጅ መሆኑን ነገረኝ፡፡ ከዚያም ይህንን ማለት ፈለግሁ፡፡ ሰለ ጋኔልና ሰይጣን የፃፈውን በተመለከት እራሱን የሚመለከት እንደሆነ ለዚህም ፀበል ተመላላሽ እንደ ነበር ሰለተረዳው አልፌዋለሁ፡፡ ጣዖቱ ሲነካበት የተንዘፈዘፈውም እርሱ ሠይፈ ደርቤ ነው፡፡ ሲቀጥልም ጓዶቹ ናቸው፡፡
አቶ ሠይፈ ደርቤን በአንቱታ መጥራት ውርደት ሰለሚሆን ሳይሆን ለፅሁፌ ሰለማይመቸኝ አልሞክረውም፡፡ ግን እኔ እንደርሱ ሰድ ሰለአልሆኑክ አሳዳጊ የበደለው ብዬ ወላጆቹን ወይም አሳዳጊዎቹን መንካት ሳይኖርብኝ ሰድነቱን እራሱን ችሎ እንዲሆን እፈልጋለሁ፡፡ አቶ ሠይፈ ከፈለግህ በግል ወይም ከመሰሎችህ ጋር አቶ መለስን ብተፈልግ ፎቶ ሰቅለህ ከተመቸህ ሀውልት አሰቀርፀህ ማምለክ መብትህ ነው፡፡ መብትህ ያልሆነው ግን እኔ አና መሰሎቼን አብረን እናምልክ ስትል ነው፡፡ እኔ የማመልከው አንድ አምላክ አለኝ መለስ ለኔ አንድ ሰው ናቸው በታሪክ አጋጣሚ ይህችን ሀገር ለሃያ አንድ ዓመት ለመምራት እድል ያገኙ ግን እድሉን አሟጠው መጠቀም ያልቻሉ፡፡ እሺ አሁን ምን ትሆናለህ፡፡ ባንተ ቤት አቶ መለስ እንዴት እንዲ ይባላሉ ልትል ትችላለህ ሀቁ ግን ይህ ነው፡፡
ፕሬዝዳንቱ ካነበቡት የመክፈቻ ፅሁፍ አንዱን ላካፍልህ “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሀገራችን ከሰማኒያ በመቶ የማያንሱ በሽታዎች በመከላከል ሊወገዱ እንደሚችሉ ባመላከቱት መሰረት ….” ይላል፡፡ አቶ ሠይፈ በዓለም ላይ ጤና የሚባል ትምህርት ከተጀመረ ጀምሮ በተለይም የህዝብ ጤና አጠባበቅ (Public Health) ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ አቶ መለስ ሳይፈጠሩ ጭምር በዝቅተኛ ኑሮ የሚኖሩ ሀገሮች/ወይም ማህበረስብ ዘንድ ያለው የጤና ችግር አሁን አንተ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ናቸው ያመለከቱት የምትለው መሆኑ እንደ መደበኛ ሀቅ የተወሰደና የተመዘገበ ነው፡፡ ሰለዚህ የአቶ መለስን አመላካችነት አይፈልግም በጤና ሴክትር ያሉ ሰዎች ይህንን ሀሁ ያውቁታል፡፡ ደርግም ይህን ይል እንደነበር ማወቅ አለብህ፡፡ ይሁን ከተባለ ደግሞ አንተ መመልከት ቸግሮህ አመላክተው ከሆነ ላንተና ለጋዶችህ ነው የሚሆነው፡፡ ሰለዚህ ይህ የሀቅ ስህት ሰለሆነ ሪፖርቱ ውስጥ መኖሩ ሪፖርቱን ሸፋፋ ያደርገዋ ነው ያልኩት፡፡
የኤኮኖሚ አምድ ምክትል አዘጋጁ “ አሁን ባለው ሁኔታ 40 በመቶ ደርሶ የነበረው የዋጋ ግሽበት ወደ 19 በመቶ ወርዷል በተያዘው በጀት አመት 1 በመቶ ዝቅ ለማድረግ እሰከመጨረሻ ባለው አቅም ለመጠቀም ቁርጠኛ ሆኖዋል … 11 በመቶ የነበረውን እድገትም 14.9 በመቶ ለማድረስ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማድረጉን ተያይዞዋል፡፡” ይለናል በፅሁፉ አንገቱ ላይ የተሸከመውን ጭንቅላቱን ሊጠቀምበት አልፈለገም አለቆቹ ቢሉ እንኳን እንዴት ተደርጎ ብሎ ለመጠይቅ ከጭንቅላቱ ሆዱ በልጦበታል፡፡ ለነገሩ ከጠበል ተመላላሽ ታካሚ ከዚህ በላይ የኢኮኖሚ ትንተና መጠበቅ ተገቢ አይሆንም፡፡ የዛሬ ዓመት ግን ይህንን ያነበበ ሁሉ ይህችን አንድ በመቶ የዋጋ ግሽበት እና 14.9 በመቶ የኤከኮኖሚ ዕድገት ከአዲሰ ዘመን ምክትል አዘጋጅ ተብዬ እንጠብቃለን፡፡ በነገራችን ላይ የፕሬዝዳንቱ ፅሁፍ ላይ የዋጋ ግሽበቱ 21 በመቶ ሲሆን የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ደግሞ 19 በመቶ ደርሶዋል ተብሎዋል፡፡ የቱ ልክ እንደሆነ ጋሽ ጋዜጠኛ አጣርተው ይንገሩን፡፡
የእብድ መካሪ የሆነው አዲሰ ዘምን ላይ በደረተው ድሪቶ እንዲህም ብሎ መክሮኛል “ አቶ ግርማና ፓርቲያቸው በትክክል መረዳት የሚኖርባቸው ከእዚህ ህመም የመዳን መፍትሔው የሚመነጨው የመለስን ራዕይ የማሳካቱን መስመር በመከተል መሆኑን ነው፡፡ ….” ይላል፡፡ የፖለቲካ አምድ ምክትል አዘጋጅ ነው እንዳትረሱት አማራጭ የሚባል ፖለቲካ አሰተሳሰብ ግን አያውቅም፡፡ በአንድ ቦይ እንድነፈስ ይፈልጋል፡፡ ለአዲስ ዘመን አዘንኩኝ የዚህ ዓይነት አዘጋጅ ይዞ በየቀኑ ሲወጣ፡፡ እኛ ሞተው ሳይሆን በቁም እያሉ የመረጡልን አብዮታዊ ዲሞክራሲ መስመር ልክ አይደለም ብለናቸዋል እናም ልክ አይደለም፡፡ አሁን ሰለሞቱ ልክ አይሆኑም፡፡ ልክ አይደሉም ሲባል ዛር የሚነሳብህ ከሆነ እና የሚያንዘፈዘፍ ከሆነ ሲያንዘፈዝፍ ይክረም እንጂ ይህንን ከማለት የሚያግድኝ ያለ አይመስለኝም፡፡ ኢህአዴግ የሚከተለው መስመር በሙሉ የመለስ ነው ከተባለ ልክ አይደሉም ያልናቸው በሙል ልክ አይደሉም፡፡
አደራ ያቋረጥከው ጠበል ካለ በመጀመሪያ ጠበሉ እንደሚያድንህ አምነህ፣ ጣዖት ማምለክ ትተህ፣ ይህንንም ለንስዓ አባትህ ነገረህ ጠበሉን ብትቀጥል መሃሪና ቸር የሆነው አመላክ ከአደረብህ እርኩስ መንፈስ ያድንሃል፡
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 20, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 20, 2012 @ 11:04 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

2 thoughts on “ለአቶ ሠይፈ ደርቤ የአዲስ ዘመን የፖለቲካና ኤኮኖሚ አምድ ምክትል ዋና አዘጋጅ በአደባባይ የተላከ ደብዳቤ

  1. Why YOu said Addis zemen? woyane Zemen woyane’s news paper even not deserving it old zemen. what can they do all of Ethiopians become their chair and they are enjoying by our poverty, freedom.

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar