www.maledatimes.com ሰራዊቱን ዝም ለማሰኘት የታቀደ የመጀመሪያ ዙር ስራ የተቃዋሚ ደጋፊ የተባሉ ወታደሮችን ለማጥቃት የታቀደ ግምገማ ሊደረግ መሆኑ ታውቋል ቆንጂት ስጦታው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሰራዊቱን ዝም ለማሰኘት የታቀደ የመጀመሪያ ዙር ስራ የተቃዋሚ ደጋፊ የተባሉ ወታደሮችን ለማጥቃት የታቀደ ግምገማ ሊደረግ መሆኑ ታውቋል ቆንጂት ስጦታው

By   /   June 23, 2017  /   Comments Off on ሰራዊቱን ዝም ለማሰኘት የታቀደ የመጀመሪያ ዙር ስራ የተቃዋሚ ደጋፊ የተባሉ ወታደሮችን ለማጥቃት የታቀደ ግምገማ ሊደረግ መሆኑ ታውቋል ቆንጂት ስጦታው

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 9 Second
ቆንጂት ስጦታው – ከጦር ሃይሎች የተገኘው መረጃ እንደተመለከተው በመከላከያ ሰራዊቱ ሁሉም እዞች በወታደሮች ላይ ግምገማ ሊደረግ መሆኑ ታውቋል::የግምገማው ዋናው ሂደት በሰራዊቱ ውስጥ የተገኘው የኢሕአዴግ ድምጽ አነስተኛ መሆኑ እና ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ከሚል አንጻር ተጠርጣሪ የተቃዋሚ ደጋፊ የተባሉ ወታደሮችን ለማጥቃት የታቀደ ግምገማ ሲሆን በግምገማው ላይ ሞባይሎች እንደሚፈተሹ እና ተቃዋሚዎችን በተመለከት ውስጥ ለውስጥ ፕሮፓጋንዳ ያራግባሉ እንዲሁም አለማቀፍ ጉዳዮችን በተመለከተ ከሚዲያ መረጃዎችን ይዘው መተው ያወራሉ የሚባሉ ወታደሮች የግምገማው ሰለባ እንደሚሆኑ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል::የመከላከያ ሰራዊቱ ከሲቭል ደህንነት እና ከኢንሳ በተመደቡ እና የወታደሩን ካኪ ለብሰው በመመሳሰል በሚሰልሉ የሕወሓት አባላት አቅራቢነት ወንጀሎች ተቀነባብረው ግምገማውን እንደሚያጦዙት ይጠበቃል ሲሉ ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል::

የለውጥ ፈላጊ ሃይሎችን ደግፋችሁሃል በሚል ለጥቃት የተዘጋጀው ይህ ግምገማ አለመተማመን እና ጥርጣሬ በሞላው የመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ልዩነቶችን በማስፋት በአንድ ብሄር የበላይነት የሚተዳደረውን አምባገነን ወታደራዊ አመራርን በማጠናከር ሌሎች ብሄሮች በፍርሃት እና በስጋት እንዲኖሩ ለማሸማቀቅ የሚያደርግ እንዲሁም ሰራዊቱን ለለውጥ ያነሳሳሉ የሚባሉ መኮንኖችን እና ወታደሮችን ሰብስቦ ለማሰር እና ደብዛቸውን ለማጥፋት የታቀደ እንደሆነ ታውቋል:ግምገማው የሚመራው በተለያዩ እና በጄነራልነት ማእረግ ባላቸው የሕወሓት መኮንኖች ሲሆን ሰራዊቱን ዝም ለማሰኘት የታቀደ የመጀመሪያ ዙር ስራ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ 450 የሕወሓት አባላት ተመልምለው ለወታደራዊ ስልጠኛ በሚል በተለያዩ የምስራቅ አውሮፓ አገሮች ለትምሕርት ሊላኩ መሆኑ ሲታወቅ ከአንድ ብሄር ብቻ ለምን/እንዴት ይህ ሆነ የሚል ጥያቄ መነሳቱን እና ምንም አይነት ምላሽ እንዳልተሰጠው ታውቋል::ምንጮቹ አያይዘው እንዳሉት ልሰላም አስከባሪ ሃይል ከፍተኛ አመራር እንዲሆኑ ለስልጠና የታጩት የሕወሃት አባላት ጉዟቸው እንደማይሰረዝ እና ጉዞውን ለተቃወሙት መኮንኖች ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ገልጸዋል::
ቆንጂት ስጦታው

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on June 23, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 23, 2017 @ 1:17 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar