www.maledatimes.com የምድራችን ታላላቅ ሃብታሞች ኑሮ ምን ይመስላል? ቴዲ አድማስ ሬድዮ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የምድራችን ታላላቅ ሃብታሞች ኑሮ ምን ይመስላል? ቴዲ አድማስ ሬድዮ

By   /   August 3, 2017  /   Comments Off on የምድራችን ታላላቅ ሃብታሞች ኑሮ ምን ይመስላል? ቴዲ አድማስ ሬድዮ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 59 Second

ብዙዎቻችን የኑሯችንን ደረጃ ከምናገኘው ሃብት ጋር እንዲመሳሰል ወይም እንዲመጣጠን እንጥራለን። በአንድ ሺብር ደሞዝ በአንድ ክፍል ውስጥ የሚኖር ሰው፣ ደሞዙ ሁለት ሺብር ከገባ ፣ የሚኖርበትንም ቤት ወደ ሁለት ክፍል ማሳደጉ፣ በፊት ይነዳው የነበረውን አሮጌ መኪናም በአዲስ መቀየሩ የማይቀር ነው። ገቢያችን በጨመረ ቁጥር የመኪናችን ዕድሜና ሞዴልም እየተቀየረ፣ የመዝናናታችን መጠን እየጨመረ ይሄዳል። ፍላጎታችን ከገቢያችን እኩል ስለሚጨምር ግን ርካታው ብዙም አይኖረንም። በተለይ አንዴ ወደ ላይ ከወጣን በኋላ ተመልሶ ወደታች ወርዶ መኖር ለብዙዎቻችን የማይታሰብ ነው። ስለዚህ አንዴ የለመድነውን የተደላደለ የኑሮ ሁኔታ ላለማጣት፣ አዲስ ሞዴል መኪናችን እና አዲሱ ምርጥ ቪላችን እንዳይወሰድብን በሥራ ተወጥረን ስንለፋ እንገኛለን።
የዓለም ሃብታሞች ንሮ ግን እንደዚህ አይደለም ይላል – ቢዝነስ ኢንሳይደር ባወጣው ዘገባ … የአንዳንዶቹን እንመልከት።

የምንጀምረው ከዋረን ባፌት ነው።
– አሜሪካዊው ዋረን ባፌት ከዓለም ሶስተኛ ሃብታም ሲሆን፣ የሃብቱ መጠን 74 ቢሊዮን ዶላር ነው። ዋረን ባፌት ታዲያ ቢሊየነር ነኝ፣ እንኳን ተጠቅሜበት ፣ ቆጥሬ እንኳን የማልጨርሰው ገንዝብ አለኝ ብሎ ቅንጡ ኑሮ ውስጥ አልገባም። ዋረን ባፌት ዛሬም የሚኖረው ከብዙ ዓመት በፊት በ31 ሺ ዶላር በገዛው ቤቱ ውስጥ ነው። የ እጅ ስልክ እና ኮምፒውተር የሉትም። የቅርብ ጓደኛው እና ሌላው ሃብታም ቢል ጌትስ ሊጠይቀው እሱ ወዳለበት ከተማ ሲመጣ ከ ኤርፖርት የተቀበለው ራሱ እየነዳ ሄዶ ነው። ምርጥ ሬስቶራንት አማርጦ መብላት አይፈልግም። በርገር ኪንግ፣ ዳያሪ ኩዊን ያዘወትራል፣ ዳየት ኮካኮላ ነው መጠጡ። ለስናክ ቺቶስ እና ቺፕስ ካገኘ በቂዬ ነው ይላል።
በአንድ ዓመታዊ የንግድ ስብሰባ ላይ ስለኑሮው ሲናገር “ያለኝ ኑሮ በቂዬ ነው፣ አሁን 7 እና 8 ቤት ቢኖረኝ ምን ያደርግልኛል? ለኑሮ የሚያስፈልገኝ አለኝ፣ ደስተኛ ነኝ” ነበር ያለው።

– ማርክ ዙከርበርግ የፌስቡክ ፈጣሪና ባለቤት ሲሆን፣ የ70ቢሊዮን ዶላር ባለቤት ነው። ማርክ አለ የተባለ ልብስ ከዓለም ገበያዎች አማርጦ መልበስ ሲችል፣ ዘወትር በቲሸርትና በጂንስ ነው የሚታየው። ስለሱ ሲጠየቅም “ልብስ አብዝቼ በማማረጥ የማጠፋውን ጊዜ ለሥራ ባውለው ይሻላል” ሲል መልሷል። የ 33 ዓመቱ ዙከርበርግ 99 በመቶ የሚሆነውን ሃብቱን እስከ ህይውቱ መጨረሻ ባለው ጊዜ ውስጥ ለበጎ አድራጊዎች እንደሚሰጥ ነው የተናዘዘው። በ2012 ዓ.ም ፐርሲላ ቻን የተባለችውን ሚስቱን ካገባም በኋላ ማክዶናልድ መመገቡን አላቆመም። የሚኖረው ፓሎ አልቶ የተባለ ከተማ ሲሆን፣ ከሚስቱና አንድ ልጁ ጋር የሚኖርበት መኖሪያ ቤቱ 7ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ነው። በአካባቢው የቤት ዋጋ የሱ ውድ እንደማይባል ይነገራል። ከሱ በላይ ዋጋ የሚያወጡ በርካታ ቤቶች ያሉበት ሰፈር ነው። በ2014 አረጀች ያላትን የ30ሺ ዶላር አኩራ መኪናውን አውቶማቲክ ባለሆነችና ማንም ሰው ሊገዛት በሚችል ቮልስዋገን ቀይሯታል።

– ካርሎስ ስሊም ሜክሲኳዊ ቢሊየነር ነው። ሃብቱ 65 ቢሊዮን ዶላር ነው። የ77 ዓመቱ ካርሎስ ቀሪ ዕድሜውን ቀርቶ የልጁንም ዕድሜ ቢጨምር እንኳን ሳይሰራ ድልቅቅ ብሎ ለመኖር ይችላል፣ ነገር ግን ቀን ሌሊት ሥራ ላይ ነው። ያገኘውን ትርፍ በሙሉ መልሶ ሥራው ላይ በማዋል ይታወቃል። እንደማንኛውም ሃብታም የግል አውሮፕላን ወይም የግል ጀልባ የለውም። ዛሬም የሚነዳው የድሮ መርሰዲስ ቤንዝ መኪና ነው። ማስታወሻ ዛሬም የሚይዘው ከኪሱ በማይለያት ኖት ቡክ ነው። ከነቤተሰቡ የሚኖረው እዚያው ሜክሲኮ 6 መኝታ ቤት ባለው መኖሪያው ሲሆን፣ እዚህ ቤት ሲኖር 40 ዓመት ሆኖታል፣ ቤት አልቀየረም። እሱም ቤተሰቡም ቤት ውስጥ አብስለው ነው የሚመገቡት።

– ቻርሊ ኤርጋን የዲሽ ኔትወርክ ኩባንያ ባለቤት ሲሆን፣ 19 ቢሊዮን ዶላር ሃብት አለው። ቻርሊ በሚመራው ቀላል ህይወት ይታወቃል። የ 64 ዓመቱ ቢሊየነር፣ ዛሬም ድረስ ጠዋት ሥራ ሲሄድ ምሳ ከቤቱ ቋጥሮ ነው የሚወጣው፣ የምሳ ሰሃን እና አንድ ጌቶሬድ ሁልጊዜ ከቤቱ ይዞ የሚወጣቸው ነገሮች ናቸው። ለሥራ ሌላ አገር ወይም ከተማ ቢሄድ ከሥራ ባለደረቦቹ ጋር ክፍል ተጋርቶ በማደርም ይታወቃል።

– ዛራ የተሰኘው የልብስና ፋሽን መደብር በዓለም ይታወቃል። የዚህ ኩባንያ ባለቤት ደግሞ አማንኮ ኦርቴጋ ይባላል፣ ኦርቴጋ በ82 ቢሊዮን ዶላር ከዓለም 3ኛው ሃብታም ተደርጎ ይቆጠራል። የስፔን ተወላጁ ኦርቴጋ ዛሬም ድረስ ከሚስቱ ጋር ድሮ ጀምሮ ይሄደበት የነበረው ቡና መሸጫ ሱቅ ነው ሄዶ ቡና የሚጠጣው፣ ምሳውን የሚበላው በዋና መሰሪያ ቤቱ ካፊቴሪያ ከሌሎች ሰራተኞች ጋር አብሮ ተሰልፎ ነው። ልክ እንደ ፌስቡኩ ማርክ ዙከርበርግ ሁሉ፣ ኦርቴጋም ቀለል ያለ ጃኬትና ካኪ ሱሪ ሁልጊዜ የሚያደርገው ልብስ ነው። 45 ሚሊዮን ዶላ የሚያወጣ አውሮፕላን በርግጥ አለው፣ ግን ብዙውን ጊዜ በሥራ ላይ ስለሚያሳልፍ አውሮፕላኑን ተጠቅሞበት አያውቅም።

– አይኪያ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች መሸጫ ሱቅ ነው፣ የስዊድን ኩባንያ የሆነው አይኪያ ባለቤት ደግሞ ኢንግቫር ካምፓርድ ይባላል። ካምፓርድ 43 ቢሊዮን ዶላር ሃብት አለው። በአውሮፓ ከዋና ሃብታሞች አንዱ ነው። ነገር ግን ይህን ያህል ሃብት ቢኖረውም ዛሬም የሚነዳው ከ10 ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው ቮልቮ መኪና ነው፣ አንዳንድ ጊዜም በህዝብ ትራንስፖርት እንደሚጠቀም ይነገራል። ቤቱ ግራንውንድ ፕላስ ዋን የሆነ የድሮ ቤት ነው።

– የህንዱ ሃብታም አዚም ፐርሚጂ ይባላል፣ ዊፕሮ የተሰኘ ኩባንያ ባለቤት ሲሆን፣ ሃብቱ 15 ቢሊዮን ዶላር ነው። ይህ ቢሊየነር ታዲያ ለአንዳንዶች ቆንቋና ቢመስልም፣ ለሱ ግን ቆንቋና ሳልሆን ጥንቁቅ ነኝ ይላል። የ71 ዓመቱ ፐርሚጂ ከአየር ማረፊያ ወደ ቤቱ ሲመጣ፣ ባለሶስት እግሮቹን የህንድ ትራንስፖርት መንገዶች (ባጃጆች) ተከራይቶ ነው። አውሮፕላን ላይ የሚሳፈረው ኢኮኖሚ ክላስ ነው፣ የሚነዳው አዲስ ሳይሆን ሌሎች የተጠቀሙባቸውን ዩዝድ የሆኑ መኪኖችን ነው። በዋናው መስሪያ ቤት ያሉ ሰራተኞቹንም ሁልጊዜ ሲወጡ መብራት ማጥፋት እንዳይረሱ ማስታወሻ እንደላከ ነው።

– በመጨረሻም ጁዲ ፎክነር ጋር ደረሰን፣ ጁዲ ኤፒክ ሲስተምስ የተሰኘ ኩባንያ ባለቤት ነች። 5 ቢሊዮን ዶላር ሃብትም አላት። የ 73 ዓመቷ ጁዲ የቅንጦት ኑሮ አይመስጣትም። ባለፉት 15 ዓመታት የቀየረችው አንድ መኪና ብቻ ነው። በዊስኮንሰን ከባለቤቷ ጋር የምትኖርበት ቤት ቢያንስ ሰላሳ ዓመት ኖራበታለች። አሁን የሃብቷን ግማሽ ለችግረኞች ለመስጠትም ወስናለች።

እንግዲህ በዓለም የገበያ ጥናት መሰረት የዓለም ሃብታም የሚባል ዝርዝር ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ቢያንስ 30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት ያላቸው ናቸው። እዚህ ዝርዝር ውስጥ ማለትም 30 ሚሊዮን እና ከዚያ በላይ ገንዘብ ያላቸው ሰዎች በዓለም ላይ 226ሺ 450 መሆናቸው ሲነገር፣ በጠቅላላው ቢደመር 27 ትሪሊየን ዶላር ሃብት እጃቸው ላይ አለ። ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 9.6 ትሪሊየኑ ካሽ ሲሆን፣ ቀሪው ንብረት ነው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on August 3, 2017
  • By:
  • Last Modified: August 4, 2017 @ 9:56 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar