“ከኢትዮጵያውያን ወጣቶች 50% ጫት ቃሚ ሆነዋል፣ ባህር ዳር ከተማ የቀድሞ ፕሬዚዳንት መንግስቱ ሃይለማርያም ሲመጡ ያርፉበት የነበረ ቤት ጫት መቃሚያ ሆኖ አግኝቼዋለሁ” ኒውዮርክ ታይምስ::

አዘጋጅቶ ያቀረበልን አድማስ ሬዲዮን እናመሰግናለን !!

_______
(Admas Radio) ኒውዮርክ ታይምስ ባለፈው ጁላይ 22/2017 ዕትሙ ከኢትዮጵያውያን ወጣቶች 50% የሚሆኑት ጫት ቃሚ ሆነዋል፣ ኢትዮጵያ በቃሚነት በዓለም እየታወቀች ነው የሚል ሰፊ ዘገባ አውጥቷል። ዘገባው በዚህም ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ ሴቶችም ዋናዎቹ ቃሚዎች ሆነዋል ሲል ያነጋገራቸውን ሰዎች ጠቅሶ አስነብቧል። አድማስ ሬዲዮ ወደ አማርኛ መልሶታል።

********
የሺመቤት አስማማው የ 25 ዓመት ወጣት ነች፣ በቀን ቢያንስ ሶስት ጊዜ ጫት ለመቃም ቤቷን አንጥፋ ትቀመጣለች፣ እሷ እንደምትለው “ሙድ” ውስጥ ለመግባትም፣ የቡና ሲኒ ደርድራ እጣን አጭሳ ሳር ጎዝጉዛ ቤቷን ታደምቀዋለች። ለምን ይህን እንደምታደርግ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ ሲጠይቃት “በቃ ደስ ይለኛል” ነበር ያለችው።

የሺመቤት፣ ቤቷ ብቻ ሳይሆን ሥራ ስትሄድም ጫት ከጉንጯ ሥር አይጠፋም።
ኒውዮርክ ታይምስ ይቀጥላል። ኢትዮጵያውያን ጫት በመቃም የረዥም ዓመታት እውቅና አላቸው ፣ በፊት በፊት ግን በአንዳንድ ፣ እንደ ሐረር ዓይነት የ እስልምና ተከታዮች በብዛት ባሉባቸው አካባቢዎች የተወሰነ ሆኖ ቆይቷል። አሁን ግን ያ ተቀይሯል። አሁን ሁሉም ከተማ ሐረርን ሆኗል ማለት ይቻላል። ጫት የማይቃምባቸው ቦታዎች እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው። ገጠራማ የሚባሉትና ቀድሞ ጫት የማይታወቅባቸው ወይም ሃጢያት ነው ብለው የሚያምኑ አካባቢዎች ጭምር ተዛምቷል።

አንዳንድ ቦታዎች አሁንም ወጣቶቹ ከወላጆቻቸው ተደብቀው እንደሚቅሙ ይናገራሉ። አቢ የተባለ የደብረማርቆስ ልጅ ፣ እሱና ጓደኞቹ ከወላጆቻቸው ተደብቀው እንደሚቅሙ ይናገራል። “ካዩንማ በቃ አለቀልን፣ ስለዚህ ተደብቀን እንቅማለን፣ ድንገት ከመጡብንም አንድ የምንነጋገርበት ኮድ አለን፣ በሱ አውርተን እንደብቀዋለን” ይላል።

**************
በኦፌሲል ተደረገ የተባለ ጥናት እንደሚያሳየው ከኢትዮጵያ ወጣቶች ቢያንስ ግማሽ ያህሉ ጫት ቃሚ ሆኗል። “አገር መገንባት ያለበት ወጣት ቁጭ ብሎ ጫት ሲቅም መገኘቱ አሳስቦናል” ሲሉ ባለሥልጣናት ነግረውኛል ይላል ኒውዮርክ ታይምስ።

በአገሪቷ ውስጥ 1.2 ሚሊዮን ኤክር መሬት በጫት ምርት እንደተሸፈነ ይነገራል። ይህ ከ20 ዓመት በፊት በጫት ተይዞ ከነበረው መሬት በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ነው። ኢትዮጵያ አሁን ከጫት የምታገኘው ገንዘብ ከቡና ከምታገኘው ሁሉ በልጧል። ጫት ተሸጦ ገንዘብ ማስገኘቱም፣ በርካታ ገበሬዎችን ምርቶቻቸውን ወደ ጫት እንዲቀይሩ ገፋፍቷቸዋል። በተለይም ይላል ኒውዮርክ ታይምስ .. በተለይም መንግስት ከገበሬዎች ላይ መሬት እየወሰደ ለውጭ ኢንቨስተሮች በመስጠቱ ገበሬዎቹ በቀራቸው ትንሽ መሬት ላይ ጫት ተክሎ ገንዘብ ማግኘትን አማራጭ አድርገውታል ይላል።

***********
በኢትዮጵያ ውስጥ በቻይናውያን የሚሰሩ ትላልቅ መንገዶችና የባቡር ፕሮጄክቶች ቢኖሩም፣ ትላልቅ ህንጻዎች በየቦታው እየተገነቡ ቢሆንም፣ መቶ ሚሊዮን ከሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ 70% የሚሆኑት ወጣቶች የሥራ እጥረት መኖሩን በምሬት ይናገራሉ። ይህ ሁሉ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እያለ ወጣቶች ሥራ አጥተው መባዘናቸው አስገራሚ ነው ይላል ኒውዮርክ ታይምስ። እናም ወጣቶቹ “ጫት ላይ ተወዝፈን የምንውለው ሥራ ስላጣን ነው” ሲሉ መናገራቸውን ይጠቅሳል።

አቶ ሺደግፍ የተባሉ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የህግ ባለሙያ ጫት በከተማቸው ትልቅ ችግር እየሆነ መምጣቱን ይናገራሉ። እንደሳቸው አባባል ግማሽ የሚሆነው የጎንደር ወጣት ጫት ይቅማል። ምክንያት ይሆናል የሚሉትንም ያክሉበታል። “እኔ እንደሚመስለኝ ፣ ወጣቱ ቃሚ የሆነው በቂ የሥር ዕድል ስለሌለ ነው፣ ስለዚህ አብዛኛው ጫት አሻሻጭና ቃሚ ሆኗል።

ወንጀልም የዚያን ያህል እየጨመረ ነው። ሁሉም ቃሚ ከሆነ ደግሞ አገር ወደ ውድቀት እያመራች ነው ማለት ነው” ሲሉ አቶ ሺደግፍ መናገራቸውን ኒውዮርክ ታይምስ ይጠቅሳል።

ቢያንስ 10 ዓይነት ጫት እንዳለ ጥናት አድራጊዎች ይናገራሉ። የጫት ዋጋም እንደጫቱ ዓይነት ይለያያል፣ “ምርቃና” ወደሚባለው የመጨረሻ ደረጃ የሚያደርስበት ፍጥነትም እንደ ጫቱ ዓይነት ይለያያል። የአሜሪካ መንግስት የበሽታ መቆጣጠሪያ መስሪያ ቤት ባደረገው ጥናት “ጫት አጉል ህልምና ምኞት ውስጥ ይከታል፣ ወደ ወንጀል ያምራል፣ ራስን ለማጥፋት ይዳርጋል፣ ጭንቀትና መረበሽን ያስከተላል” .. በመሆኑም አሜሪካ ውስጥ ህገወጥ ዕጽ ሆኖ ይቆጠራል።

“ጫት የአዕምሮም የአካልም ችግር ነው” የሚሉት ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሳይካትሪ ዲፓርትመንት ሃላፊ ዶክተር ዳዊት ወንድማገኝ ናቸው። እንደሳቸው አባባል “ጫት እንደ ባህል ተቆጥሯል፣ በአንድ ጊዜ በህግ ለማገድ መሞክር አስቸጋሪ ነው፣ ምክንያቱም አንዳንዶች ከሃይማኖትና ከባህል ነጻነት ጋር ስለሚያያዙት ነው” ይላሉ።

**********
ሙሉጌታ ጌታሁን 32 ዓመቱ ሲሆን የባህር ዳር ነዋሪ ነው፣ የተማረው አርክቴክቸር ነው፣ ነገር ግን በተማረበት ሥራ ባለማግኘቱ በቀን ሠራተኛነት እየሰራ ይገኛል: እሱ እንደሚለው ከሆነ በተለይ ሥራ የሌለው ቀን ትልቁ መዝናኛው ጫት መቃም ነው። “ዘና የምለው ጫት ስቅም ነው” ይላል። ከጫት በኋላ ደግሞ “ጨብሲ” የሚሰኘውን የተገኘውን ዓይነት የአልኮል መጠጥ በመጠጣት ማሳረጊያውን ያደርጋል።

የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ በጎበኘው በአንድ የባህር ዳር ከተማ ጫት ቤት ውስጥ ፣ በርካታ ወጣቶች መሬት አንጥፈው ጫት ይቅማሉ፣ የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ተከፍቷል። ራሳቸውን እየወዘወዙ ጉንጫቸውን በጫት ወጥረው በሃሳብ ነጉደዋል ይላል። ይህ ከውጭ ምልክት ባልተጻፈበት፣ ግን ደምበኞቹ ብቻ በሚያውቁት ጫት ቤት ውስጥ ነው።
ጋዜጠኛው ዞር ዞር ብሎ እንዳየው በአባይ ወንዝ ዳር በሚገኙ ዛፎች ሥርም አንጥፈው ቁጭ ብለው የሚቅሙ በርካታ ወጣቶችን አግኝቷል። በሚገርም ሁኔታ ከዚህ በፊት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ባህር ዳር ሲመጡ ያርፉበት ነበር የተባለ የ እንግዶች ማረፊያ ውስጥም ፣ ወጣቶች ቁጭ ብለው ጫት ሲቅሙ እንዳገኛቸው ጋዜጠኛው ይናገራል።

"I have found 50% of Ethiopia's youth working as a chemist, and I found the house where Mengistu Hailemariam came to be." New York Times.
“I have found 50% of Ethiopia’s youth working as a chemist, and I found the house where Mengistu Hailemariam came to be.” New York Times.

*************
የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት የ 17 ዓመቱ ያሬድ እና የ27 ዓመቱ ዮናስ፣ ሥራቸው መኪና ማጠብ ነው፣ ታዲያ ሲያጥቡም ሆነ አጥበው ጨርሰው ሌላ መኪና እስኪመጣ ድረስ ጫት ከአፋቸው አይለይም። ሁለቱም ከአስር ዓመት በፊት ወደ አዲስ አበባ እንደመጡ ያናገራሉ። ሊመጡ የቻሉትም፣ በሚኖሩበት ክፍለሃገር የወላጆቻቸው መሬት ለአንድ ባለሃብት እንዲሰጥ ከተወሰነ በኋላ ወላጆቻቸው በመሞታቸው ነው።

ዮናስ ሲናገር. .ይላል ኒውዮርክ ታይምስ .. ዮናስ ሲናገር … “ባለፉት 10 ዓመታት እኔ ሰውነቴ ከማደጉ ውጪ ኑሮ ላይ ለውጥ ያለም፣ ያኔም አሁንም መኪና ነው የምናጥበው፣ ለኛ የሚሆን ሌላ ነገር የለም፣ ይህ አገር የተመቸው ለኢንቨስተር ብቻ ነው” ይላል።

የ 17 ዓመቱ ያሬድ ደግሞ የራሱ ታሪክ አለው “እኔ ጠንክሬ መስራት እፈልጋለሁ፣ ቢቻል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኜ ይህን አገር መለወጥ እፈልጋለሁ” ይላል፡ ክንዱ ላይ በ እንግሊዘኛ “ነቨር ጊቭ አፕ” የሚል ጽሁፍ ተነቅሷል።

ያሬድ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛን ቤቱ ጋበዘው ፣ ጋዜጠኛው እንዲህ ይላል .. “ቤቴ የሚለው፣ መኪና ከሚያጥበብት ቦታ ብዙ ያልራቀ፣ ከሁለት ሰው በላይ የማይዝ በካርቶን የተሰራ ዳስ ነው። ውስጡ በአንድ በኩል ጥቂት መጽሃፎች አሉ፣ ከላይ በኩል የክርስቶስ ምስል ተሰቅሏል። ያሬድ እንዲህ አለ “ተምሬ ዶክተር መሆን ዓላማዬ ነው፣ ከ20 ዓመት በኋላ ተመልሰህ ከመጣህ እዚህ ካርቶን ቤት ሳይሆን፣ ቢሮዬ በጸሃፊ ነው የምትገባው” አለኝ ሲል ጽሁፉን ይደመድማል።

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar