www.maledatimes.com ካህናትና ምእመናን በነቂስ በመውጣት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስንና የሰላም ልኡካኑን እንዲቀበሉ ቤተ ክርስቲያን ጥሪ አቀረበች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ካህናትና ምእመናን በነቂስ በመውጣት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስንና የሰላም ልኡካኑን እንዲቀበሉ ቤተ ክርስቲያን ጥሪ አቀረበች

By   /   July 29, 2018  /   Comments Off on ካህናትና ምእመናን በነቂስ በመውጣት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስንና የሰላም ልኡካኑን እንዲቀበሉ ቤተ ክርስቲያን ጥሪ አቀረበች

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 4 Second
FB_IMG_1532757965516

ካህናትና ምእመናን በነቂስ በመውጣት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስንና የሰላም ልኡካኑን እንዲቀበሉ ቤተ ክርስቲያን ጥሪ አቀረበች

FB_IMG_1532721784275

  • ረቡዕ ማለዳ 12:00፣ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ ቦሌ አየር ማረፊያ ይደርሳሉ፤
  • በቦሌ አየር ማረፊያና በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ደማቅ አቀባበል ይደረጋል፤
  • “የሁላችሁ በዓል ነው፤በቅዱስነታቸው እንድትባረኩ በነቂስ ውጡና ተቀበሉ፤”

†††

  • በሁለቱም የተላለፈው ቃለ ውግዘት እንዲፈታ የተወሰነው እየተፈጸመ ነው፤
  • ከአሜሪካ የተላለፈው፣በተገኙት አባቶች ውሳኔ ባለፈው ዓርብ ተነሥቷል፤
  • ከአ/አበባ የተላለፈውን ለማንሣት፣ ለነገ ሰኞ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቷል፤

†††

በአባቶች ዕርቀ ሰላም ፍጻሜ የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶሳዊ አንድነት በዋሽንግተን ዲሲ መበሠሩን ተከትሎ፣ የፊታችን ረቡዕ ማለዳ፣ ወደ ኢትዮጵያ ለሚመለሱት 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፥ ሊቃውንት፣ ካህናትና ምእመናን በነቂስ በመውጣት በድምቀት እንዲቀበሏቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ጥሪ አቀረበ፡፡

የአቀባበል ዐቢይ ኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ዛሬ እሑድ፣ ሐምሌ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ማምሻውን ለብዙኃን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ ለ26 ዓመታት የዘለቀው መለያየት በዕርቀ ሰላም ተቋጭቶ ቅዱስነታቸው አቡነ መርቆሬዎስና በውጭ ያሉት ብፁዓን አባቶች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው፣ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ታላቅ ደስታ፣ ታላቅ ልደት በመኾኑ፣ ካህናትና ምእመናን በነቂስ ወጥተው በድምቀት እንዲቀበሏቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

FB_IMG_1532465115929

የሰላም ልኡካኑና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጋራ

በፓትርያርክ ክብርና ደረጃ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስንና የሰላም ልኡካኑን ለመቀበል፣ በተለያየ ዘርፍ ኮሚቴ ተቋቁሞ ዝግጅቱ መጠናቀቁን የገለጹት ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ የአቀባበል ሥነ ሥርዐቱ፣በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያና ከዚያም በመቀጠል በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተለያዩ መርሐ ግብሮች እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም መሠረት፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስና የሰላም ልኡካን ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ ከሚደርሱበት የፊታችን ረቡዕ፣ ሐምሌ 25 ቀን ማለዳ 12:00 ጀምሮ፣በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ምእመናን በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ይደረጋል፤ በጋራ የምስጋና ጸሎት ይደርሳል፡፡

ከዚያም በመቀጠል፣ ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጉዞ ተደርጎ፣ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ስብሐተ እግዚአብሔር ቀርቦ ፍጹም የቤተ ክርስቲያናችን አንድነት መመለሱን የሚያበሥርና የሚያውጅ የደስታ መግለጫ መልእክት ከተላለፈ በኋላ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ኾኖ ቅዱስነታቸውና የሰላም ልኡካኑ በመንበረ ፓትርያርኩ ወደተዘጋጀላቸው ማረፊያ እንደሚያመሩ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡ ሥላሴ ካቴድራል ጉዞ ተደርጎ፣ በሊቃውንተ ቤተ ክ

His Grace Abune Diyoscoros

“ሊቃውንት፣ ካህናትና ዲያቆናት፥ለአቀባበሉ ዝግጅት እንድታደርጉና እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን፤” ያሉት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ “በዓላችሁ ስለኾነ ሁላችሁንም ይመለከታችኋል፤ የበረከቱ ተሳታፊ እንድትኾኑ፣ በቅዱስነታቸውም እንድትባረኩ ረቡዕ ከማለዳው 12:00 ጀምሮ እንድትወጡ እናስታውቃለን፤”በማለት የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በተያያዘ ዜና፣ ልኡካን አባቶች በደረሱበት የዕርቀ ሰላም ስምምነት መሠረት፣ የቤተ ክርስቲያንን መብት ባለማስጠበቅና ጊዜውን በመምሰል በአዲስ አበባም ይኹን በአሜሪካ በነበረው ሲኖዶስ ቀኖናዊ ጥሰት እንደተፈጸመ በመታመኑ በኹለቱም በኩል የተላለፈው ቃለ ውግዘት እንዲፈታ በተወሰነው መሠረት እየተፈጸመ መኾኑ ታውቋል፡፡

በአሜሪካ በስደት በነበረው ሲኖዶስ የተላለፈው ቃለ ውግዘት፣ ከትላንት በስቲያ ዓርብ፣ ሐምሌ 20 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በተገኙበት መነሣቱ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል፣ ነገ ሰኞ፣ ሐምሌ 23 ቀን በአዲስ አበባ በተጠራው አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ፣ በ1984 ዓ.ም.፣ በ1985 ዓ.ም. እና በ1999 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ የተላለፉት የውግዘት ውሳኔዎች እንደሚፈቱ ተጠቁሟል፡፡

ጥፋቱና የዓመታት ልዩነቱ የምእመናኑን ልብ በሐዘን የሰበረ በመኾኑ፣ ያለፉትንም ኾነ በሕይወት ያሉትን ልጆቿን በጋራ ይቅርታ ለመጠየቅልኡካኑ በጋራ ወስነዋል፡፡ ከሁለቱ ሲኖዶስ መዋሐድ በኋላ ቤተ ክርስቲያንን ከዳግም መከፋፈል ለመጠበቅና ሉዓላዊነቷን ለማስከበር፣ ሕጉንና ሥርዐቱን ያገናዘበ ደንብ በቅዱስ ሲኖዶሱ እንዲወጣ ልኡካኑ ተስማምተዋል፡፡

EOTC Holy Synod

ከዚህም በኋላ፣ ቤተ ክርስቲያን፣ ከአንድ ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ እየተቀበለች የምትመራ ሲኾን፣ ኹለቱንም ቅዱሳን ፓትርያርኮች በእኩል የአባትነት ክብር ትቀበላለች፡፡ አገልግሎቷን በምታከናውንባቸው የዓለም ክፍሎች ሁሉ፣ የሁለቱንም ስም በቅደም ተከተል ትጠራለች፡፡

ሁለቱም ቅዱሳን ፓትርያርኮች የሥራ ድርሻ እንደሚኖራቸው በስምምነቱ ተጠቅሷል፡፡ 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በጸሎትና በቡራኬ መንፈሳዊ አገልግሎት ይሰጣሉ፤ 6ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱ አቡነ ማትያስ ደግሞ፣ የአስተዳደሩን(የቢሮውን) ሥራእያከናወኑ አጠቃላይ አመራር ይሰጣሉ፡፡

ከልዩነቱ በፊት የተሾሙ ነባር ሊቃነ ጳጳሳት፣ ስማቸውና ክብራቸው ተጠብቆ በውጭ ሀገርም ኾነ በሀገር ቤት እንዲመደቡና እንዲያገለግሉ፤ ከልዩነቱ በኋላ የተሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት፣ ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት ደግሞ፣ ስማቸውን እንደያዙ ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲቀበላቸው፣ በውጭም ኾነ በሀገር ቤት አህጉረ ስብከት ተመድበው እንዲያገለግሉ ልኡካኑ ተስማምተዋል፡፡ የስም ተመሳስሎ ያላቸው አባቶች፣ እንደ ሢመት ቅደም ተከተላቸው ቀዳማይ፣ ካልዓይ፣ ሣልሳይ…ወዘተ በሚል እንዲለዩ ተወስኗል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on July 29, 2018
  • By:
  • Last Modified: July 29, 2018 @ 5:39 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar