www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ እንዲመለስና የጀግና አቀባበል እንደሚያደርጉለትም ገልፀዋል! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ እንዲመለስና የጀግና አቀባበል እንደሚያደርጉለትም ገልፀዋል!

By   /   August 14, 2018  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ እንዲመለስና የጀግና አቀባበል እንደሚያደርጉለትም ገልፀዋል!

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 15 Second

በሪዮ ኦሎምፒክ ሀገሩን ወክሎ ለማራቶን ሩጫ ውድድር ሄዶ በሩጫ መጨረሻ ክልል ከመድረሱ 100 ሜትር ርቀት ላይ እጁን በማጣመር ኢትዮጵያ በጭቆና ላይ መሆኗን ለአለም ያሳወቀው አትሌት ፈይሳ ሊሊሳ ወደ ሀገር እንዲመለስ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ወሰነ ።

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ጥሪ አቅርበውለታል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ መጋበዛቸውን ያስታወቁት።

በመግለጫቸውም በሪዮ ኦሎምፒክ እና በልዩ ልዩ የዓለም አትሌቲክስ መድረኮች በመሳተፍ የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አስተዋጽኦ ያበረከተው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ፍላጎታቸው መሆኑን
አስታውቀዋል።

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ከዚህ ቀደም ለሀገሩ ያደርግ የነበረውን አስተዋጽዎ እንዲቀጥል በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጥሪ አቅርበውለታል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተዘጋጁት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለአትሌት ፈይሳ የጀግና አቀባበል እንደሚያደርጉም ገልፀዋል፡፡

አትሌቱ በሪዮ ውድድር ላይ ባደረገው  ሰላማዊ የፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መሰረት ከሀገር ከወጣ በኃላ መመለስ እንደማይችል እና በስደት መኖር እንደሚፈልግ በመግለፁ በጠበቃ ሸክስፒር ፈይሳ ትልቅ ትግል ወደ አሜሪካ እንዲገባ መደረጉ ይታወሳል።

ጠበቃ ሸክስፒር ፈይሳ ወደ ሪዮ በማቅናት ጉዳዮን ባላሰለሰ ጥረት በመከታተል የአትሌቱን የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኝ አስችለዋል።

ባለፉት አመታት በህወሀት መንግስት ስር ይመራ የነበረው ይሄው ድርጅት አትሌት ፈይሳን በተለያዩ ጉዳዮች ሲከሰው እና ሲወቅሰው የነበረም ሲሆን በስነ ምግባር ብልሹነት በሚል ከአትሌቲክስ ውድድር እንዳይሳተፍ ማገዱም  ይታወቃል፣ ሆኖም አትሌቱም የዋዛ አልነበረም እና ከሚኖርበት የሰሜን አሜሪካ በግሉ መወዳደርን ከያዘው ቆየት ብሎአል ።

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ እንዲመለስና የጀግና አቀባበል እንደሚያደርጉለትም ገልፀዋል!

አትሌት ፈይሳ ሊሊሳ ከሀገሩ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ ባለቤቱን እና ልጆቹን ጠቅልሎ ወደ አሜሪካ የገባ ቢሆንም በሀገር ውስጥ የነበረው ንብረቱ ግን እስከአሁን በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንደአለ አይታወቅም።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar