www.maledatimes.com የበረራ አስተናጋጆቹ ሕገ ወጥ መድኃኒቶችን ይዘው ሊገቡ ሲሉ ተያዙ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የበረራ አስተናጋጆቹ ሕገ ወጥ መድኃኒቶችን ይዘው ሊገቡ ሲሉ ተያዙ

By   /   January 29, 2019  /   Comments Off on የበረራ አስተናጋጆቹ ሕገ ወጥ መድኃኒቶችን ይዘው ሊገቡ ሲሉ ተያዙ

    Print       Email
0 0
Read Time:32 Second

ለስንፈተ ወሲብ፣ ለጸጉር እድገት እና ለካንሰር ሕመም ይውላሉ የተባሉ ሕገ ወጥ መድኃኒቶችን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጆች በቦሌ ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ በኩል ይዘው ሊገቡ ሲሉ መያዛቸው ተሰማ።

አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ እንደሰማችው ሰራተኞቹ የአየር መንገዱ ቢሆኑም፤ ሕገ ወጥ ድርጊቱን በመፈጸም ተጠርጥረው የተያዙት ግለሰቦች ብዛት ግን ምን ያክል እንደሆነ በውል አልታወቀም።

የኢትዮጵያ የምግብ፣ መድኃኒት፣ ጤና ክብካቤ ቁጥጥርና አስተዳደር ባለሥልጣን እንደገለጽው፤ መድኃኒቶቹ ቪማክስ፣ ሲስቶን እና ሚኖክሲድል የሚባሉ ሲሆን በኢትዮጵያ ያልተመዘገቡና ጥራታቸው ያልተረጋገጠ ነው።

መድኃኒቶቹ ከሕገ ወጥ ወኪሎች በኩል የገቡ በመሆኑ የኅብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉ ነው ባለሥልጣኑ ያሳሰበው።
ተጠቃሚዎች በዚህ ረገድ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የመከረው ባለሥልጣኑ፣ ሕገ ወጥ ድርጊቱ በሕጋዊ መንገድ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን እየጎዳ ስለመሆኑም አስገንዝቧል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on January 29, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 29, 2019 @ 3:09 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar