www.maledatimes.com የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን የሕይወት ታሪክ በአሜሪካ ታተመ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን የሕይወት ታሪክ በአሜሪካ ታተመ

By   /   March 21, 2013  /   Comments Off on የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን የሕይወት ታሪክ በአሜሪካ ታተመ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 47 Second
 የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን የሕይወት ታሪክ በአሜሪካ ታተመ
የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን የሕይወት ታሪክ በአሜሪካ ታተመ
 በ

ጸጋዬ ገብረመድህንን ካጣናቸው ድፍን ሰባት ዓመታት አልፈዋል፡፡

የጸጋዬ ሴት ልጆች የአባታቸውን ሰባተኛ ሙት ለማሰብ ከሁለት ሳምንት በፊት አዲስ አበባ ነበሩ፡፡ ባለፈው ሳምንት ደግሞ ከሀገረ አሜሪካ ጸጋዬን የሚመለከት መልካም ዜና ተበስሯል፡፡

የዜናው ምንጭ ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸውን እና ኢትዮጵያን የሚመለከቱ መጽሐፍትን ሲያሳትም የቆየው “ፀሐይ ፐብሊሸርስ” ነው፡፡ ይኸው አሳታሚ ድርጅት የሎሬት ጸጋዬን የግል ማስታወሻ (Memoir) ሰሞኑን  ሎስ አንጀለስ በሚገኘው ሎይላ ሜሪማውንት ዩኒቨርስቲ በይፋ አስመርቋል፡፡

በገጣሚ፣ ደራሲና ተርጓሚ ፋሲል ይትባረክ የተዘጋጀው የግል ማስታወሻ ‹‹Soaring on Winged Verse: The Life of Ethiopian Poet – Playwright Tsegaye Gabre-Medhin›› የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተዘጋጅቷል፡፡

መጽሐፉ ሎሬት ጸጋዬ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ የተጀመረ ሲሆን፣ ከእርሳቸው ጋር በተደረጉ ጥልቅ እና ተከታታይ ቃለ ምልልሶች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ደራሲው ፋሲል ከባለቅኔው ህልፈት በኋላ በአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ያደረጋቸው ቀጣይ ጥናቶችም የመጽሐፉ አካል ናቸው፡፡ መጽሐፉ ከሎሬት ጸጋዬ የእረኝነት ጊዜ አንስቶ በጥበባዊ ስራዎቻቸው ዓለም አቀፍ እውቅና እስከተጎናጸፉበት ድረስ ያለውን አስገራሚ የሕይወት ጉዟቸውን ያስቃኛል፡፡ በ244 ገጾች የተዘጋጀው መጽሐፍ በ24.95 የአሜሪካን ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

የካቲት 18 ቀን 1998 ዓ.ም. ያረፉት ሎሬት ጸጋዬ፣ በጸሐፊ ተውኔትነት በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ከደረሷቸው ተውኔቶች ባሻገር የእንግሊዛዊው ደራሲ ዊልያም ሼክስፒር ተውኔቶች (ሐምሌት፣ ማክቤዝ፣ ኦቴሎ፣ ንጉሥ ሊር) የሞሊየር (ታሪቲዩፍ፣ የፌዝ ዶክተር) በመተርጐምም ይታወቃሉ፡፡

በአንድ ባለሙያ እንደተገለጸው፣ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊና ማኅበራዊ፣ ባህላዊም ገጽታዎች፣ የአፄ ኃይለሥላሴ፣ የደርግና የኢሕአዴግን ዘመን የሚያንፀባርቁ ሥራዎቻቸው ዘመኑን ከመግለጽ አኳያ ፋይዳ ያላቸው ናቸው፡፡ ብሂልን ከባህል በማዛመድ፣ የኢትዮጵያ አብዮት ሒደት የገለጹባቸው ተውኔቶች ከባህላዊ ትምህርት መጠርያዎች ነቅሰው ያወጡባቸው ናቸው፡፡ ‹‹ሀሁ በስድስት ወር›› (1966)፣ ‹‹አቡጊዳ ቀይሶ›› (1968)፣ ‹‹መልእክተ ወዛደር›› (1971)፣ ‹‹መቅድም›› (1972)፣ ‹‹ሀሁ ወይም ፐፑ›› (1985) ለመድረክ አብቅተዋል፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ በሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን የተደረሱ ‹‹ቴዎድሮስ››፣ ‹‹ምኒልክ››፣ ‹‹ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት›› እና ‹‹ዘርዓይ ደረስ በሮም አደባባይ›› የተሰኙ አራት ተውኔቶችን ‹‹ታሪካዊ ተውኔቶች›› በሚል ርእስ በቤተሰቡ ፈቃድ አሳትሞ በብሔራዊ ቴአትር ማስመረቁ ይታወሳል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar