www.maledatimes.com የቀደሙት የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤዎችና የተላለፉ ውሳኔዎች ሁነቶች ከሂደታቸው ጋር ምን ይመስላሉ የሚለውን ማለዳ ታይምስ ዳሶአቸዋል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የቀደሙት የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤዎችና የተላለፉ ውሳኔዎች ሁነቶች ከሂደታቸው ጋር ምን ይመስላሉ የሚለውን ማለዳ ታይምስ ዳሶአቸዋል

By   /   March 22, 2013  /   Comments Off on የቀደሙት የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤዎችና የተላለፉ ውሳኔዎች ሁነቶች ከሂደታቸው ጋር ምን ይመስላሉ የሚለውን ማለዳ ታይምስ ዳሶአቸዋል

    Print       Email
0 0
Read Time:23 Minute, 36 Second

1ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ

በትግራይ ክልል ቆላ ተምቤን የተካሄደው ይህ ጉባኤ ጥር 1983 ዓ.ም ላይ ነበር።

በዚህ ጉባኤ የደርግን ወታደራዊ ስርአት ውድቀት ለማፋጠን የትጥቅ ትግሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ውሳኔ ተላልፏል።

እንዲሁም የደርግ አምባገነናዊ ስርአት ከወደቀ በኋላ በመላው ሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ማምጣት የሚቻልባቸው አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።ወታደራዊ መንግስቱን ለመጣል የተዘረጉትን ስልቶች እንዴት ማጠናከር የሚለው በሰፊው የተነገረበት እንደነበር ያሳያል ።

2ኛ የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ

ታህሳስ ወር 1988 ዓ.ም በሃዋሳ ከተማ የተካሄደው ይህ ጉባኤ ኢህአዴግ ያዘጋጀው የመጀመሪያው የሰላም ፣ የልማትና የዲሞክራሲ እቅድ የፀደቀ ሲሆን ፥ ህገ መንግስታዊ ስርአትን ውጤታማ በሆነ መልኩ መተግበር የሚቻልባቸው አቅጣጫዎች ተቀምጠውበታል።ሆኖም ግን ህገ መንግስታዊ ስራቱን ወደ ቀጥተኛ አቅጣጫ ከመሄድ ይልቅ ከራስ የጥቅም አኳያ ጋር ያመዘነ እና ያዘነበለ እንደነበር ማንም የሚገልጸው ነው እስከዛሬ ድረስ ህወሃት ኢሃዴግ እየተከተለ ያለው ይሄው ህገመንግስታዊ ስራት የራሱን ድርጅት ህልውና ብቻ የሚጠብቅ እንደሆነ ይታወቃል   በዚህም ላይ ማለዳ ታይምስ ተጨመሪ ዘገባዎችን ይዞ ለመቅረብ ይሞክራል ።

 

 

3ኛውን የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ

በ1991 ዓ.ም ያስተናገደችው የጅማ ከተማ ናት ። በዚህ ጉባኤ በግንባሩ ድርጅታዊ ፕሮግራሞች ላይ ማሻያዎች ተደርገዋል።የአብዮታዊ ዲሞክራሲ እና የግንባሩን ትግል ልዩ ገጽታዎችን ለማስቀጠል ውሳኔ ተላልፎበታል።የዚህ ጉባኤ ለየት የሚያደርገው ከፍተኛ ወጭ የወጣበት ከመሆኑም በላይ የኢሃዴግ አስተዳደር ለትግራይ ልማት እና ለህወሃት አጋር ድርጅቶች ብቻ ሊውል የሚችል ከፍተኛ በጀት በመለገስ ልማታቸውን እና አካባቢያቸውን ሊስያስተናግዱበት የሚችል መርህ ቀጾ እንደነበር ይታወሳል ።በተለይም የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ እቃዎቹን በማሸሽ መስፍን ኢንጂነሪንግ የተሰኘውን ኩባንያ ካቋቋሙ በሁዋላ ሙሉ ወጭ እና በጀት እንዲሁም ሃይላቸውን ወደዚህ የሚያርፍበትን ስልት የቀየሩበት ወቅት እንደሆነ ማንም ሊረዳው ይገባል።አሁን መቀሌ ደረሰችበት ለተባለው ደረጃ ግንባር ቀደሙ ጨዋታ የተካሄደው እዚህ ጋር የተወሰነው ውሳኔ ከአንጻሩ ሊታይ የተተገበረበት ።

4ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ  በወርሃ ነሃሴ 1993 ዓ.ም አዲስ አበባ  ያስተናገደችው ይህ ጉባኤ የተሃድሶ ጉባኤ የሚል መሪ ቃል ይዞ ነበር። ጉባኤው የኢህአዴግ የአስር አመታት ጉዞን ገምግሟል።በዚህ ወቅት ደግሞ ወያኔ በዘር ከፋፍለህ ግዛ የሚለውን መሪ ቃሉን ካሰፈረበት ጊዜ ጀምሮ ለአስር አመታት ህብረተሰቡን በጭቆና ቀንበር ውስጥ ግዞተኛ ካደረገው በሁዋላ ከተኛሁበት እንቅልፌ ባነንኩ በማለት ከዘረም ከሃይማኖት የጸዳ መንግስትን ማፍራት አለበን ብሎ በአዲስ ምእራፍ ተመለስኩ ብሎ እራሱን ያዘጋጀበት ወቅት የነበረ ቢሆንም ከዚያ በባሰ ሁኔታ ቁጭ ብሎ በአዘቅት ውስጥ መውደቁን የሚያሳዩት የወቅቱ የሙስሊሞች ጥያቄ እና የክርስቲያኑ በሃይማኖቱ ጣልቃ ገብነት እና በገዳማቶቹ ላይ የሚደረጉት ሰበአዊም ሆነ ንብረታዊ ፖለቲካዊ የህግ ጥሰት ነው ።በተለይም ሙስናን ፣ ጠባብነትን ፣ ጎጠኝነትን ፣ የኢ-ዲሞክራሲያዊነትና የኪራይ ሰብሳቢነት አዝማሚያዎችን በፓርቲው አመራርና አባላት ዘንድ ለመዋጋት ያሳለፈው ውሳኔ ዋነኛው ነበር። በዚህ ጉባኤ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት መንስኤና በመንግስት የተሰጠው ውሳኔ ምላሽ ተገምግሞ ለቀጣይ ጊዜያት ትምህርት የሚሆኑ ተሞክሮዎች ታይተውበታል ተብሎ የሚፎከርበት እንጂ አንዳችም ነገር ለውጥ ያልታየበት መሆኑን ከመግለጽ ወደ ኋላ አንልም።

የመጀመሪያ የአምስት አመት የሰላም ፣ የልማትና የዲሞክራሲ ዕቅድ እንዲሁም በ2ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ የፓርቲው አፈጻጸም በጥልቀት ተገምግሟል ይላል ይህ ደግሞ ሁለተኛው ምርጫ ምንም ተወዳዳሪ በሌለበት የተወዳደረው ምርጫ መሆኑም አይዘነጋም ።

ይህ ጉባኤ 2ኛውን የሃገሪቱን የሰላም ፣ የልማት እና የዲሞክራሲ ዕቅድንም አጽድቋል።

5ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ

በ1997 የባህር ዳር ከተማ መስከረም ወር ላይ ጉባኤውን ስታስተናግድ ጉባኤ ዕመርታ የሚል መሪ ቃል ነበረው።በዚህ ጉባኤ ላይ የሰላም ፣ የልማትና ዲሞክራሲ ዕቅዶች ትግበራ በዝርዝር ተገምግሞ አቅጣጫዎች ተቀምጠውበታል።እንዲሁም ልማትና መልካም አስተዳደርን በተመለከተ ህዝቡን በሚጠቅም መልኩ ውጤት እንዲመዘገብ እንሰራለን የሚል ውሳኔ አሳልፎም ነው የተጠናቀቀው።በዚህ ወቅት የምርጫ ዘጠና ሰባት ዝግጅት ወቅት መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ የምንሊክ ጋዜጣ ሰፊውን ሽፋን በመስጠት አጠቃላይ የሪፖርት መዛግብቶችን ማስቀመጡን እያስታወስን በድርጅቱ ውስጥ ጠፉ እና ለሙ የተባሉትን ነገሮች በሙሉ በስፋት አቅርቦት ነበር አሁንም እኛ ይህንን ነገሮች ወደ ኋላ መለስ በማለት ዲሞክራሲን ለማስፈን በማለት ለየክልሎች የሰጡትን በጀት እና ይህ በጀት ከዲሞክራሲ ማስፈን ይልቅ ለምርጫ ቅስቀሳ ያደረጉበትን መንገድ ምን እንደነበር መመልከት ችለናል ።ይህም ማለት በየአጋጣሚዎቹ ኢሃዴግ ለሚፈልጋቸው ነገሮች በወቅቱ ተነስተው በሚገኙ ሃሳቦች ላይ በጀቶችን በማፍሰስ በጎንዮሽ በለሎእች ላይ እንደሚያውላቸው ያወቅንበት ወይንም የተረዳንበት አንዱ ዘዴ ሰለመሆኑ ነው ።

6ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ

6ኛውን የድርጅቱን ጉባኤ ያስተናገደችው የመቀሌ ከተማ በመስከረም ወር 1999 ዓ.ም አስተናግዳዋለች ።

በዚህ ጉባኤ በመልካም አስተዳደር ዘርፍና በምጣኔ ሃብት እድገት ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ውሳኔ ተላልፏል። የአመራር ብቃትን ከፍ ለማድረግ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ትኩረት እንዲሰጣቸውም ውሳኔ ተላልፎበታል። በገራችን ውስጥ ያሉትን ምጣኔ ሃብቶች ተጠቅመንባቸዋል ወይንም አልተጠቀምንባቸውም በማለት የሚንቀሳቀሰው ኢሃዴግ ትኩረቱ የሃገሪቱን ምጣኔ ሃብት የማሳደግ ዘዴ ላይ ያደረገው ትኩረት በተወሰነ መልኩ ሊያስመሰግነው ቢገባም ከአስፓልት መንገድ ዝርገታ እና ከባለሃብቶች ህንጻ ግንባታ ያለፈ ነገር ምንም እንደሌለው የሚታወቅ ነው ይህ ደግሞ ዛሬም ድረስ ነገም የሚወቀስበት ትልኩ እኩይ ባህሪው እንደሆነ ይታወቃል ለምን ቢባል ድርጅቶቹንም ሆነ ንብረቶቹን በትግራይ ህዝብ እና በህወሃት አጋር ድርጅቶች ስም የከፈታቸውን እና ያደራጃቸውን ኩባንያዎች የሃገር ሃብት ናቸው ተብሎ ለሃገሪቱ የሚገባው አጠቃላይ የገንዘብ ኢኮኖሚ ምንም እንደሌለ እና የትግራይ ህዝብም ሆነ የተቀረው ህዝብ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ብሎ ቁጭ እንዳለ የተረዳው አልመሰለኝም ። እድገት ማለት አእምሮ መለወጥ የመጀመሪያው ሲሆን የወያኔ ኢሃዴግ አስተዳደር ሰዎች ግን እዚያው ጫካ እንዳሉ እንደነበሩበት አብረዋቸው የጫካን ህይወት እንደተጋፉአቸው ጉሬላዎች አስተሳሰባቸው ወደታች የወረደ ከመሆኑም በላይ ነጻነት የሚለው ነገር እና የሰው ልጅ እኩልነት የሚለውን አስተሳሰብ ከእደገት ጋር ሊፈርጁት እንደማይችሉ የሚታወቅ ሃቅ ነው ።

7ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ

ይህ ጉባኤ በመስከረም ወር 2001 ዓ.ም በሃዋሳ ከተማ የተካሄደ ነው። ኢትዮጵያን የሚያሸጋግሩ መልካም ተሞክሮዎችን ማስፋት የሚል መሪ ቃል ይዞ ነው ጉባኤው የተካሄደው። በዚህ መሪ ቃል ግን አሁን የተካሄደውም ውሳኔም ሆነ ለውጥ ምንም ማሻሻያ ያልተደረገበት እና በዘርፉ ሂደትም ላይ ተሞክሮውን ያላዩበት በድንጋይ ላይ ዉሃ ማፍሰስ ብለው ገንዘባቸውን ብቻ በማባከን የታለፈበት ወቅት ነው ።

በዚህ ጉባኤ በከተሞችን ዕድገት ፣ በመሰረተ ልማት ፣ በቴክኖሎጂ ዕድገት እና በማይክሮ ኢኮኖሚ ልማት ላይ በማተኮር ሰፊ ግምገማ አድርጎ ውሳኔዎችን አሳልፏል የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ እድገት ከአፍሪካ አገሮች ኋላ ቀር ከመሆኗም የተነሳ በአሁን ሰአት ለክፋት የተሞሉ ነገሮች ላይ ግንባር ቀደም በመሆን ከፍተኛ መእዋለ ንዋይ በማጥፋት ኔትወርኮችን ለማጥፋት የሚጥሩበት ቴክኖሎጂዎች ላይ ደርሰዋል ።በዚህም ሁኔታ ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ኔትወር ተጠቃሚ ከሚሉአቸው የአለም አገሮች ተርታ  የመጨረሻውን ደረጃ በመያዝ ስትጠቀስ የመረጃ ኔትወርኮችን በመዝጋት ደግሞ ከኤርትራ ቀጥላ በአራተኝነት ደረጃ ላይ ትይዛለች  በአፍሪካ ሁለተኛዋ አገር ሆናም ተመዝግባለች ።ይህንን እድገት ብለው የሚደሰኩሩልን መንግስቶቻችን ዛሬ የደረስንበት የቴክኖሎጂ እድገት እመርታን አሳይተናል በማለት ላልተማረው ህዝባችን ውሸትን ይመግቡታል በድህነት ይጨፈልቁታል በረሃብ ይገድሉታል ። የኑሮ ውድነቱን እያሻቀበ በሄደበት በዚህ ወቅት ከነሱ ውጭ ሰው የለም የተባለበት አስመስለው ህዝቡን ከፋፍለህ ግዛ በሚለው አጀንዳቸው አሁንም እያሰቃዩት ይገኛሉ ።ይህ ነው የእነሱ የቴክኖሎጂ እድገት ።

8ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ

2003 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ በአዳማ ከተማ የተካሄደው 8ኛው ጉባኤ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ የኢትዮጵያ ህዳሴ በማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ይደርሳል በሚል መሪ ቃል  ነበር የተከናወነው።

ይህ ጉባኤ የቀደሙት አመታት የግንባሩን ስራዎች በመገምገም በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመኑ ሃገሪቱ ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ውሳኔዎች ተላልፈውበታል በማለት ገልጸውልናል መቼም አዳዲስ ቃል መፍጠር የማይሰለቸው ወያኔ ካለፉት 2 አስርተ አመታት ጀምሮ እስካሁን ተኝቶ ዛሬ ነቃሁ ለልማት ተዘጋጀሁ እያለ በአባይ ግድብ እና በትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ ትኩረቱን ያዞረው ወያኔ የመውደቁን አዝማሚያ በተመለከተበት ወቅት ምን አድርጌ ህብረተሰቡን ከጎኔ ልያዝ እንዴት አድርጌ ነፍሴን ላድን በሚል እሳቤ ይህንን ያረጀ እና ያፈጀ የቀዳማዊ ንጉስ ሃይለስላሴን እቅድ በማንሳት ዛሬ ልክ እራሱ ፈጥሮ እራሱ አድራጊ በመምሰል ሁሉንም እኔ አድርጌዋለሁ በማለት የመሬት ቁፋሮውን ተያይዞታል ያዝልቅለት የምንል ሲሆን እድገቱን የማንጠላው ቢሆንም እንዲህ አይነቱ እድገት ግን የፖለቲካ መሰረታዊ መጠቀሚያ ባይሆን መልካም ነው እንላለን ።ሌላው የደሃውን ህዝብ ደመወዝ ከመቁረጥ እና የህዝቡን ጉሮሮ ከመዝጋት ይልቅ ለሃገር እድገት የምታስቡ ከሆነ የትምኒት ድርጅቶች እና የኢፈርት ድርጅቶች ካካበቱት ሃብት ላይ ገሚሱን በማዋል ግንባታው ቢጠናቀቅ እና ከዚያም በሁዋላ ህብረተሰቡ የልማቱ ተጠቃሚ ሲሆን ከአገልግሎቱ ከሚገኘው ክፍያ በታክስም ይሁን በአገልግሎት ክፍያ የሚቆረጥበት አካሂያድ ቢፈጸም መልካም እመርታን ያመጣል ከማለት ያለፈ ሃሳብ ለማስፈር አንችልም።

9ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ

መቸም ጉድ የፈላበት አንድ ሰው አለ ያለ እሱ ሁሉም ነገር ምንም የማይመስላቸው እሱን ልክ እንደ ቅዱስ ገብርኤል አምልኮአዊ ውዳሴአቸው አጽሙ በሲኦል ትሁን በገነት ባረፈችበት እንዳታርፍ አድርገው እያሰቃዩት ስለሚገኘው የትላንትናው መለስ የዛሬው ሙት ስም ሳይነሳ አሁንም አልቀረም ምን ብለው ሊያወድሱት እንደሚችሉ እና ሌላ ፈጣሪ ቃላቶችን እስኪሰታቸው እኛም ልመናችንን እናበዛላቸዋለን  በጉባኤው ” በመለስ አስተምህሮዎች ጠንካራ ድርጅትና የልማት ሃይሎች ንቅናቄ ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል ከቅዳሜ ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ ነው የሚካሄደው።

ጉባኤው በአራት ቀናት ቆይታው ያለፉት ሁለት ዓመታት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸምና ቀጣይ እቅዶች ላይ ይወያያል፣ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።የዚህን አጠቃላይ ይዘት ምን ይመስላል የሚለውን ደግሞ በቀጣይ ርእሳችን ይዘን እንቀርባለን ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 22, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 22, 2013 @ 9:43 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar