www.maledatimes.com የትግራይ ጠላት ……!በአብርሃ ደስታ መቀሌ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የትግራይ ጠላት ……!በአብርሃ ደስታ መቀሌ

By   /   March 22, 2013  /   Comments Off on የትግራይ ጠላት ……!በአብርሃ ደስታ መቀሌ

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 58 Second

! ….. የትግራይ ጠላት ……!

የኢህኣዴግ መንግስትን የተቃወመ ሰው ወይ የፖለቲካ ድርጅት የትግራይ ህዝብ ጠላት እንደሆነ ኣድርገው በማቅረብ የትግራይን ህዝብ ለማጭበርበር የሚሞክሩ የመንግስት ኣካላት እንዳሉ ይታወቃል።

ግን ህወሓትን መጥላት የትግራይ ህዝብን መጥላት ኣያሰኝም። ህወሓትን መቃወም የትግራይ ህዝብን መቃወም ማለት ኣይደለም። ምክንያቶች

(1) ህወሓት (ገዢው መደብ)ና የትግራይ ህዝብ (ተገዢው ህዝብ) አንድ አይደሉም፤ ሊሆኑም ኣይችሉም። ፓርቲና ህዝብ አንድ ተደርጎ የሚወሰደው ለፕሮፓጋንዳ (የህዝብ ግንኙነት) ሥራ ነው። ህዝብና ፓርቲ ሊመቻቹ ይችላሉ።

(2) ተቃዋሚን በጠላትነት ማየት የፖለቲካዊ ኣስተሳሰብ ችግር ውጤት ነው። መቃወም ተፎካካሪ (ኣማራጭ ሃይል) መሆን እንጂ ጠላት ኣይደለም። ዴሞክራሲ ኣሰፍናለሁ የሚል መንግስት ተቃዋሚዎችን በጠላትነት መፈረጅ ተገቢ ኣይደለም።

(3) ሰዎች ወይ ድርጅቶች ህወሓትን (እንደገዢ ፓርቲ) የመቃወም ተፈጥሮኣዊ መብት ኣላቸው። የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ከፈለገ (በፍላጎቱ) ይምረጠውና ትግራይን ያስተዳድር (መብቱ ነው)። ህወሓት ላልመረጠው ህዝብ ኣሻንጉሊቶችን በመፈብረክ ሌሎች ህዝቦችን በእጃዙር የመግዛት መብት የለውም። የኢትዮዽያ ህዝቦች የራሳቸውን ተወካዮች በነፃነት የመምረጥ ሙሉ መብት ኣላቸው።

ለምሳሌ፦ ህወሓት ለኣማራ ህዝብ ብኣዴን እንዲሁም ለኦሮሞዎች ኦህዴድ መርጦ ገዢዎች ሰጥቶዋቸዋል። ህወሓት ለነዚህ ህዝቦች መሪዎች የመምረጥ መብት ማን ሰጠው? ራሳቸው እንዲመጡ ለምን ኣይፈቀድላቸውም? ስለዚ ህወሓትን የመቃወም በቂ ምክንያት ኣላቸው። ይህን ሁኔታ በመቃወማቸው የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ሊያሰኛቸው ኣይችልም።

(4) ህወሓት ለትግራይ ህዝብ የቆመ ድርጅት ከሆነ ለምን እንድንደራጅ ኣይፈቅድልንም? መደራጀትኮ ሃይል ይፈጥራል። ለምንድነው ተደራጅተን ሃይል እንዳንፈጥር የሚያደርገን? ከዚህ በላይ ጠላትነት ኣለ እንዴ? ስለዚ የትግራይ ህዝብ ጠላት ህወሓት ነው ማለት እችላለሁ። በትግራይ ህዝብ ስም መንግስት ሲጠቀም እንጂ የትግራይ ህዝብን ሲጠቅም የታየበት አንድም ቀዳዳ አልተፈጠረም እንዲያውም ይባስ ብሎ የትግራይ ህዝብ ለችግር ተዳርጎ ከሚያርሰው መሬት እና ከቀየው ተሰዶ ወደ መሃል ከተማ በመግባት ለችግር ተዳርጎ ልመናን እንደ ባህሉ አድርጎት በጎዳናዎች ላይ እንዲበዙ አድርጎታል ይህ ደግሞ ለትግራይ ህዝብ እና አገር ትልቅ ውድቀት መሆኑን የሚያሳይ ነው ። እንዲህ ከሆነ ነገሩ የትግራይ ህዝብን ጫንቃው ላይ የቆመበትን መንግስት የመቃወም መብቱ ሊከበርለት አይገባም ትላላችሁን ?እኔ እንደትግራዋይነቴ ሳስበው ሁላችንም የተፈጥሮ ነጻነታችን ሊገፈፍ አይገባም በማለት የራሴንም ነጻነትም ሆነ ተወልጄ ያደኩባትን ምድር እንዲሁም በአንድነት አንድ ህዝብ ተብለን አብረን ያደግንባቸውን ቀያት አድባራት ታቦታት እና መጂዶችን በህብረት ሆነን አንድ የምናደርግባት እና የምናጸናበት መንገድ መፍጠር የሚኖርብን አለም መሆን ይገባዋል ብዬ አምናለሁ ።ሆኖም መንግስት እኛን ከፓርቲው ጋር አያይዞ አቅርቦን እንደሚታረድ በግ ለመሰዋእት ካቀረበን ዘመን አምላክ አልፎታል በዘር ከለያየን በሃሳብ ከበታተነን ቆይተናል ግን መሆን የማይገባው እና የማይሆነው ነገር በ እኛ ውስጥ ተፈጥሮ ሆኖአል ለህወሃትም ስኬት ሰምሮለታል::በነገራችን ላይ የትግራይ ልማት ማህበርም ሆነ ኢፈርት ያላቸውን ካፒታል ከትግራይ ህዝብ ጋር ሲነጻጸርም ሆነ ሲወዳደር የትየለሌ መሆኑን ሳታውቁት የምትቀሩ አይመስለኝም ታዲያ እኛ ከዚያ ጥቅም ተጋራን ማለት ነውን? የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ አሁንም የምንጠይቅህ ነገር ቢኖር የትግራይ ህዝብ ማለት ህወሃት አይደለም ህወሃት ማለት ጥቂት የትግራይ ልጆች ጥርቅም ሲሆን በትግራይ ህዝብ ስም የሚነግዱ ነጋዴዎች ናቸው ።ስለዚህ እባካችሁ አንድነታችንን አንጣው ።

(5) የትግራይ ህዝብ (ባይሳካም) አንድ ኣስተሳሰብ እንዲኖረው ጥረት ማድረግ ትውልድን መግደል ነው። ብዙ ሰዎች አንድ ዓይነት ኣስተሳሰብ እንዲይዙ ለማድረግ የብዙዎቹ ኣስተሳሰብ መግደል ግድ ይላል። ኣስተሳሰብ ታፈነ፣ ተገደለ ማለት ደግሞ ትውልድን ተገደለ ማለት ነው። ምክንያቱም የለውጥ ምንጭ ኣስተሳሰብ ነው።

(6) ደሞ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት አገዛዝ ነፃ መውጣት ኣይፈልግም ያለ ማነው? በትግራይ ሁሉም ቢሮዎች (ከላይ እስከ ታች) በተወሰኑ ሰዎችና ቤተሰቦቻቸው ቁጥጥር ስር ነው። ማነው ትግራይ የነሱ ብቻ ናት ያለው? ትግራይኮ የሁላችን ናት? ወይስ የነሱ ባሮች (Slaves) ሁነን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል?

ማንም ሰው የመደገፍም የመቃወምም ተፈጥሮኣዊ መብት ኣለው። የህወሓት የግል ስጦታ ኣይደለም። ህወሓት ሲፈልግ የሚሰጠን ሲፈልግ ደግሞ የሚከለክለን የግል ሃብቱ መሆን የለበትም እላለሁኝ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 22, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 22, 2013 @ 11:54 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar