www.maledatimes.com (ከደብረሰላም ቦርድ አባላት አንዱ ህዝብ እንዲያውቀው የተላከ መልዕክት) ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክን ወያኔ ጉያ ሊወስዱልህ ጁን 2 ቀጠሮ ያዙልህ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

(ከደብረሰላም ቦርድ አባላት አንዱ ህዝብ እንዲያውቀው የተላከ መልዕክት) ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክን ወያኔ ጉያ ሊወስዱልህ ጁን 2 ቀጠሮ ያዙልህ

By   /   May 2, 2013  /   Comments Off on (ከደብረሰላም ቦርድ አባላት አንዱ ህዝብ እንዲያውቀው የተላከ መልዕክት) ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክን ወያኔ ጉያ ሊወስዱልህ ጁን 2 ቀጠሮ ያዙልህ

    Print       Email
0 0
Read Time:22 Minute, 45 Second
አባ ሃለሚካኤል (የደብረሰላም መድሃኔዓለም አስተዳዳሪ)
አባ ሃለሚካኤል
(የደብረሰላም መድሃኔዓለም አስተዳዳሪ)
ሊቀትጉሃን ጌታሁን (ከአስተዳዳሪው የተሻለ ሃሳብ የማቀርበው እኔ ነኝ የሚል መከራከሪያ ቢያቀርቡም ከቦርድ ስብሰባ የታገዱ)

ሊቀትጉሃን ጌታሁን
(ከአስተዳዳሪው የተሻለ ሃሳብ የማቀርበው እኔ ነኝ የሚል መከራከሪያ ቢያቀርቡም ከቦርድ ስብሰባ የታገዱ)
"አቶ መለስ ንሰሃ ገብተው ነው የሞቱት" በሚል በድፍረት ያስተማሩት ቀሲስ አሃዱ

“አቶ መለስ ንሰሃ ገብተው ነው የሞቱት” በሚል በድፍረት ያስተማሩት ቀሲስ አሃዱ
ቀሲስ ስንታየሁ

ቀሲስ ስንታየሁ
በገለልተኛነት ለረዥም ዓመታት ከቆዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ.ክ አንዱ ነው። ይህ ቤ/ክ በተለይ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን በሥሩ የያዘ መሆኑን ትናንት በደብረሰላም አገልግለው ዛሬ በወያኔው የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ስር “ዋልድባን ጆሮ ዳባ ልበስ” በሚል ለሕሊናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው እየሰሩ ባሉት አቡነ ዳንኤል አማካኝነት የኢትዮጵያ መንግስት ጠንቅቆ ያውቀዋል። ታዲያ ይህን የምርጥ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ቤተክርስቲያንን በእጁ በማስገባት እነዚህን ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን ለመበታተን የወያኔ መንግስት በአንዳንድ ገጣሚያን ነን ባይ የቤተክርስቲያኑ አስተናጋጆች በአራቱ ካህናት አማካኝነት እጁን በማስገባት ይህችን ውድ ቤ/ክ ለመበታተን ለጁን 2 ቀን 2013 ቀጠሮ ይዟል።
የቤተክርስቲያንን ሥራ በአግባቡ ሳይወጡ በታክሲ ሾፌርነት ሥራ ላይ የተሰማሩት 3ቱ ካህናት በየቤቱ እየዞሩ አንዴ “ደመወዝ ካልተጨመረን ይህን ደብረሰላምን እንበትናለን” እያሉ ሲፎክሩ፤ በሌላ በኩል የዋልድባን ገዳም መፍረስ በመቃወም ኑ ሰልፍ ውጡ ሲባሉ “ሃገር ቤት መግባት እንፈልጋለን እና አንቃወምም፤ ሃገር ቤት የገዛነው ቤት እንዲወሰድብን ስለማንፈልግ አንገኝም” በሚል፤ ሲቀጥሉም “ደብረሰላምን በአዲስ አበባው ሲኖዶስ ስር ስናስገባ የትም አንሄድም” በሚል ምዕምናኑን እያስፈራሩ ካሉት ከነዚህ ካህናት መካከል አንዱ ቀሲስ አሃዱ ከአንድ አባት በማይጠበቅ ሁኔታ በውሽት አቶ መለስ ዜናዊ ንሠሃ ገብተው ነው የሞቱት በሚል በደብሩ በመስበክ ከየትኛው ወገን እንደቆሙ ራሳቸውን አጋልጠዋል። ከትናንት በስቲያ እሁድም በሚኒሶታው የኢትዮጵያ ድምጽ ራድዮ በርከት ያሉ የሚኒሶታ ም ዕምናን “የሚኒሶታውን ደብረሰላም መድሃኔዓለም ወደ ወያኔ መዳፍ ከመውደቁ እናድን” የሚል አይነት አስተያየት በቀጥታ ስርጭት አስተያየት መስጠቱ ድንገት በውስጣቸው ያለውን የፈነቀለባቸው ቀሲስ ስንታየሁም ወደ ራድዮ ጣቢያው በመደውል የወያኔ መንግስት በሃገር ቤት የከለከለውን ሃሰብን በነፃነት የመግለጽ መብት እዚህ ሰሜን አሜሪካ ውስጥ መረጋገጡ ጠፍቷቸው ይሆን አይሆን በማይታወቅ መልኩ በስሜታዊነት “እናንተ ስለቤተክርስቲያን ጉዳይ ለማወያየት ስልጣን የላችሁም” በማለት የሃገር ቤት ወያኔዎች ለ20 ዓመታት ሲነግሩን የነበረውን በመድገም የት እንዳሉ አሳይተውናል።
በሁለት መንታ መንገድ ላይ የሚገኘው የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ

በሁለት መንታ መንገድ ላይ የሚገኘው የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ
ሌላው እዚህ አሜሪካ በኢንጂነርነት ሙያ ተመርቆ ሥራ በማጣቱና ሃገር ቤት በመግባት በዚያ ሥራ ለመሰማራት የቋመጠውና ቃልም የተገባለት ግለሰብ በየለቅሶ ቤቱ ም ዕምናኑን ከሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ጋር እንዲቀላቀል ሲሰብክና ምርጫ ሲያለማምድ በብዙሃኑ ትችት ቢደርስበትም ማን እንደሆነና ምን እንደሚፈልግ ከወዲሁ ታውቆበታል።
ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መነገሪያ እንጂ የግጥም ማንበቢያ እንዳልሆነች እየታወቀ በቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መልዓከ ሰላም አባ ሃይለሚካኤል “ይህ ሰው ግጥም እንዳያነብ ክልክዬ አልነበር እንዴ” ተብሎ በምዕመናን ፊት እስከ መታገድ ደርሶ አሁንም በድፍረት ግጥም እያነበበ በበርካታ ም እመናን የተተፋው ግለሰብ ሃገር ቤት ሄዶ መጽሐፍ ለማሳተም ሲኖዶሱን ሲጠይቅ “አንተ ገለልተኛውን ቤ/ክ እያገለገልክ ነውና በቤ/ክ ስር ያንተን መጽሐፍ አናትምም፤ በነፃ እንዲታተምልህ ከፈለህ አጀንዳችንን አሳካ” ተብሎ የተላከው እናንተ የምታውቁት ግለሰብም ደብረሰላምን ወደ ወያኔ መንደር ለመውሰድ ቀን ከለሊት እየሰራ ነው።
እንደቦርድ አባልነቴ ከቦርድ ሊቀመንበሩ አቶ ጥበቡ የተሰጠውን “እኛ የቦርድ አባላት ከየትኛውም ወገን ሳንወግን የሕዝቡን ድምጽ መስማት አለብን” በሚል የተሰጠውን ውሳኔ አከብራለሁ። የተከበረችውን ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክንን ወደ ሃገ ቤቱ ሲኖዶስ ለመውሰድ ሲሯሯጡ የነበሩ የቦርድ አባላትን ዝም አስብሏል። ሆኖም ግን ግጥም አንባቢውና ኢንጂነሩ አንዳንድ ተከታዮቻቸውን በመያዝ (73 ይሆናሉ) ጁን 2 ቀን 2013 ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ እንዲወሰድ ለማስወሰን ስብሰባ ጠርጠዋል። የሚገርመው እነዚህ 73 የሚሆኑት አባላትን ስም ዝርዝራቸውን ለህንጻ ማሰሪያ ከተሰበሰበው ገንዘብ ሰጪዎች ዝርዝር ላይ ሳየው የአንዳቸውም ስም የለም። አላማቸው ደብረሰላም ትልቅ ካቴድራል እንዲገነባ ሳይሆን እንዳለ ሆኖ ለወያኔ አሳልፎ መስጠት ነው። ልብ በሉ እነዚህ ከሃገር ቤቱ ሲኖዶስና ከመንግስት ጥቅማጥቅም እናገኛለን ብለው እየሰሩ የሚገኙ ግለሰቦች በጁን 2ቱ ስብሰባ ለምርጫ ለማቅረብ የፈለጉት ደብረሰላም በኢትዮጵያው ሲኖዶስ ይመራ ወይስ በገለልተኛነት ይቆይ? በሚለው እንጂ እንደ 3ኛ አማራጭ በስደተኛው ሲኖዶስ ስር ይጠቃለል የሚል ነገር አልቀረቡም፤ ይህ ምርጫ ቢቀርብ የሚወሰነውን ያውቃሉና ። ምናልባት ይህን የኔን ግልጽ መል ዕክት ካነበቡ በኋላ ብዙዎች ሶስተኛውን አማራጭ ይዘው እንደሚነሱ እተማመናለሁ።
በሌላ በኩል ለደብረ ሰላም አዲስ ሕንጻ ለማሰራት በትጋት እየሰራ የሚገኘው ቡድን ይህ የምርጫ ጊዜ ይራዘም እያለ እየተከራከረ ነው። የዚህ ቡድን ፍራቻ ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ይኬድ ከተባለ ገንዘብ የሚሰጥ አይኖርም። የሕንጻው ሕልምም ያከትማል። ጁን 2 ደብረሰላምን የወያኔ ቅጥረኞቹ ግሩፖች ከወሰዱት ደብረሰላም በ እርግጠኝነት ለ2 ይከፈላል። ከወዲሁም የወረቀት ብተናው፤ በኢሜይል የሚደረገው ቅስቀሳ ተጠናቅሮ ቀጥሏል።
በነገራችን ላይ “በደንቡ መሰረት በቦርድ ስብሰባ ላይ ከካህናቱ አንድ ሰው ነው መወከል ያለበት ቢባልም 2 ካህን ሲወከል ቆይቷል። አሁን ግን ይህ ቀርቶ በአስተዳዳሪው ብቻ ካህናቱ እንዲወከሉ በመደረጉ የተከፉትና እኔ ከአስተዳዳሪው መልዓከ ሰላም አባ ሃይለሚካኤል የተሻለ ሃሳብ የማቀርብ ሰው ነኝ። እኔ ከቦርድ ስብሰባው መታገድ የለብኝም በማለት ሲከራከሩ የነበሩት መልዓከ ሃይል ቀሲስ ጌታሁን መኮንን (መሪጌታ)” በቦርድ ስብሰባ ላይ እንዳይገኙ ታግደዋል። ይህ ለምዕመናኑ ትልቅ ዜና ነው።
የኒሶታ ምዕምናን ሆይ ደብረሰላም መድሃኔዓለምን በወያኔ ልትቀማ ጁን 2 ቀጥሮ ተይዞልሃል። ንቃ!
ለግንዛቤ ለቦርዱ ተልከው ከነበሩ ደብዳቤዎች መካከል የሚከተለውን ላካፍላችሁ፦
ሰላመ እግዜብሔር ለመድሃኔ ዓለም ቦርድ አባላት ይድረስ
ተጠሪ፡ አቶ ጥበቡ ታምራት
የካቲት 10 2005 ዓ.ም. የግል ስሜ ተጥቅሶ ለነ አቶ ታየ ረታ በማለት የጻፋችሁልኝ ደብዳቤ ደርሶኝ ተመልክቼዋለሁ። እናንተንም እግዜር ያክብርልኝ።
ሁለትም ሦስትም ሆነን በቃል ማስረዳቱ ለሌሎቹ ፈራሚዎች ተወካይ አያደርገንም። እያንዳንዱ ፈራሚ በግሉ አምኖበት ያደረገው ነውና። ሆኖም ከጠየቃችሁኝ ዋና ዋና ነጥቦቼን እንደሚከተለው እገልጣለሁ።
——————————————————————————————————
የካቲት 12 2005 ዓ. ም
ይድረስ ለደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ያስተዳደር ቦርድ አባላት
ሚኔያፖሊስ፡ ሚኔሶታ 55406
ተጠቃሽ፡ አቶ ጥበቡ ታምራት ሊቀ መንበር
የካቲት 5, 2005 ከአስተዳደር ቦርዱ ለነአቶ ታየ ረታ ተብሎ የተጻፈ ደብዳቤ ደርሶኝ ተመልክቼዋለሁ። ጉዳዩም በደብራችን ስላለው የአስተዳደር ይዘትና ስነ-ሥርዓት ጉድለት 73 ተቃዋሚ ተብዬዎች በኢሜይል ሳይሆን ፈርመን በወረቀት ጽፈን ላቀረብነው መልስ ሲሆን ለኔ ብቻ መጻፉ ስህተት ነው እላለሁ። ማንም ማንን ስለማይወክልና አንድ ግለ ሰብ ተጠሪ ስለሌለ፤ ሁላችንም መጠራት አለብን።የውስጠ ደንቡን ለመከተል በመጀመራችሁ እሰይ በርቱልን እላለሁ።
ለማናቸውም በደብዳቤው የላካችሁልኝ አስተሳሰብም ሆነ የሂሳብ ስሌት በጣም የተሳሳተ መሆኑ እንዲታወቅ አሳስባለሁ። ከ73 ፈራሚ
ላይ 24 ሲቀነስ 49 እንጂ 45 አይሆንም። 24ቱ ለአባልነት አልበቁም ከተባለ 525 አባላት የሉንም ማለት ነው። 24ቱ እነማን እንደሆኑ
ዝርዝሩን ለማስተካከል ስማቸው ቢገለጽልን እናመሰግናለን።
ለተጻፈልኝ ደብዳቤ ከዚህ በታች ባሰፈርኳቸው ዘጠኝ ነጥቦች መልስ እሰጣለሁ። የውስጥ ደንቡን በማገናዘብ ተመልከቱልኝ።
1. በተጠቀሰው የመተዳደሪያ የውስ ደንብ ክፍል 3 (ለ) ሃያው ፐርሴንት ባያሟላም በጉዳዩ አሳሳቢነት ምክንያት በክፍል ሦስት (ሀ) ጠቅላላ ስብሰባ መጥራት ይቻላል። እኔ ራሴን ብቻ ስለምወክል ደብዳቤው ለያንዳንዱ ፈራሚ መላክ ይኖርበታል።
2. በውስጠ ደንቡ መሰረት ሲገመገም የአባሎች ቁጥር 525 ይደርሳል ብትሉም ከግማሽ የማይበልጥ ነው እላለሁ።
3. በደምቡ መሰረት በቦርዱ ስብሰባ ላይ ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ ተሣታፊዎች የቤተ ክርስቲያን ከፋይ አባል የሆኑና በሕዝብ የተመረጡ መሆን ሲገባቸው አስመስለው በሕገ-ወጥነት የሚሳተፉት ባስቸኳይ ሊወገዱ ይገባል።
4. ካሁን ቀደም በኦዲተር ተጠንተው ጠቅላላ ጉባኤው ያጸደቃቸው ያሠራር ደንቦች በሥራ ላይ እንዲውሉ ለማስገንዘብ፤
5. ማናቸውም ቤተ ክርስትያኑን ለማገልገል የሚቋቋም ኮሚቴ አባላቱ በጠቅላላው ጉባኤ እንዲጸድቅና ምእመናን ባሉበት ቃለ ምህላ እንዲቀበሉ ማስፈለጉ ለማንም ግልጽ ስለሆነ፤ ይኸው እንዲፈፀም።
6. እኛ የደብረ ሰላም መ/ዓ ምዕመናን ገለልተኝነትን ባፀደቅንበት ጊዜ በኢትዮጵያ የነበረው ያቡነ ጳውሎስ አመራር ብልሹና ዘረኛ በመሆኑ ነበር። ከዚያም አመራረጡ ሥርዓት ሲይዝ ወደእናት ቤተ ክርስቲያን እንደምንመለስ ታውቆ ነው። ተዋህዶነታችንን ለመለወጥ ያሰብንበት ጊዜ የለም። አንዳንድ ሰዎች በጎን መጠቀሚያ ለማድረግ ቢሞክሩም ቤቱ አልተቀበለውም። የፓትርያርክ ምርጫ ገና ቁርጡ ሳይለይለት ‘ሳይከካ ተቦካ’ እንዲሉ፤ በአዲስ አበባ ጉዳዩ ሳይስተካከልና ጠቅላላው ጉባኤአችን ሳይፈቅድ ‘አንድነት’ እያሉ የሚሯሯጡት ለምን እንደሆነ አልተረዳነውም። በዴሞክራሲ አገር እየኖርን የመደብ አምባገነንነት ከየት መጣ? የሕዝብን መብት መድፈር ወይም የተሳሳተ መልዕክት መስጠት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያይላልና። የምንተዳደረው በሚኔሶታ ሕግ መሆኑን መረዳት ያስፈልገናል።
7. አሁንም በድጋሜ የማስገነዝበው የጻፋችሁልኝን በመጥቀስ “ለካህናት የተደረጉት የደመወዝ ጭማሪዎች፤ የካህናት አቀጣጠር፤የቤት አበል ክፍያዎች” በብልሹ አመራር፤ ስድብና ዛቻ ተጨምሮ ባለ ጉዳዮቹ አፍጥጠው ባስገደዱበት ግምት ባጣ አሠራር የሆነው መታረም አለበት።
8. ሥጋ ወደሙ ሲፈተት ስለ ክፉ ነገር፤ ስለጥፋት፤ መዓትና ቅጣት ዐውደ ምሕረት ቆመው ክፉ ከሚለፍፉ መንፈሳዊ ትምህርት ላይ ቢያተኩሩ በበጀን !!! በተመሳሳይ የእግዚአብሔርን ስም አንስተው በቀደሱበት አንደበታቸው፤ ዐውደ ምሕረት ላይ ቆመው ከቅዳሴ በኋላ የሚያሰሙት አሽሙር ሽሙጥና ስድብ አባሎችን እያራቀብን ሆኗልና ጥንቃቄ!! ጥንቃቄ!!
የሁነታው አሳሳቢነት ሁዳዴ ገብቷል ሳይባል ጠቅላላ ጉባኤ የሚያስጠራ ነውና አደራ ጭምር እጠይቃለሁ።
9. ቅጥር ካህናት ግዳጃቸውን ለማሟላት ቅዳሜ በየሣምንቱ ፕሮግራም ይዘው የቤተ/ክ ሕፃናትና ወጣት ልጆችን እንዲያስተምሩ ግዴታ ማስገባት ያሻል።
የዚህ ደብዳቤ አዘጋጅና አቅራቢ፡ ታዬ ረታ
ለማውቃቸው አባሎችም በግልባጭ አስታውቃለሁ።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on May 2, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 2, 2013 @ 11:19 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar