www.maledatimes.com ተስፋዬ ገብረአብ ማን ነው ? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ተስፋዬ ገብረአብ ማን ነው ?

By   /   May 28, 2013  /   Comments Off on ተስፋዬ ገብረአብ ማን ነው ?

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 36 Second

ተስፋየ ገብረዕባብ ማነው ?? ለሚለው ባጭሩ የሚያምታታ የሻቢያ ትግሬ ነው

ተስፋየ ገብረዕባብ ማነው ?? ለሚለው ባጭሩ እኔ ኤርትራዊ ብሆንም በኢትዮጵያዊነቴ ነው የማምነው እያለ የሚያምታታ የሻቢያ ትግሬ ነው [ ኤርትራውያኖች ራሳቸውን ትግርኛ ነን ብለው የጠራሉ ]።
ኤርትራ ነጻነቷን [ባርነት ??] መርጣ ዛሬ በችግር ማቅ ውስጥ ስላለች ሀገር አንድ ዜጋ ለምን መጻፍ አስፈለገኝ ?? ነገሩ እንዲህ ነው ይህ ሰው ኤርትራዊም ቢሆን ዛሬ የሚይዙት የሚጨብጡት ያጡ የሃገራችን ፖለቲከኞች [ግራ ዘመም ?? ]እንደ አማካሪ አድርገው ይዘውት በኤርትራ በኩል ታጥቃችሑ ነጻ ትወጣላችሑ የሚል አሉቧልታ ሲደሰኩርላቸው የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ይሉ ዘንድ “ይህን ሃሳብ ተስፋየ ገብረዕባብ አመጣልን” እያሉ እምቧ ዘራፍ የሚሉ አልጠፉም ። በሌላ በኩል ደግሞ ተስፋየ እንዲህ አለ እየተባለ ሜድያ ተሰቶት ዛሬ በየድረገጹ ሲጨበጨብለት እናያል ።
ግን ይሄ ሰው የሚጨበጨብለት ነው ወይ ?? እስኪ ከጻፋቸው ጽሁፎች አንድ አንድ ነገር እንይ ….
ተስፋየ የቡርቃ ዝምት ብሎ በኦሮምኛ በጻፈው መጽሃፍ እንዲህ ይለናል

“ቡርቃ ሲገኣ የሮን ጌሴ ጂራ ቡርቃ፤
ዋቀዮ መራንፍራ ዲኒ ኬኛ አርባ ጉጉ ጂራ፤
አማሪ ቡርቃ ጂራ ቆንጨራ ካስኔ ጪራ”።

ይህ ከላይ ያሰፈርኩት የተስፋዬ ገብረአብ ጽሁፍ ወደ አማርኛ ሲተረጎም የሚከተልውን መልእክት ያስተላልፋል።

“ጊዜው ደርሶአል ቡርቃ በቃህ
ጠላታችን አርባ ጉጉ ላይ ነው ያለው
አማራ ቡርቃ ነው ያለው
ቆንጮራ አንስተን እንቆራርጠዋለን”።

የቡርቃ ዝምታ ማለት ምን ማለት ነው ?? ብሎ አንድ ሰው ይጠይቅ ይሆናል ተስፋየ እንዲህ ይለናል “ምንሊክ አርሲን ሲወርና የገዳውን ስርዐት ሲያጠፋው ግን የቡርቃ ወንዞች በኦሮሞወች ተንበርካኪነት አዝኖና አፍሮ መሬታችሑን በጃችሑ ካላገባችሑ እኔንም አታዩኝም ብሎ አካላቱን ሁሉ እንደዘንዶ ስቦ ከመሬት ቀበረ” ይለናል እንግዲህ ቡርቃ የሚባለው ወንዝ አኩርፎ አልታያችሑም አላቸው ነው የሚለን ።
በመሰረቱ ተስፋየ ይሄን ነገር ሰርቢያወች ህዝባቸውን በኮሶቮ ላይ አነሳስተው ለዛ ሁሉ እልቂት ከዳረጋቸው የተኮረጀ ሲሆን ልዩነቱ ተስፋየ ሰርቢያወች አበቦች አኮረፉ የሚለዉን ወንዝ አኮረፈ ማለቱ ብቻ ነው ። በዚህ ጉዳይ ላይ ዶክተር አሰፋ ነጋሽ የስነልቦና ሙህር ከሙያቸው አኳያ የሰጡትን ገለጻ እዚህ ሊንክ ላይ ያዳምጡ [Dr. Assefa Negash Part 7 Of 17 on Youtube ።http://www.youtube.com/watch?v=SlBFP5qjRKc

በምን አይነት መለኪያ ነው በምን አይነት ፖለቲካ ነው ይህን ሰውየ በጭፍን አትጥላው የምባለው ። እኔ ተዉት ሰው መሆንን !! እንደ አንድ አማራ ይሄን ሰው ልውደደው ብል አልችልም ።
ይህን ሰው “ሌሎች የጻፋቸው መጽሃፎች ላይ ስለ ወያኔ ጽፎልናል ለዛም ነው የምንደግፈው ” ይሉናል ከወያኔ ያልተናነሰ ያማራ ጥላቻ ያላቸው ግለሰቦች ። ወያኔን ተስፋየ ሳይሆን የሚያሳውቀኝ ወያኔ በገባ ሁለት አመት እስከሚሆነው ድረስ ምን ምን አደረገ የሚሉትን ነገሮች ልብ ብየ ካየሁ የበቂየ ነው ። ልብ ላለው ሰው ጉዳዩ ያገባኛል ላለ ሰው የተስፋየ ልብ ወለድ መጽሃፍ ሳይሆን ወያኔ በተግባር ያሳየን ስለወያኔ ምንነት ይነግረናል ። ባማርኛ በጻፈው መጽሃፉ ላይ እንዲህ ይለናል …
“መሬታችን ጥቁር ቅቤ ነው ። ምንሊክ የሚባለው ስግብግብ ሲያየው ጎመዠ እኛን ማክበር አቃተው ። እንደፈረስ ልጋልባችሑ አለን አሻፈረን አልነው በመሳርያ ብቃት ተማምኖ ጨፈጨፈን ። የሴቶችንም ጡት ጥሬ ስጋ እንደሚበላ ሰው እየተስገበገቡ ቆረጡት የሰቶቻችን ጡት እኛ ከበግ ላይ ጸጉር እንደምንሸልተው እንዲያ ነበር የሚቆርጡት እነኝህ ሰወች በግ ሲያርዱ በስመዐብ ብለው ይጀምራሉ የሴቶችን ጡት ሲቆርጡ ግን በስመ አብ አይሉም ግን ሃይማኖት አለን ይላሉ … “።

ይህን መጽሃፍ ዶክተር ነጋሱ ጊዳዳና ሎሬት ጸጋየ ገብረመድህን ያወገዙት ሲሆን ሎሬት ጸጋየ እንዲህ ብለዋል “ይህ መጽሃፍና ጽሃፊው ከኢትዮጵያ መወገድ አለባቸው” ነበር ያሉት ።

ጀግኖች ኢትዮጵያ ነጻ ስትወጣ ተስፋየን ኢትዮጵያ ውስጥ ባገኘነው ይላሉ ። ወራዳ ከንቱወች ደግሞ ኧረ እሱ ቢጠላን ጥላቻ መልስ አይሆንም ይላሉ ።
ከጀግኖቹ ወይም ከወራዶቹ ጎራ ለመሆን የዕያንዳንዱ ሰው ምርጫ ነው ።
በተስፋየ ገብረዕባብ የሚመሩ ከንቱወች [ ሃሳብ የሚወስዱ ] ኢትዮጵያን ነጻ ከማውታታቸው በፊት ለራሳቸው ነጻ ይውጡ ።
አመሰግናለሁ ።ለተጨማሪ መረጃ ይህንን ብሎግ ይዳብሱ http://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/05/28/231-7/

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on May 28, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 28, 2013 @ 10:30 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar