www.maledatimes.com ዲያስፖራው ጽንፈኛ ነው “ሚሚ ስብሃቱ “ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዲያስፖራው ጽንፈኛ ነው “ሚሚ ስብሃቱ “

By   /   July 28, 2012  /   Comments Off on ዲያስፖራው ጽንፈኛ ነው “ሚሚ ስብሃቱ “

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 53 Second

በዛሚ ማስታወቂያ እየተዘጋጀ የሚቀርበው የጋዜጠኞች ክብ ጠረጰዛ የተሰኘው የሬዲዮ ፕሮግራም ጋዜጠኞችን እና የአውሮፓ እና በአሜሪካ እንዲሁም በአረብ አገራት የሚገኙትን ትውልደ ኢትዮጵያውያኖችን ህልውና በሚነካ መልኩ የስድብ እና የዘለፋ ፕሮግራም አቀረበ ። በተለይም በአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ እና በነጻው ፕሬስ ላይ ከፍተኛ የሆነ የስድብ ውርጅብኝ እንዳወረደችበት ከአቀረበችው የፕሮግራም ስርጭት ለመረዳት ችለናል ። እርሷን ተከትለው ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበር አባል የነበረ እና በጥቅም ጉዳይ የማህበሩን ማህተም እና ሌሎች ዶክመንቶችን ከነጻ ጋዜጠኞች ማህበር በመስረቅ የግል ጥቅሞችን በማስተካከል እና በመስራት ጥቁር ስም ያለው ወንደሰን መኮንን  መይሳው የሚል ጋዜጣ ያሳትም የነበረ ሲሆን በአንባቢ ማጣት ከአንድ ወር ያልዘለለ እትም á‹­á‹ž መውጣት ሳይችል ቀርቶ የጋዜጠኞች ማህበር ከመንግስት ጋር በነበረው የመብቴ ይጠበቅልኝ ጉዳይን ተከትሎ መንግስት የጣለበትን እገዳ ምክንያት በማድረግ ፣ከመንግስት ጋር በመመሳጠር ተገንጣይ የነጻ ጋዜጠኞች ማህበርን አቋቋምኩ በማለት ከኢሃዴግ መንግስት ባለስልጣን  ማለትም ከአቶ በረከት ስምኦን በ1997 አመ ምህረት መጨረሻ አካባቢ  የገንዘብ ልገሳ ከተደረገለት በሁዋላ ለረጂም ዘመን የቆየውን ኢነጋማ እንዲፈርስ ጥረት ያደረገው ጋዜጠኛ መሆኑ በነጻው ፕሬስ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ስሙ በስነ ምግባረ ብልሹነት ወይንም  በመልካም የለሽ የሚጠቀስ ነው ።ይህም ግለሰብ ከአንድ ጋዜጠኛ የማይጠበቅ አነጋገር ከመናገሩም በላይ ስለ ሚዲያ ነጻነት እና የመረጃ ፍሰት ምንነትን መረዳት ያልቻሉ መሆናቸውን ከሚናገሩት ያልበሰለ እና በእውቀትም ይሁን በትምህርት ያልዳበረ ሙያዊ ተሰጦ እንዳላቸው  የሚያሳይ ንግግር መናገራቸውን ከአንደበታቸው የሚጠቁም  በመሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙት ማንኛውም የሚዲያ ሽፋን ሰጪ ጋዜጠኞች መረጃን በነጻነት እና  በእኩልነት ማስተላለፍ መማር እንዲችሉ ማለዳ ታይምስ ሲመክር ለዚህም ደግሞ የማንኛውም ፓርቲ ተቃዋሚ እና ደጋፊ ሆኖ መረጃን ከማቅረብ ይልቅ ወገንተናዊነት ባልተላበሰ መልኩ የመረጃ ፍሰትን ልህብረተሰባቸው በነጻነት ማስተላለፍ የሚችሉበትን መንገድ መፍጠር የሚገባቸው ሰዎች መሆን አለባቸው ሲል አመክሮ ይገልጻል። ለዚህም ይላል የማለዳ ታይምስ የመረጃ ማእከል  ከመንግስት ሊደርስባቸው የሚችለውን ጫና ተቋቁሞ ለህዝብ እውነተኛ ነገርን ማቅረብ ይህም ሆኖ ሳለ  በተመሳሳይ ሁኔታ ለወደፊት የጠንካራ የሚዲያ ተቋምን ሲፈጥር በህብረተሰብ ዘንድ ከበሬታን እና ተአማኒነትን ሊያገኝ የሚችል ተቋም መፍጠር ይችላሉ በማለት አስተያየቱን ሰጥቶአል ። አያይዞም አቶ ወንደዘን መኮንን ሚሚ ስብሃቱ  መሰረት አታላይ እና አንድ ደንበኛቸው  ዲያስፖራውን ሲሳደቡ የቆዩ ሲሆን በተለይም “ጥርሳቸው ገጦ ጥፍራቸው ወጥቶ “በማለት አንድ ሚዲያ ፐርሰናሊቲ ካለው ጋዜጠኛ የማይጠበቅ ስድብ በማውረድ ስትሳደብ የነበረችው ሚሚ ስብሃቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ገና በመነሳት ላይ  ያለውን የኢቶጵያን የሚዲያ እድገት በእጭጩ ለመግደል የተነሳች እና ስነ ምግባር የጎደላት መሆኑን ይገልጻል። በሌላም በኩል ጎጃም ውስጥ በነፍስ ግድያ ወንጀል የሚፈለገው መሰረት አታላይ በተመሳሳይ ሁኔታ የወያኔ ልሳን በመሆን እና በሰሜን አሜሪካ ያሉትን ጋዜጠኞች ሲሳደብ መሰማቱ ህብረተሰብን ሳያስገርም እንዳልቀረ ተገልጾአል ። በኢትዮጵያ ውስጥ የመገናና ብዙሃን አፈና በበዛበት በዚህ ሰአት ህብረተሰቡ ምንም እንዳያውቅ እና እንዳይረዳ በማድረግ ከፍተኛ ጥረት የሚያደርገው የወያኔ መንግስት ለአቀንቃኞቹ ብቻ ሚዲያውን በመፍቀድ እንደፈለጋቸው እንዲጨፍሩበት  ማድረጉ ከትዝብት እና ከተጠያቂነት እንደማያድነው ህብረተሰቦች ይጠቁማሉ ።የዛሚ ማስታወቂያ ድርጅት የሚያስተላለፈውን ሬድዮ ለመስማት እዚህ ይጫኑ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 28, 2012
  • By:
  • Last Modified: July 29, 2012 @ 5:43 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar