www.maledatimes.com የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ህክምና ክፍል እና የሆስፒታሉ አስተዳደር ለ7 አመታት በመብራት ችግር ላይ አልፏል ፣ብዙሃኖችንም ለሞት ዳርጓል ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ህክምና ክፍል እና የሆስፒታሉ አስተዳደር ለ7 አመታት በመብራት ችግር ላይ አልፏል ፣ብዙሃኖችንም ለሞት ዳርጓል !

By   /   October 23, 2013  /   Comments Off on የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ህክምና ክፍል እና የሆስፒታሉ አስተዳደር ለ7 አመታት በመብራት ችግር ላይ አልፏል ፣ብዙሃኖችንም ለሞት ዳርጓል !

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 51 Second

tk

ህወሃት አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላ ከፍተውት ዛሬ በደጋፊዎቻችው ከፍተኛ ተደማጭነትን ያገኘው ሬዲዮ ፋና በቀትር የዜና እወጃው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከትናንት 10 ሠዓት ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ የሆስፒታሉ ታክሚዎች በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የገለጸ ሲሆን ፡፡ ሬዲዮው የሆስፒታሉ ናፍጣ  ጄኔሬተርም አገልግሎት እንደማይሰጥ አክሎ በመግለፅ የችግሩን አሳሳቢነት ደርጃ ላይ መድረሱን ገልጾአል ፡፡

በሆስፒታሉ ውስጥ በቀዶ ጥገና ህይወታቸው መትረፍ የሚችል፣ በሰው ሠራሽ መንገድ የሚተነፍሱ ሰዎችና በማሞቂያ ክፍል ውስጥ ያሉ ህፃናት ህይወት ጉዳይ ነው ምንም ሊሰራ ባለመቻሉ የብዙሃኑ ህይወት ሊቀጠፍ ችሏል ፡፡ በመብራት መቋረጥ ምክንያት ለሚጠፋው ውድ የሰው ህይወት ተጠያቂው ማነው ? ለሚለው ምላሽ ግን ምንም ሊገኝለት አልተቻለም በአፍሪካ በህክምና እጦት እና እንዲሁም በአቅም ማነስ አለበለዚያም በችሎታ መጓደል በሺዎች የሚቆጠሩ ህይወት በቀን ይጠፋል ከዚህም መካከል ኢትዮጵያ ግንባር ቀደሙን ስፍራ ትይዛለች ? ይህንንስ ሃላፊነት ማስን ይወስዳል ፣የሆስፒታሉ አስተዳደር? የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክና መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን? ወይስ ይህ መስሪያ ቤት በሥሩ ያለ ክላስተር ክላስተር አስተባባሪ ሚኒስቴር?

ከዚህ ጋር በተያያዘ ደግሞ አንዳንድ ገልለልተኛ ግለሰቦች በዚህ ሰባት አመታት ብዙ መዳን የሚችሉ የሆስፒታሉ ህመምተኞች በቂ አገልግሎት ባለማግኘት እና የተሟላ የመደሃኒት አቀርቦት ባለመሰጠቱ ምክንያት ማለፋቸውን አያይዘው ገልጸዋል ።ይህንን ጉዳይ ግን የሆስፒታሉ አስተዳደሮች ከማመን ይልቅ ችላ ብለው ማለፋቸውንም ጠቁመዋል ።የዚህ የሆስፒታሉ አስተዳደርም ሆነ ሌሎች የመንግስት አካላት ቅድሚያ ለህመምተኞች ወገኖቻቸው ባለመስጠት በህይወት ማጥፋት ሊጠየቁ ይገባል ሲሉ የህክምና ባለሙያዎቹም ቢሆኑ ተመርቀው ስራቸውን በተገቢው ሁኔታ  መስራት ካልቻሉ የህክምና ፈቃዳቸው ሊነጠቅ ይገባል ሲሉ ጠቁመዋል ።የዚህን ዜና ዘገባ ሃተታ ሙሉውን ከራዲዮ ፋና የቀረበው እንዲህ ይነበባል ።

የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በኤሌትሪክ መቋረጥ ለ7 ሰዓታት ስራ አቁሞ ነበር !

በባሃሩ ይድነቃቸው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 13፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ለሰባት ሰዓታት መብራት ባለመኖሩ ሆስፒታሉ ተገቢ አገልግሎት መስጠት አቋርጦ ነበር።

የኤሌክትሪክ ሀይሉ በመቋረጡ የቀዶ ጥገናና ጽኑ ህሙማን ታካሚዎች፣ ጠቅላላ ቀዶ ጥገና እና ድንገተኛ ቀዶ ጥገና ህክምና የሚሰጥባቸው ክፍሎች እንዲሁም ያለ ጊዜያቸው የተወለዱና ሙቀት የሚፈልጉ ህጻናት ሙቀት የሚያገኙባቸው ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ስራ አቁመው ነበር።

ዛሬ ማለዳ ላይ ዘጋቢያችን በሆስፒታሉ ባደረገው ቅኝት ወቅት የኤሌትሪክ ሃይል በመቋረጡ የተነሳ ሃኪሞቹ ለታካሚዎቹ ኦክስጂን በእጃቸው እየጨመቁ ሲሰጡ አስተውሏል።

የህክምና ባለሙያዎቹ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ በእጃቸው ለነዚህ ከሞት አፋፍ ለደረሱና በተፈጥሮ መተንፈስ ላልቻሉ ህሙማን ዓየር በእጃቸው ሲሰጡ ቆይተዋል።

ያነጋገርናቸው ተረኛ የህክምና ባለሙያዎች እንደገለፁልን ለቀዶ ጥገና ዛሬ ተቀጥረው የነበሩና ያለ ምግብ የቆዩ ህሙማን አገልግሎቱን ማግኘት ስለማይችሉ ለሌላ ጊዜ ቀጠሯቸው እንዲዛወር ተደርጓል።

ይህም ሆስፒታሉ ላይ የስራ መደራረብ ፈጥሮበታል ነው ያሉን ።

ሆስፒታሉ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቀበለው ከሁለት ምንጮች ነው።

ነገር ግን የሀይል ማስተላለፊያው ላይ በደረሰ ችግር ምክንያት ኃይል እንዳጣ ተገልጿል።

በማንኛውም ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በሆነ ምክንያት ሊቋረጥ እንደሚችል ቢታወቅም፥ የሆስፒታሉ መጠባበቂያ ጄኔሬተር በማርጀቱ የተነሳ እንደ ሌለ የሚቆጠር ነው ይላሉ የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ማህሌት ይገረሙ ።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አሁን ሆስፒታሉ ያለውን ጄኔሬተር ለማደሰ በሂደት ላይ እንደሆነ ተናግረዋል።

ዶክተር ማህሌት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ሶስተኛ የኃይል ምንጭ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

ዛሬ ምናልባትም ለ7 ሰዓታት የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል ሌላ ጊዜ ለብዙ ሰዓታት ቢቋረጥ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አይታወቅም።

ይህ እንዳይሆን ግን ሆስፒታሉ ያሉትን አነስተኛ ጄኔሬተሮች ወሳኝ ለሆኑት ክፍሎች የመትከል እቅድ እንዳለውና ከዚህ ባለፈም አዲስ ጄኔሬተር ለመግዛት በሂደት ላይ እንደሚገኝ ተገልፆልናል ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on October 23, 2013
  • By:
  • Last Modified: October 23, 2013 @ 9:42 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar