www.maledatimes.com አስር ፓርቲዎች ‘‘ትዴኢ’’ የሚባል ቅንጅት ፈጠሩ *አንድነትና መድረክ የቅንጅቱ አባል አይደሉም - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አስር ፓርቲዎች ‘‘ትዴኢ’’ የሚባል ቅንጅት ፈጠሩ *አንድነትና መድረክ የቅንጅቱ አባል አይደሉም

By   /   October 23, 2013  /   Comments Off on አስር ፓርቲዎች ‘‘ትዴኢ’’ የሚባል ቅንጅት ፈጠሩ *አንድነትና መድረክ የቅንጅቱ አባል አይደሉም

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 22 Second
 
በዘሪሁን ሙሉጌታ
ከአንድ አመት በፊት በአዳማ ከተማ ከ2005ቱ የአካባቢና የከተማ አስተዳደር ምርጫ በፊት ውይይት ይቅደም በማለት ፒቲሽን ተፈራርመው የነበሩት 33ቱ ፓርቲዎች አስር በመሆን ‘‘ትብብር ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ’’ (ትዴኢ) የሚባል አዲስ ቅንጅት ፈጠሩ።
አዲስ በተመሰረተው ቅንጅት ውስጥ ዋና ዋናዎቹ አንድነትና መድረክ እንዲሁም ሰማያዊ ፓርቲዎች አባል አልሆኑም።
ባለፈው እሁድ ጥቅምት 10 ቀን 2005 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት በተካሄደ ስብሰባ አዲሱን ቅንጅት ለመፍጠር አስሮቹ ፓርቲዎች ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ከቅንጅቱ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ቅንጅቱን ለመመስረት የሚያስችሉ የጋራ መግባቢያ ሰነድ፣ መተዳደሪያ ደንብና ፕሮግራም ተቀርፆ የጋራ ስምምነት ላይ መደረሱን ገልፀዋል። በቀጣይ ቀናትም ቅንጅቱን መመስረቱን ለማብሰር የሚያስችል ልዩ ፕሮግራም እንደሚዘጋጅም አስታውቀዋል።
ቀደም ሲል በጎሳ ወይም በቡድን ከተደራጁ ፓርቲዎች ጋር እንደማይሰራ ገልፆ የነበረው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅር (መኢአድ) ከቅንጅቱ መስራቾች አንዱ መሆኑ ታውቋል። የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ስለጉዳዩ ተጠይቀው ፓርቲው ቀደም ሲል የያዘውን አቋሙን አለመለወጡን ገልፀው፣ አሁን ቅንጅት የፈጠሩት ፓርቲዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመዋሐድ ዝግጁ በመሆናቸው መኢአድ ቅንጅቱ ውስጥ መግባቱን አስታውቀዋል።
‘‘ከመድረክ ጋር መኢአድ ያለው ልዩነት በቡድን መደራጀት ባለፈ መሠረታዊ በሆኑ የሕዝብ ጥያቄዎች ላይ ጥርት ያለ አቋም ባለመያዙና ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ እስካልተገኘ ድረስ አባል አንሆንም’’ ማለቱን ያስታወሱት አቶ ተስፋዬ አሁንም መኢአድ በቡድን ከተደራጁ ፓርቲዎች ጋር የተቀናጀው ሁሉም ፓርቲዎች በኢትዮጵያ አንድነት ጥላ ስር ተዋህደው ለመታገል ያመኑበትና የተስማሙበት በመሆኑና ጊዜው የፓርቲዎችን ህልውና የማስጠበቅ ጉዳይ በመሆኑ ነው ብለዋል።
ከምርጫ 97 በፊት ባሉ ጊዜያትም በተመሳሳይ ‘‘ትዴኢ’’ የተባለ ቅንጅት ሲመሰረት መኢአድ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስና ዶ/ር መረራ ጉዲና ከሚመሯቸው ፓርቲዎች ጋር ቅንጅት ፈጥሮ እንደነበርና በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ህብረት (ኢድኃህ) ውስጥ መኢአድ እንደነበር በማስታወስ መኢአድ ከጎሳ ፓርቲዎች ጋር መቀናጀቱ አዲስ ነገር አለመሆኑን አብራርተዋል። ከመድረክ ጋር ያለው ልዩነት በጎሳ ከመደራጀት ባለፈ የፕሮግራም ልዩነት በመኖሩ እንደሆነም አቶ ተስፋዬ አያይዘው ገልፀዋል።
አሁን በተመሰረተው ‘‘ቅንጅት’’ አንድነትና መድረክ ያልተሳተፉት በመድረክ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ከውህደት ባለፈ በቅንጅት ላይ ቅንጅት መፍጠር ስለማይፈቅድ ሲሆን ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የመዋሐድም ሆነ ግንባር የመፍጠርና የመቀናጀት ፍላጐት የሌለው መሆኑን አስቀድሞ በማሳወቁና ከጥቂት ሳምንታት በፊትም ከ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ እንዲወጣ በመደረጉ ጭምር ነው።)።n

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on October 23, 2013
  • By:
  • Last Modified: October 23, 2013 @ 9:53 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar