www.maledatimes.com 2017 - MALEDA TIMES - Page 24
Loading...
You are here:  Home  >  2017  -  Page 24
Latest

መንግስት የገቢ ግብር እምቢታ አመፅን ለመግታት ዝግ ስብስባ ተቀምጧል – ዋዜማ ራዲዮ

By   /  July 26, 2017  /  Ethiopia  /  Comments Off on መንግስት የገቢ ግብር እምቢታ አመፅን ለመግታት ዝግ ስብስባ ተቀምጧል – ዋዜማ ራዲዮ

ከኦሮሚያ የጨለንቆ ነጋዴዎች ተነስቶ ጊንጪ፣ አምቦና ወሊሶን ያዳረሰውየግብር በዛብን ስሞታ መልኩን እየቀየረ ባለፉት ሦስት ቀናት ወደ አዲስ አበባ ኮልፌ፣ታይዋንና አጠና ተራ ተዛምቶ ቆይቷል፡፡ ኾኖም የግብር እምቢታ አመጹ በዚህ ፍጥነትታላቁን የገበያ ስፍራ መርካቶን ያዳርሳል ብሎ የገመተ አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡ለብዙ ነጋዴዎች ያልጠበቁት ክስተቱ ኾኖ መገረምን የፈጠረው ይህ አመጽ ለመንግሥትሹማምንትም ዱብ እዳ ሆኖባቸዋል፡፡ ከትናንት ጀምሮ ግምገማ የተቀመጡ የአስሩ ክፍለ ከተማ የድርጅት ኃላፊዎች አመጹንማን አስተባበረው በሚለው ጥያቄ ላይ ከረር ያለ ግምገማ ያካሄዱ ሲሆንአዝማሚያዎችን ዐይቶ ማስቆም ሲቻል ይህ አለመደረጉ ትልቅ የመንግሥት ድክመትሆኖ ተነስቷል፡፡ ትናንት ከቀትር ጀምሮ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮና የኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች በአንድነት በማዘጋጃ ቤት የካቢኔ አዳራሽ፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የድርጅትጽሕፈት ቤት አስተባባሪዎች ራስ ኃይሉ ሜዳ በሚገኘው ቢሯቸው እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በስብሰባ ተሰንገው ማምሸታቸውን የዋዜማ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ የማዘጋጃ ቤቱን ስብሰባ ከተካፈሉ ምንጮች ዋዜማ እንደሰማቸው አመጹ ገፍቶ ከቀጠለ ቁርጥ ግብሩን የመክፈያ ጊዜ በተራዘመ ዓመታት እንዲሆን ከማድረግ ጀምሮሙሉ በሙሉ እስከማንሳት የሚሄድ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ከኃላፊዎች ፍንጭ መሰጠቱን ነው፡፡ ኾኖም እንዲህ ዓይነቱ ውሳኔ መንግሥት ሁኔታዎችንመቆጣጠር እየተሳነውና እየተዳከመ የመጣ ስለሚያስመስል የመጨረሻ አማራጭ እንደሚሆንና አሁን ዋናው ሥራ የእምቢታ አመጹን አስተባባሪዎች የመለየት ሥራእንደሚሆን  አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡ የዚህ ሥራ መጀመርያ የሚሆነው ደግሞ ነጋዴዎች ስሜታቸውን የሚተነፍሱባቸው መድረኮች በየወረዳው እንዲመቻቹላቸውማድረግ፣ ቅሬታ አቅራቢዎችን በፍጥነት ማስተናገድ፣ በእምቢተኝነት የሚጸኑትን መለየት እንደሚሆንና ይህንንም የየክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችበአስተባባሪነት እንዲያስፈጽሙ ተወስኗል፡፡ የማዘጋጃ ቤቱን ስብሰባ የመሩ አንድ ባለሥልጣን “ትልልቅ አሶችን በቀጣይ መያዝ እንጀምራለን፤ይህንን ስል ከኛም ከነጋዴዎችም ይሆናል” ሲሉ መናገራቸውን የዋዜማምንጭ መስክሯል፡፡ ይህን የተናገሩት መንግሥት ለምን ትልልቅ ነጋዴዎች ላይ ትኩረት እንደማያደርግ ሐሳብና ጥያቄ በመነሳቱ ነው፡፡ በየወረዳው የሚገኙ ደንብ አስከባሪዎች በፖሊስ እየታጀቡ “ሱቃችሁን ካልከፈታችሁ እናሽግባችኋለን” የሚል ማስፈራሪያ ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ ማሰራጨታቸውንናዛሬ ጠዋትም ይኸው ቀጥሎ እንደነበር ታዝበናል፡፡  የነጋዴ አመጹን ማን አስተባበረው የሚለው ለመንግሥት ብቻም ሳይሆን ለአመጹ ተካፋዮችም ግራ ሆኗል፡፡ ትናንት የዋዜማ ዘጋቢ በተዘዋወረባቸው የመርካቶአካባቢዎች ነጋዴዎች ሱቆቻቸው ላይ ሆነው የሚሆነውን በመጠባበቅ ላይ እንደነበሩ ታዝባለች፡፡ “በርግጥ ጭምጭምታ ሰምቻለሁ፡፡ ጠዋት ስመጣ ግን ብዙ ሱቆችአልተከፈቱም ነበር፣ እኔም ዘግቼ ዋልኩኝ” ትላለች በብርድልብስና አልጋ ልብስ ንግድ የተሰማራች አንዲት ነጋዴ፡፡ “በፌስቡክ ተነግሯል ሲባል ነው የሰማሁት፤ እኔፌስቡክ የለኝም” ያሉ ሌላ በእድሜ የገፉ የኤሌክትሮኒክስ ነጋዴ  “ሰው የሚሆነውን መሆን ነው እንግዲህ፤ ይሄ ሁሉ ሰው ዘግቶ እኔ አልከፍትም” ብለዋታል ለዋዜማዘጋቢ፡፡ ኾኖም በእሚቢታ አመጹ ቀጣይነት ላይ ሁሉም የአመጹ ተሳታፊዎች ሳይቀር ጥያቄ አላቸው፡፡ “ሳንበላ እስከ ስንት ቀን ሱቅ ዘግተን እንውላለን?” ከሚሉት ጀምሮ“ንግድ ፍቃዳችን ሊነጠቅ ይችላል” የሚል ስጋት ያላቸው ነጋዴዎች በርካታ ናቸው፡፡ “በእርግጠኝነት የምነግርህ ይህ አመጽ ነገ አይቀጥልም፡፡ አሁን ራሱ ሁሉም ሰው እርስበርሱ ተፈራርቶ ነው ያለው፡፡ አስተባባሪ የለውም፡፡ በዚህ ላይ መሐላችንመንግሥትን በዚህ መልኩ መቃወም የማይፈልጉ  አሉ፡፡ ሱቁን ያልከፈተ ንግድ ፍቃዱን ይቀማል እየተባለ እየተወራ ነው፡፡ ነገሩ አስቸጋሪ ይመስለኛል” ይላል ሚሊቴሪተራ ብትን ጨርቃ ጨርቅ ንግድ ላይ የተሰማራ ጎልማሳ ነጋዴ፡፡ ዋዜማ ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ በደረሳት ያልተጣራ መረጃ ከትናንት ሰኞ ጀምሮ ሱቅ ያለመክፈት እንቅስቃሴ በመርካቶ በተለምዶ ወንበር ተራ በሚባለው አካባቢእንደሚኖር የሚጠቁም ቢሆንም ነገሩ አመጹ ትናንት እንደሆነው መላው መርካቶንና አካባቢውን የሚያዳርስ ይሆናል ተብሎ አልተጠበቀም ነበር፡፡ ኾኖም አብዛኛውነጋዴ በግብር ዉሳኔ ከፍ ያለ ቅሬታ የተፈጠረበት በመሆኑ እድሉን ሲያገኝ አመጹን ፈራ ተባ እያለም ቢሆን ለመቀላቀል ድፍረት እንዳገኘ ተገምቷል፡፡ “በአሁኑ ሰዓት ንግድ ፍቃዴን መልሱልኝ ማለት እንኳን በአመጽ የሚያስከስስ ሆኗል እኮ፡፡ ታምናለህ! የቀን ሽያጭህ 90 ሺህ ብር ነው ብለውኛል፡፡ ለምን ብዬ ነውከእንግዲህ መንግሥትን የምፈራው? ለምን ብዬ ነው ሱቅ የምከፍተው?” የሚለው አቶ አያሌው በሰሀን ንግድ ችርቻሮ ላይ የተሰማራ ነጋዴ ነው፡፡ “እኔ ከዚህ በኋላበንግድ ላይ ብዙ አልቆይም፡፡ ግን እኔ ብቻ አይደለሁም፡፡ ይህ መንግሥትም ብዙ ዓመት በሥልጣን ይቆያል ብዬ አልገምትም” ይላል በልበ ሙሉነት፡፡ “ነጋዴ ፈሪ ነው፡፡ ለአንድ ቀንም ቢሆን ሱቅ መዝጋቱ ቀላል ዉሳኔ አይምሰልህ፡፡ ነገሮች ካልተስተካከሉ እመነኝ የዚህ መንግሥት እድሜ እያጠረ ነው የሚሄደው” ሲልሀሳቡን ያጠናክራል፡፡ አቶ አያሌው ከባንክ ሠራተኝነት በቤተሰብ እገዛ ወደ ንግድ ከገባ አምስት ዓመት እንኳን አልሞላውም፡፡ “የዚህ ዓመት የቁርጥ ግብር ግምት ዉሳኔበመንግሥት የተመራ የለየለት ዘረፋና ዉንብድና ነው” ብሎ ያምናል፡፡ የዋዜማ ዘጋቢ ትናንትና በመርካቶ ዙርያ ባደረገው ሀሰሳ ከተክለሀይማኖት እስከ በርበሬ ተራ የሚገኙ ብረት ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች አብዛኛዎቹ ማለት ይቻላልሱቆቻቸውን ከፍተው በሥራ ላይ ሆነው ታይተዋል፡፡ ሲኒማ ራስ ዙርያ አርከበ ሱቆች ሙሉ በሙሉ የተዘጉ ሲሆን ሚስማር ተራ ዙርያ፣ ሳህን ተራ፣ ምናለሽተራ፣ ድርተራ፣ ሚሊቴሪ ተራ፣ ወንበር ተራ በአብዛኛው በአመጹ ተካፋይ ነበሩ፡፡ የአንዋር መስጊድና ራጉኤል ቤተክርስቲያን አጥሮችን ታከው የተገነቡ ሱቆች በስፋት አመጹንሳይቀላቀሉ በንግድ ላይ እንደነበሩ ለማየት ችለናል፡፡ ጎንደር ተራም በከፊል በሥራ ላይ ነበር፡፡ ወትሮ ለመኪና እጅግ አስጨናቂ የነበረው የመርካቶ መንገድ ትናንት የእረፍት ቀን እስኪመስል ድረስ ጭር ብሎ ታይቷል፡፡ ለመርካቶ ትልቁ የመኪና ማቆምያ የሆነውጣና ገበያም የፓርኪንግ አገልግሎቱን ዘና ብሎ ሲያከናውን ተመልክተናል፡፡ ይህ ስፍራ በሌሎች ቀናት ከፍተኛ መጨናነቅ የሚታይበት ነበር፡፡ በዱባይ ተራና ሳጥን ተራ አካባቢ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ሁኔታውን በካሜራ በመቅረጽ ላይ ሳሉ ” ዉሸታሞች፣ ሌቦች፣ ማታ የምትሉትን እንሰማለን…፣አንድ ጊዜ እንኳን እውነት ተናገሩ እስቲ…” የሚሉ ተቃውሞዎች በአካባቢው ቆመው ከነበሩ ነጋዴዎች ተሰንዝረውባቸዋል፡፡ ሱቆቻቸውን የከፈቱ ነጋዴዎችበበኩላቸው በካሜራ ላለመቀረጽ ጀርባቸውን ሲሰጡ ተመልክተናል፡፡ ዛሬ ጠዋት ላይ የዋዜማ ዘጋቢ በተዘዋወረባቸው የመርካቶ ሰፈሮች ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን ላለመክፈት ሲያመነቱና እርስበርስ ሲጠባበቁ የተመለከትን ሲሆን ብዙዎችየሚሆነውን ለማየት ከሱቆቻቸው አቅራቢያ ቆመው በመጠባበቅ ላይ ነበሩ፡፡ በሰዓቱ መጠነኛ ዝናብ እየጣለ ከመሆኑ ጋር ማለዳው ጭጋጋማ ስለነበረ ብዙዎችሱቆቻቸውን የከፈቱት ዘግይተው ነው፡፡ አብነት አዲሱ ሱማሌ ተራና ቁልፍ ተራ እስከ ረፋድ ድረስ ሱቆቻቸውን ባለመክፈት ጸንተዋል፡፡ ደንብ አስከባሪዎች የተዘጉሱቆችን መዝግቡ ተብለዋል፤ እርምጃም ይወሰዳል የሚል ወሬ በስፋት ከተሰማ በኋላ በርካቶች ሱቃቸውን ገርበብ አድርገው ታይተዋል፡፡ ምዕራብ ሆቴል አካባቢ የሚገኙ ከ10 የማይበልጡ ሱቆች ትናንት ማምሻውን ‹‹ደንብ በመተላለፍ ታሽጓል›› የሚል ወረቀት ተለጥፏል።

Read More →
Latest

‹‹በደረሰብኝ ድብደባ ግራ ጆሮዬ መስማት ተስኖታል›› ዳንኤል ሺበሽ

By   /  July 26, 2017  /  Ethiopia  /  Comments Off on ‹‹በደረሰብኝ ድብደባ ግራ ጆሮዬ መስማት ተስኖታል›› ዳንኤል ሺበሽ

#Ethiopia #HumanRights #FreeDanielShibeshi ስም፡- ዳንኤል ሺበሺ ከምሮ ዕድሜ፡- 41 አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 02 አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡- ቂሊንጦ እስር ቤት ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፋኝነት ምክንያት እንደታሰርሁ ነው የማምነው፡፡ ለእስር የሚያበቃኝ ወንጀል የሰራሁ ሆኜ አልነበረም ለእስር የበቃሁት፡፡ በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- በፌደራል አቃቤ ህግ የቀረቡ፣ ሁለት ክሶች አሉብኝ፡፡ አንደኛው ቀደም […]

Read More →
Latest

በብዕር ስም የሚንቀሳቀሱ አክቲቪስቶቹን ማን ነዉ እያሲያዛቸዉ ያለዉ? – ሸንቁጥ አየለ

By   /  July 26, 2017  /  Addis Admas, Ethiopia, ባላገሯ በአሜሪካ  /  Comments Off on በብዕር ስም የሚንቀሳቀሱ አክቲቪስቶቹን ማን ነዉ እያሲያዛቸዉ ያለዉ? – ሸንቁጥ አየለ

ሰሞኑን የአማራ አክቲቪስቶች በወያኔ መጠለፋቸዉን አንዳንድ ወንድሞች እዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለጥፈዉ አነበብኩ:: የመረጃዉ አስገራሚነት ደግሞ አንዳንዶቹ ስድስት አክቲቪስቶች ናቸዉ የተጠለፉት ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ ሁለት ናቸዉ ወይም ሶስት ናቸዉ የሚል መረጃ ላይ መከራከራቸዉ ነዉ:: ነገሩን ጠጋ ብሎ ለመረመረዉ ሰዉ ደግሞ አንድም ተጠለፈ ስድስትም ተጠለፈ ለዉጥ የለዉም:: በጣም አስገራሚዉ ነገር ታዲያ እነዚህ ሁለት ወይም አንድ ወይም […]

Read More →
Latest

ነገሪ ሌንጮ፣  አቦይ ስብሃት በሙስና መታሰራቸውን ይንገሩን ክንፉ አሰፋ

By   /  July 26, 2017  /  Ethiopia  /  Comments Off on ነገሪ ሌንጮ፣  አቦይ ስብሃት በሙስና መታሰራቸውን ይንገሩን ክንፉ አሰፋ

የነጋዴዎች አድማ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ገዥው ፓርቲ ከየአቅጣጫው በመወጠሩ – የችግሩን ትኩረት አቅጣጫ ማስቀየር አለበት። የተለመደ የፉገራ ካርዳቸውን መዘዝ አድርገው ለዶ/ር ነገሪሌንጮ ሰጡዋቸው። ኦቦ ነገሪ ሌንጮ 34 የመንግስት ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ትናንት ምሽት  አብስረዋል።   እነማን እንደታሰሩ ግን አልገለጹም።  ታሳሪዎቹንሊያውቁዋቸው ስለማይችሉ ሊገልጹ እንደማይችሉ ግልጽ ነው።     እንደወትሮው ተጽፎ የተሰጣቸውን ከማንበብ ውጭ አማራጭ የላቸውም።  የፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን መታሰር  እንደማንኛውምተራ ሰው በዜና የሰሙት ነገሪ ሌንጮ ምን አፍ ኖሯቸው ስለ ባለስልጣናት መታሰር ይነግሩናል?  ስራዎቼን ሁሉ በግምት ነው የምሰራው – መረጃ እንኳን አይሰጡኝም የሚሉ ጠቅላይ ሚኒስትርስ ምንአቅም ኖሯቸው ጉዳዩን ያስፈጽሙታል? የሙስና ጉዳይ በየአመቱ ነው የሚነሳው። ችግር ሲመጣ እየጠበቁ ለአቅጣጫ ማስቀየርያ ይለቁብናል። አንዳንዴ በሙስና ታሳሪ ገጸ-ባህርያትን ይፈጥሩና አስቂኝ ድራማ ያሳዩናል። ሌላ ግዜ ደግሞየንግድ ባላንጣዎቻቸውን ለመበቀል ይጠቀሙበታል። አንዳንዴም ለመታመን ሲሉ ተራ የመንግስት ሰራተኞችን እና ነጋዴዎችን ይዘው ያጉሯቸውና ግርግሩ ሲረሳሳ ደግሞ ይለቋቸዋል። በእርግጥ የሙስና ተጠርጣሪዎችን ማሰር ቢያስቡ-  መጀመርያ አቦይ መስፍንን ወይንም አዜብ መስፍንን በማሰር ያሳዩን ነበር።  ጸረ-ሙስናው ዘመቻ እውን ቢሆን ኖሮ የህወሃት የጦር አለቆችበሙሉ መኖርያቸው ቂሊንጦ በሆነ።  የአቶ ስብሀት ነጋ ልጅ ተከስተ ስብሀት ነጋ እና  እህት ቅዱሳን ነጋ ህልቕ መሳፍርት ንብረት ቢታገድ ነበር ጸረ-ሙስና ዘመቻ ተጀመረ ምንለው። የሙሰኞች ንብረት ታገደ የምንለው የጄነራል  ሳሞራ የኑስ፣  የሌ/ጄ ታደሰ ወረደ፣  የሌ/ጄ ገዛኢ አበራ፣ የሌ/ጄ ብርሃነ ነጋሽ፣ የሌ/ጄ ሳእረ መኮንን ቦሌ ላይ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ቤቶችሲታገዱ ነው። ሌ/ጄ ገዛኢ አበራ፣ ሌ/ጄ ብርሃነ ነጋሽ ፣  ሌ/ጄ ሳእረ መኮንን ፣  ሌ/ጄ አበባው ታደሰ፣   ሜ/ጄ አብርሃ ው/ገብርኤል ፣ ሜ/ጄ ዮሃንስ ገ/መስቀል፣  ሜ/ጄ ስዮም ሃጎስ፣  ሜ/ጄ ሃየሎም አርአያ፣  ሜ/ጄ ገ/እግዚአብሄር መብራቱ፣  ብ/ጄ ታደሰ ጋውና፣  ብ/ጄ ተክላይ አሽብር፣  ብ/ጄ ፍስሃ ኪዳነ፣ ብ/ጄ ፓትሪስ፣ ብ/ጄ መስፍን አማረ፣  ብ/ጄ ምግበ ሃይለ፣ ብ/ጄ ሃለፎም ቸንቶ፣  ኮ/ል ታደስ ንጉሴ፣  ኮ/ልጸሃየ መንጁስ በህዝብ ገንዘብ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ያሰሩዋቸው  በሚሊዮኖች የሚገመቱ ቤቶች  በወር ደሞዛቸው እንዳልሆነ  ፖሊስና አቃቤ ህግ ሳያውቁት ቀርተው ነው? እነ ብርሃኔ ገብረ ክርስቶስ፣   አባዲ ዘሙ፣   ስብሃት ነጋ፣ ሽመልስ ኪዳኔ፣  አርከበ እቁባይ፣  አባይ ጸሃዬ፣  ገብረ መድህን ገብረ ዮሃንስ፣ ደብረጽዮን ገብረ ሚካአኤል, ቴዎድሮስ ሃጎስ፣   ታደሰ ሃይሌ፣  ሰምሃል መለስ ዜናዊ ከባህር ማዶ ያከማቹት በቢሊዮን የሚቆጠር የህዝብ ገንዘብ እስቲ ይታገድ እና ነገሪ ሌንጮን እንመን። ይህን መራራ ሃቅ የሚክድ የለም። ራሳቸውም የሚሉት ነው።  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲፈሩ ሲቸሩ “ሙስና አለ – ማስረጃ የለም” ብለውናል። አቦይ ስብሃት ደግሞ በሰንደቅ ጋዜጣ አዳልጧቸው  “መቶሚልዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፤ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ሲያስፈራሩት ይታያሉ”  ብለው ነበር።  የየሃገራቱን የሙስና መጠን ደረጃ  በየአመቱ የሚዘግበው  ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናልየተባለዉ ተቋም ኢትዮጵያ   ከፍተኛ ሙስና ከሚፈፀምባቸዉ ሃገራት አንዷ መሆኗን አመልክቷል። እንደ ተቋሙ ዘገባ ከሆነ ከኢትዮጵያ በህወሃት ዘመን ተዘርፎ የወጣው ገንዘብ 17 ቢሊየን ዶላርይደርሳል።  ጥናት ከተደረገባቸው 174 ሃገሮች መካከል ኢትዮጵያ 113ኛ ቦታን ይዛለች። ይህ  ቁጥር መንግስታዊ ሙስናው ሃገሪቱን ምን ያህል እንደ መዥገር እመጠጠ መሆኑን ያሳየናል።   በታቦኢምቤኪ የመሩት ሌላ ጥናት ደግሞ በአምስት ዓመታት ዉስጥ ብቻ ከኢትዮጵያ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ 10 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ወደ ዉጭ እንዲወጣ ተደርጓል። በአንድ ወቅት በጸረ-ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣናቱን ንብረት የመመዝገብ ደንብ ወጣና ስራውን ጀመረ። ብዙ የተወራለት ይህ ኮሚሽን  ወደ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ቤት ነበር ቀድሞ ያመራው። አይተሳሞራም የጸረ-ሙስናውን ቡድን አስቀምጦ “ስራችሁን አደንቃለሁ። ጥሩ  ጅምር ነው። ግን ከላይ ጀምሩ” ብሎ ወደ  አዜብ መስፍን መራቸው።  ንብረት መዝጋቢዎቹ ወደ አዜብ ቤት  ሳይደርሱግማሽ መንገድ ላይ እንደጠፉ ይነገራል።  አዲዮስ ፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን! የሲቪክ ማኅበራት በነፃነት መንቀሣቀስ  በማይችሉበት፣  የፕሬስ ነጸነት በታፈነበትና  የህግ የበላይነት በሌለበት ሃገር ሙስናን እናጠፋለን ማለት በህዝብ ሳይሆን በራስ ላይ መቀለድ ነው የሚሆነው።አላማው ከችግሩ አቅጣጫ ለማስቀየር ከሆነ ደግሞ ሌላ ካርታ መጠቀሙ የሚበጅ ይመስላል። ደጋግማችሁ በተባላ ካርታ  አትጫወቱ።

Read More →
Latest

ሌንጮ ለታ እቅጩን ተናገሩ – “ተቃዋሚዎች ራሳችንን ማታለል የለብንም” | ሊታይ የሚገባው ወቅታዊ ቃለምልልስ ይዘናል

By   /  July 26, 2017  /  Ethiopia  /  Comments Off on ሌንጮ ለታ እቅጩን ተናገሩ – “ተቃዋሚዎች ራሳችንን ማታለል የለብንም” | ሊታይ የሚገባው ወቅታዊ ቃለምልልስ ይዘናል

<…ተቃዋሚዎች ራሳችንን ማታለል የለብንም። በአስቸኳይ ከኢህአዴግ ተቃራኒ የሆነ ሀይል መፍጠር አለብን። እነሱ ስልጣን ላይ ሲወጡ ሁለት ስትራቴጂ ነድፈው ነው። ከቻሉ ኢትዮጵያን መግዛት ካልቻሉ እስር በእርስ አጋጭተው አገሪቱን በትነው ወደ መጡበት መሄድ ነው። በአስቸኳይ አማራውም ሌላውም ብሄር የተወከለበት …ሁል ጊዜ ከወያኔ የሚመጣ ነገር መጠራጠር አለብን። እነሱ በሚሰጡን አጀንዳ መነታረክ የለብንም የአዲስ አበባም ጉዳይ ቢሆን እነሱ አማራና […]

Read More →
Latest

በሲያትል የኢትዮጵያዊው አሟሟት እንቆቅልሽ አልተፈታም

By   /  July 26, 2017  /  Ethiopia  /  Comments Off on በሲያትል የኢትዮጵያዊው አሟሟት እንቆቅልሽ አልተፈታም

  አድማስ ዜና፦ ከሲያትል የተሰማው ዜና አሳዛኝ ነው። ባለፈው እሁድ፣ ጁላይ 23 ንጋት ላይ ነው፣ የ 36 ዓመቱ ይትባረክ ደሞዝ፣ ለባለቤቱ፣ “ጓደኞቼን አንድ ቦታ ማድረስ አለብኝ” ይላትና ይወጣል። በምን ምክንያት እንደሆነ አይታወቅም፣ የጠቀሳቸው ሰዎችና እሱ፣ 25 ጫማ ርዝመት ባለው የይትባረክ ጀልባ ላይ ተሳፍረው ዩኒየን በተባለ ሐይቅ ላይ ነበሩ። በመካከል ድንገት ለፖሊስ አንድ ጥሪ ይደርሳል፣ ጥሪውም […]

Read More →
Latest

የግብር አሰባብሰብ የአዲስ አበባን ንግድ ተቋማትን እያዘጋ ነው ክልሎችም ይቀጥላሉ

By   /  July 24, 2017  /  Ethiopia  /  Comments Off on የግብር አሰባብሰብ የአዲስ አበባን ንግድ ተቋማትን እያዘጋ ነው ክልሎችም ይቀጥላሉ

በመዲናችን አዲስ አበባ እና በክክል ከተሞች የተካሄደው የቀን ገቢን አስልቶ የተተመነው የታክስ (ግብር አሰባሰብ ስርአት የተዛባ ከመሆኑ የተነሳ በሃገሪቱ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ለውጥ እንንደሚያመጣ ተፈረⶆል ። እንደ አንዳንድ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች አገላለጽ ከሆነ መንግስት ይህንን ያህል ጫና በማህበረሰቡ ላይ ልጭን የተፈለገበት ዋነኛ ምክንያት በእራሱ በመንግስት ባለስልጣናት በስውር የተመዘበሩ ገንዘቦችን በህዝቡ ላብ ሊተካው ስላሰበ ነው ሲሉ ጠቁመዋል […]

Read More →
Latest

የግብሩ አመጽ – የፍጻሜው ጦርነት ክንፉ አሰፋ

By   /  July 23, 2017  /  Ethiopia  /  Comments Off on የግብሩ አመጽ – የፍጻሜው ጦርነት ክንፉ አሰፋ

        የአስቸኳይ (የአፈና) ግዜ  አዋጁ ገና አልተነሳም። በአዲሱ የግብር ትመና ሳብያ ከዳር እስከዳር የተነሳው ሕዝባዊ አድማ እና አመጽ ግን አዋጁን ውድቅ ያደረገው ይመስላል። አንድ ስርዓት ራሱ ያወጣው ህግ በህዝብ ሲሻርበት – ያኔ ነው ያበቃለት!         ከቶውን “የአለምን  ኢኮኖሚ እየመራች ያለች ሃገር” የበጀት ሸክሟን ለምን በህዝብ ላይ መጣል እንዳለባት ግልጽ አልሆነም። እውነታው ከነዚህ ሁለት እይታዎች ውጭ […]

Read More →
Latest

በአዲስ አበባ ሳሪስ፣ ኮልፌ፣ ቡራዩ፣ ደምቢዶሎ፣ ነጆ፣ ነቀምቴ በሥራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው | ወደ ሰሜን ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች ማስጠንቀቂያ ተላለፈ!!

By   /  July 22, 2017  /  Ethiopia  /  Comments Off on በአዲስ አበባ ሳሪስ፣ ኮልፌ፣ ቡራዩ፣ ደምቢዶሎ፣ ነጆ፣ ነቀምቴ በሥራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው | ወደ ሰሜን ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች ማስጠንቀቂያ ተላለፈ!!

(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት መራሹ መንግስት የጣለውን አግባብ ያልሆነ ግብር በመቃወም የተጀመረው የሥራ ማቆም አድማ በተለያዩ ቦታዎች እየተስፋፋ ነው:: በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሳሪስ እና ኮልፌ አካባቢ ንግድ ሱቆች መዘጋጋታቸው ታውቋል:: ሳሪስ ሙሉ በሙሉ ዝግ ስትሆን በኮልፌ አካባቢ ግን አንዳንድ ነጋዴዎች የመንግስትን ማስፈራሪያ ተቀብለው መክፈታቸው ተሰምቷል:: ለነዚህ ሱቃቸውን በመክፈት መንግስትን ለተባበሩት ነጋዴዎች ከአካባቢው ነዋሪዎች ማስጠንቀቂያ እንደተላለፈላቸው ለማወቅ […]

Read More →
Latest

EU commend Ethiopia’s initiative to make political reforms

By   /  July 21, 2017  /  AFRICA, Ethiopia, WEST AFRICA, ኣማርኛ  /  Comments Off on EU commend Ethiopia’s initiative to make political reforms

AFRICA INTELLIGENCE MEDIA By Tesfa-Alem Tekle July 20, 2017 (ADDIS ABABA) – The European Union (EU) on Thursday commended the ruling party, Ethiopia peoples Revolutionary Democratic Front (EPRDF) for opening space for dialogue with opposition parties. Currently, 21 political parties, including the ruling coalition EPRDF are engaged in consultations and debate to bring about political […]

Read More →
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar