ፓርኮቹ በናይጄሪያ አርብቶ አደሮች አደጋ ገብተዋል
ከምዕራብ አፍሪካ አገራት በመነሳት በረሃዎችን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ የሚፈልሱ የፈላታ ጎሳዎች መጨመራቸው የጋምቤላ እና አልጣሽ ፓርኮችን ችግር ውስጥ ከቷቸዋል ሲል የፌዴራል ዱር እንስሳት ልማት ባለሥልጣን ለአዲስ ማለዳ ስጋቱን ገለፀ። ከናይጄሪያ እንዲሁም ጥቂቶቹ ከቻድ እና ማሊን በመነሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚፈልሱት የፈላታ ጎሳዎች፤ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ከብቶቻቸውን በመያዝ መድረሻቸውን የጋምቤላ በተለይም ደግሞ አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ማድረጋቸው የአገሪቷ […]
Read More →የአዲሱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆቴል የቻይና ኩባንያ ያስተዳድረዋል
በ65 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባውና ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ ሰካይ ላይት ሆቴል ዕዳውን ከፍሎ እስኪጨርስ በቻይናው ኩባንያ ‹‹ግራንድ ስካይ ላይት ሆቴል ማኔጅመንት›› አስተዳደር ሥር እንደሚሆን ተገለፀ። በቻይና ብሔራዊ የአየር ቴክኖሎጂ ዓለም ዐቀፍ የምህንድስና ኮርፖሬሽን የተገነባው ይህ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል የግንባታ ዕዳውን በጨረሰ ጊዜ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥር እንደሚሆን ታውቋል። ለሆቴሉ […]
Read More →በኦነግና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት መካከል የነበረው ቅራኔ በእርቅ ተፈቷል መባሉን ተከትሎ ኦነግ ሠራዊቱን በ20 ቀናት ወደ ካምፕ እንዲያስገባ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ። ወታደሮቹ ወደካፕ ሲገቡ የጀግና አቀባል እንዲደረግላቸው የሚል ውሳኔ የተላላፈም ሲሆን፣ በመንግሥት በኩል ወታደሮቹ ቶሎ ወደ ካምፕ እንዲገቡ ጉጉት መኖሩ ተነግሯል። በአዲሱ እርቅ የተላላፉ ውሳኔዎችን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበልም መንግሥት አሳውቋል። ወታደሮቹ ወደ ካምፕ ሲገቡ […]
Read More →የአዲስ አበባ አስተዳደር ከ7,700 በላይ ለሚሆኑ ነጋዴዎች የግብር ዕዳ ምሕረት ማድረጉን አስታወቀ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ የተጣለባቸው ግብር ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ እንዲታይላቸው ሲጠይቁ ለቆዩ 6,000 ነጋዴዎች፣ እንዲሁም በግብር ይግባኝ ተከራክረው ለተፈረደባቸው 1,780 ነጋዴዎችም ምሕረት እንዲደረግላቸው ካቢኔያቸው መወሰኑን አስታወቁ። ምክትል ከንቲባው ይህን ያስታወቁት የአስተዳደሩ ገቢዎች ባለሥልጣን በጠራው ከተማ አቀፍ የታክስ ንቅናቄ መድረክ ላይ ነው። በቅርቡ በገቢዎች ሚኒስቴር ‹‹ግዴታዬን እወጣለሁ፣ መብቴንም እጠይቃለሁ›› በሚል መርሐ […]
Read More →የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ታስረው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የተሰጠው ትዕዛዝ ተቀየረ
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የፍርድ ቤት ውሳኔ አፈጻጸምን ተግባራዊ ሊያደርግ ባለመቻሉ፣ ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን ታስረው እንዲቀርቡ በፍርድ ቤት የተሰጠ ትዕዛዝ በሌላ ኃላፊ መቀየሩ ታወቀ፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 26(1)ን በመተላለፍ የተቋሙን አንድ ኃላፊ ያለፈቃዳቸውና በሌለ የሥራ ቦታ መመደባቸው ተገቢ አለመሆኑ ተገልጾ፣ በፍርድ ቤት የተሰጠን ውሳኔ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው፣ የፌዴራል መጀመርያ ደረጃ […]
Read More →ከእስር ለመፈታት ከፍተኛ ገንዘብ መክፈላቸው የተሰማው ሼክ አል አሙዲ ሀብታቸው ማሽቆልቆሉ በፎርብስ ተረጋገጠ
እሑድ ጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ከአንድ ዓመት ከሁለት ወራት በላይ ታስረው የተለቀቁት ሼክ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አል አሙዲ፣ ከእስር ነፃ ለመውጣት ከፍተኛ ገንዘብ መክፈላቸው ተሰማ፡፡ ባለፈው ዓመት 10.9 ቢሊዮን ዶላር ሀብት የነበራቸው ሼክ አል አሙዲ፣ በአሁኑ ወቅት በፎርብስ የቢሊየነሮች ዝርዝር ላይ በ1.2 ቢሊዮን ዶላር ሀብት 159ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ፎርብስ እ.ኤ.አ. በ2018 ሼክ አል […]
Read More →ይድረስ ለከንቲባ ታከለ ኡማ !! ከዘካርያ መሃመድ
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ታከለ ዑማ፣ በአዲስ አበባ የጎዳና ላይ ሕይወት የሚገፉ ወገኖች (ሕፃናትና ወጣቶች) “የነገ ህልማቸውን እንዲኖሩ የማድረግ ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን” ከሚል ስሜት ተነስተውና፣ በተጨማሪም ልመናን “ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት” በማለም በከፍተኛ የገንዘብ አቅም የሚተገበር የድጋፍ ማዕከል ለመመሥረት “የማኅበራዊ ትረስት ፈንድ” ማቋቋማቸውን በዜና ሰማሁ። .ከንቲባ ታከለ ይህን ዓላማ ለማሳካት፣ ከከተማው አስተዳደር ካዝና ወጪ የሚደረግ ከፍተኛ […]
Read More →በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ወደ ጎዳና ላይ የወደቁ ማህበረሰቦችን ለማንሳት ዝግጅት ተጀመረ
ኑሮ ካሉ መቃብር ይሞቃል፤ ያሉት ከንቲባ ታከለ ኡማ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት ከሆነ “==================አዲስ አበባችን ከድሃ እስከ ሃብትም፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚኖሩበትና “ኑሮአቸውን ” በአቅማቸው ልክ የሚገፉበት ከተማ ናት። ዛሬ ጠዋት በከተማችን ጎዳናዎች ላይ ካሉት ጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር የቁርስና ውይይት ጊዜ ነበረን። ወደ ማገገሚያ ማዕከል የማስገባት ሥራዎችን በኣንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል። ” ብለዋል። ተጠሪነቱ ለኘሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ […]
Read More →40 በመቶ እናቶች ከጤና ተቋም ውጪ ይወልዳሉ ተባለ
በኢትዮጵያ በጤና ተቋም መውለድ ከነበረባቸው እናቶች 40 በመቶዎቹ ከጤና ተቋማት ውጪ መውለዳቸውን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ። ሚንስትሩ ዶክተር አሚር አማን ማክሰኞ፣ ጥር 14 ለተወካዮች ምክር ቤት የመስሪያ ቤታቸውን የስድስት ወራት አፈፃፀም ባቀረቡበት ወቅት ነው፤ ይህን የተናገሩት። ሚንስትሩ እንዳሉት በሰለጠነ ባለሙያ የሚሰጥን የወሊድ አገልግሎት ማግኘት ይጠበቅባቸው ከነበሩት አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ነፍሰ ጡር እናቶች መካከል በጤና ተቋማት […]
Read More →6 የሱማሌ ክልል ከፍተኛ ኃላፊዎች ከሥልጣናቸው ተነሱ
ረቡዕ፣ ጥር 15 የሱማሌ ክልል መንግሥት ካቢኔ ባደረገው ስብሰባ ስድስት የክልሉን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ወስኗል።ከኃላፊነት ከተነሱት ውስጥ የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና የምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪ ይገኙበታል። የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊውም ምክትላቸው በነበሩት አብዱላሂ መሐመድ ተተክተዋል። ‹‹ለአመራሮቹ ከስልጣን መነሳት ምክንያት የሆነው በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ዑመር መሐመድ […]
Read More →
