የቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ አምስት ኃላፊዎች በሙስና ወንጀል ተከሰሱ
በመንግሥት ላይ ከ319.4 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብሏል ሥልጣናቸውን ያላግባብ ተገልግለው በመንግሥት ላይ ከ319.4 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ፣ አምስት ኃላፊዎችና ሦስት በግል ሥራ ተሰማርተዋል የተባሉ ግለሰቦች ላይ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ጥር 2 ቀን 2011 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት […]
Read More →በሙስና ወንጀል የተከሰሱ የአቢሲኒያ ባንክ ሠራተኞች ጥፋተኛና ነፃ ተባሉ
ትክክለኛውን የስዊፍት መክፈያ መልዕክት መለያ ቁጥር፣ የተቀባይን ስምና አድራሻ በማስተካከል፣ ሌሎችንና ራሳቸውንም ለመጥቀም በአቢሲኒያ ባንክ ላይ ከፍተኛ የገንዘብ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው የተከሰሱ አራት ሠራተኞች ጥፋተኛና ነፃ ተባሉ፡፡ የወንጀል ድርጊቱን ፈጽመዋል ተብለው በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት፣ በኢቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ዓለም አቀፍ የባንኮች ግንኙነት መምርያ የትራንስፈር ሰርቪስና ኮሮስፖንዲንግ ባንኪንግ ኦፊሰር ወ/ሮ ሔለን አሰፋ፣ የትራንስፈር […]
Read More →ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሪዮስ ዛሬ ጐንደር ይገባሉ
ህዝቡ በጉጉት ይጠብቃቸዋል ተብሏል ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሪዮስ ዛሬ ጐንደር የሚገቡ ሲሆን ከ27 ዓመታት በኋላ የጐንደርን መሬት ይረግጣሉ ተብሏል፡፡ የአቀባበሉ ኮሚቴ አባል ዲያቆን አደራጀው አዳነ ለአዲስ አድማስ እንደገለፀው የጐንደር ህዝብ በጉጉት ነው የሚጠብቃቸው፡፡ ለፓትሪያሪኩ ከጐንደር አፄ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ ፋሲል ግንብ አጠገብ እስከሚገኘው አደባባይ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ድረስ በበርካታ ህዝብና ተሽከርካሪዎች ታጅበው እንደሚጓዙ የተገለፀ ሲሆን፤ […]
Read More →በጎንደር የንፁሃን ህይወትን ያጠፉ በህግ ይጠየቃሉ ተባለ
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር በገንዳ ውሃ ከተማ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ህፃናትን ጨምሮ 8 ሰዎች የሞቱበትን ሁኔታ የሚያጣራ ቡድን ወደ ሥፍራው እንደሚላክ የገለፀው የአማራ ክልል መንግስት፤ ያልተመጣጠነ ኃይል የተጠቀሙ በህግ ይጠየቃሉ ብሏል፡፡ በአካባቢው በመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ላይ ተሰማርቶ የነበረው ሱር ኮንስትራክሽን ድርጅት፣ ተሽከርካሪዎቹን ለማንቀሳቀስ በሞከረበት ወቅት በተፈጠረ አለመግባባት ክስተቱ መፈጠሩን የጠቆሙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ […]
Read More →ላለፉት 2 ወራት በብሄር በግጭት ሳቢያ የ256 ዜጐች ህይወት ጠፍቷል ለጠፉት ህይወት ዳውድ ኢብሳ ተጠያቂ ነው
በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በተፈጠሩ ግጭቶችና በተሰነዘሩ ጥቃቶች ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ 256 ዜጐች መገደላቸውን የሠብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሠመጉ) አስታወቀ፡፡ የተለያየ መነሻ ምክንያት ባላቸው ብሔር ተኮር ግጭቶች ሳቢያ የሰው ህይወት በከንቱ እየጠፋ መሆኑ እንዳሳሰበው የገለፀው ሠመጉ፤ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል ክልሎችና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በህዳርና ታህሳስ 2011 ዓ.ም በተፈጠሩ ግጭቶች 256 ሰዎች መገደላቸውንና በአስር ሺዎች […]
Read More →Sidama referendum should proceed without further delay
After the Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF) assumed power in 1991, the Sidama nation was granted regional self-administration. This proved to be short-lived. Five districts of the south were then merged together without due consultation to construct the Southern Nations Nationalities and Peoples’ Regional State (SNNPRS). However, the constitution provides the right to statehood, […]
Read More →በእነ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የክስ መዝገብ ስር የሜቴክ ከፍተኛ ኃላፊዎች በመንግሥት ላይ ከ319 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ ተጠርጥረው ክስ ተመሠረተባቸው
የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከፍተኛ ኃላፊዎች በመንግሥት ላይ 319,475,287 ብር ጉዳት በማድረስ ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ በክሱ የተካተቱት የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ የሜቴክ የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የግብይትና ሽያጭ ኃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁርንዲ፣ የአዳማ እርሻ መሣሪያዎች ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የቀድሞ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል […]
Read More →ሰበር ዜና አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
የአክሰስ ሪል ስቴትና የዘመን ባንክ መሥራች አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሥረኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጥር 3 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀረቡ፡፡ አቶ ኤርሚያስ ፍርድ ቤት የቀረቡት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በሸጡት የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ጋር በተገናኘ መሆኑ ታውቋል፡፡
Read More →ETHIOPIA HAS PAID A NEW YORK AGENT TO SEND BY AIR FREIGHT SOME AMERICAN SPARE PARTS FOR ITS WARPLANES
WikiLeaks ShopDonateSubmit Leaks News About Partners Press releaseAbout PlusD Browse by creation date 19661972197319741975197619771978197919851986198719881989199019911992199319941995199619971998199920002001200220032004200520062007200820092010 Browse by Classification UNCLASSIFIEDCONFIDENTIALLIMITED OFFICIAL USESECRETUNCLASSIFIED//FOR OFFICIAL USE ONLYCONFIDENTIAL//NOFORNSECRET//NOFORN Browse by Handling Restriction EXDIS – Exclusive Distribution OnlyONLY – Eyes OnlyLIMDIS – Limited Distribution OnlyNODIS – No Distribution (other than to persons indicated)STADIS – State Distribution OnlyCHEROKEE – Limited to senior […]
Read More →የናይጀሪያውያን በኢትዮጵያ እጽ የማዘዋወር ህገ ወጥ ስራ መስፋፋቱ ተገለጠ
ባለፉት ስድስት ወራት በሕገወጥ መንገድ አደገኛ እጽን ሲያዘዋውሩ ከተገኙ 56 የተለያዩ አገራት ዜጎች 19ኙ ናይጀሪያዊያን መሆናቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።በአደገኛ እጽ ዝውውር ባለፉት ስድስት ወራት የ15 አገራት ዜግነት ያላቸው 56 አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለው ኮሚሽኑ 19 ናይጄሪያውያን ሲሆኑ ዐሥሩ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አሳውቋል። እንደኮሚሽኑ መግለጫ ከአዘዋዋሪዎቹ 95 ኪሎ ግራም ካናቢስ እና 141 ኪሎ ግራም በላይ ኮኬን ተይዟል።በተያያዘ […]
Read More →
