የትምባሆ የአልኮልና የመድኃኒት ቁጥጥር አዋጅ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆን ጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ጠየቁ
የትምባሆ፣ የአልኮል፣ የመድኃኒትና ምግብ ነክ ምርቶችን ለመቆጣጠር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆን የጤናጥበቃ ሚኒስትሩ ምክር ቤቱን ጠየቁ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕፃናት ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ረቂቅ አዋጁን በዝርዝር ለመመርመር ዛሬ ረቡዕ ታኅሳስ 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሄደው ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን በረቂቅ አዋጁ ላይ የተቀመጡ ክልከላዎች በቂ አለመሆናቸውንበመገንዘብ ክልከላዎቹ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆኑ የማሻሻያ ሐሳብ ለቋሚ ኮሚቴው አቀረቡ። ካቀረቧቸው ጥብቅ የማሻሻያ ክልከላዎች መካከል እንደ ቢራ ያሉ የአልኮል ምርቶች በኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች ማለትም በሬዲዮና በቴሌቪዥን ከምሽቱ 3፡00ሰዓት እስከ ሌሊት 12፡00 ሰዓት ብቻ እንዲተዋወቁ በረቂቁ ላይ የተቀመጠው ድንጋጌ ተሻሽሎ፣ የአልኮል ምርቶች በተጠቀሱት ሚዲያዎች ሙሉ ለሙሉእንዳይተዋወቁ ክልከላ እንዲጣል የሚል የማሻሻያ ሐሳብ አቅርበዋል። የአልኮል ምርቶች ማለት የአልኮል ይዘታቸው ከሁለት በመቶ በላይ መሆኑን የሚገልጸው የረቂቅ አዋጁ ትርጓሜ ተሻሽሎ የአልኮል ይዘቱ ከ0.5 በመቶ በላይበሚል እንዲሻሻልም የጠየቁ ሲሆን፣ ለዚህ ያቀረቡት ምክንያትም አልኮል የሚያመርቱ ኩባንያዎች ከሁለት በመቶ በታች የሆኑ የአልኮል ምርት ዓይነቶችንበማምረት የአልኮል መጠጦች በተጠቀሱት ሚዲያዎች እንዲተዋወቁ ዕድል የሚሰጥ በመሆኑ ነው። የአልኮል መጠጦችን ለማስተዋወቅና ገበያውን ለማስፋት ከፍተኛ ሽልማቶችን የሚያስገኙ ዕጣዎችን በቆርኪ ላይ ማያያዝ ክልከላ እንዲደረግበትም ሐሳብአቅርበዋል። ሚኒስትሩ እነዚህ ጥብቅ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ቋሚ ኮሚቴውን በጽሑፍ መጠየቃቸውን ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በሕዝባዊ ውይይትመድረኩ ላይ የተገኙ የጤና ባለሙያዎች፣ ታዋቂ አርቲስቶች፣ ወጣት ተማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች ረቂቅ አዋጁ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆንና የአልኮልማስታወቂያ እንዲቆም በተደጋጋሚ በመጠየቃቸው ነው። የትምባሆና አልኮል ሽያጭን በተመለከተ ረቂቅ ሕጉ ላይ ሁለቱም ምርቶች ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች እንዳይሸጡ የሚደነግገው አንቀጽ ተሻሽሎ ከ21 ዓመትበታች እንዲባል ጠይቀዋል። ይኼን ሐሳብም በሕዝባዊ የውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት አብዛኞቹ ደግፈውታል። የኢትዮጵያ ትምባሆ ኢንተርፕራይዝ የሥራ ኃላፊዎች በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ረቂቅ የቁጥጥር ሕጉ በኩባንያው ላይ ሊያደርስ ይችላል ያሏቸውንሥጋቶች አንስተዋል። ካነሷቸውም ሥጋቶች መካከል ዋነኛው በረቂቁ የተቀመጡ የቁጥጥር ሕጎች የኮንትሮባንድ የሲጋራ ንግድን ያበረታታል የሚል ነው። ይኼም ከሥጋት ባለፈተጨባጭ መሆኑን ለማስረዳት በአሁኑ ወቅት እንኳን የአገሪቱ የሲጋራ ገበያ 44 በመቶው በኮንትሮባንድ በሚመጡ ምርቶች የተያዘ መሆኑን አንስተዋል። የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጡት ምላሽ አጠቃላይ የኮንትሮባንድ ንግድን በተመለከተ መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንጠቅሰው፣ የሲጋራ ኮንትሮባንድ ንግድን በተመለከተ ግን የትምባሆ አምራች ኩባንያዎች ጥብቅ የቁጥጥር ሕግ መንግሥታት እንዳያወጡባቸው ሲሉ ራሳቸውየኮንትሮባንድ የሲጋራ ንግድ እንዲስፋፋ በማድረግ አልያም መስፋፋቱን በመደገፍ መንግሥት የቁጥጥር ሕግ ቢያወጣ ኮንትሮባንድ እንዲስፋፋ ከማድረግየዘለለ ትርጉም እንደማይኖረው ለማስመሰል እንደሚሞክሩ ለመድረኩ አስረድተዋል። ከመድኃኒት አስመጪዎችም በርከት ያሉ ሥጋቶች የተነሱ ሲሆን፣ ቋሚ ኮሚቴው የተነሱትን በግብዓትነት ወስዶ ተጨማሪ የውይይት መድረክ መጥራት አስፈላጊመሆኑን ካመነበት የሚከለክለው ነገር ባለመኖሩ ሊጠራ እንደሚችል ገልጿል። ይሁን እንጂ ረቂቅ አዋጁ የንግድ ጥቅማቸውን የሚነካባቸውም ሆኑ ሌሎች ለቋሚ ኮሚቴው አመራሮችና አባሎች በግል ስልካቸው ላይ በመደወል ማስቸገርእንደሌለባቸውና ተግባሩ እንዲቆም አሳስበዋል።
Read More →አርበኛ፣ ፀሐፊ- ተውኔት፣ ደራሲ፣ የመጀመሪያዋ ሴት የፓርላማ ተመራጭ እና ዲፕሎማት- ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ
በሸዋ ክፍለ ሀገር በመናገሻ አውራጃ በአዲስ ዓለም ከተማ ጥር 6 ቀን 1908 ዓ.ም ተወለዱ። አባታቸው ታዋቂው ዲፕሎማት፣ የመጀመሪያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዘደንት፤ ጣሊያኖች ከኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ ደግሞ የምክር ቤቱ ፕሬዘደንት ፤በዳግማዊ ምኒልክ ሹመትም የመጀመሪያው የጎንደር ከተማ አስተዳዳሪ የነበሩት ከንቲባ ገብሩ ደስታ ሲሆኑ ታናሽ እህታቸው ደግሞ የውብዳር ገብሩ (እማሆይ ጽጌ ማርያም) ናቸው። ዕድሜያቸው ለትምህርት […]
Read More →በአዲስ አበባ የመሶብ ቅርፅ ያለው ባለ 70 ወለል ሕንፃ ሊገነባ ነው
እስከ ስድስት ዓመት ድረስ ይገነባል የተባለው ሕንፃ ባለቤት የባሕልና ቱሪዝም ሚንስቴር ሲሆን፣ የመሶብ ቅርጹ የተመረጠው የኢትዮጵያዊያንን የአብሮነት፣ የመሰባሰብ፣ የጋራ ደስታና ቃልኪዳን ምሳሌነትን ይወክላል በሚል ነው ተብሏል።ሚንስቴሩ የሚያሠራው ባለ 70 ወለል ሕንፃ 250 ሜትር ከፍታ እንደሚኖረው ተነግሯል። ይሕም በምሥራቅ አፍሪካ ረጅሙ ሕንፃ ሊያደርገው እንደሚችል ተገምቷል። ለግንባታውም ከ50 ሺሕ ካሬ ሜትር በላይ ቦታ ይፈለጋል የተባለ ሲሆን ሕንጻው […]
Read More →የማዕድንና ነዳጅ ሥራን የሚያግዙ ‹ድሮኖች› አገልግሎት ላይ ሊውሉ ነው
2019-01-03Author: አዲስ ማለዳ የማዕድንና ነዳጅ ሥራን የሚያግዙ ‹ድሮኖች› አገልግሎት ላይ ሊውሉ ነው የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር ለማዕድን አሰሳ እና በቅርቡ ለሚጀምረው የኢቲዮ-ጅቡቲ የተፈጥሮ ጋዝ ቱቦ ዝርጋታ ድሮን መጠቀም እንደሚጀምር አስታወቀ።ሚንስቴሩ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚታየው አስቸጋሪ መልክዓ ምድር የማዕድን አለኝታ ቦታዎችን ለመለየት ስላስቸገረኝ የድሮን ቴክኖሊጂን ልጠቀም ነው ብሏል።በቅርቡ ለሚጀምረው የተፈጥሮ ጋዝ ቱቦ ዝርጋታም ድሮኖችን ለመጠቀም ከኢኖቬሽን […]
Read More →ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አዲስ መተግበሪያን ይፋ አደረገ
አዲስ ማለዳhttp://WWW.MALEDATIMES.Com ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የኅብረተሰቡን ተደራሽነትን ለማስፋት አዲስ መተግበሪያን ዓርብ፣ ታኅሣሠ 19 ይፋ አደረገ።አዲሱ የመረጃ ቋትን የያዘው መተግበሪያ በሕግና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን ለማግኘት ጉልህ አስተዋፅኦ ያደርጋል የሚል ተስፋም ተጥሎበታል። መተግበሪያው ከ1934 እስከ 2010 ድረስ ያሉ ሕጎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንና የሰበር ውሳኔዎችን አካቶ የያዘ የመረጃ ቋት ነው ተብሏል። ይህ መተግበሪያ የበይነ መረብ አገልግሎት በማይገኝባቸው ቦታዎችም […]
Read More →የደህንነት ሃላፊ የነበረው አቶ ጌታቸው አሰፋ የእስር ማዘዣ ወጣበት ፍትህ ሚንስትር
የደህንነት ሃላፊ የነበረው አቶ ጌታቸው አሰፋ የእስር ማዘዛ ወጣበት ፍትህ ሚንስትር
Read More →“አቶ ጌታቸው አሰፋ በትግራይ ክልል እንደተሸሸጉ መንግስት መረጃው አለው” – ጠቅላይ አቃቢ ህግ
የትግራይ ክልል አስተዳደር፣ ከፌዴራሉ ሥልጣን በላይ ሆኗል ማለት ነው?! …. ኤልያስ ገብሩ!——- “አቶ ጌታቸው አሰፋ በትግራይ ክልል እንደተሸሸጉ መንግስት መረጃው አለው – ጠቅላይ አቃቢ ህግ #Ethiopia : የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ በትግራይ ክልል ተሸሽገው እንደሚገኙ መንግሥት መረጃ እንዳለው ነገር ግን እሳቸውን በሕግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል ሲባል ጥይት በመታኮስ የሌላ ሰው […]
Read More →በተለያየ የትምህርት ደረጃ ዶክትሬት ያገኙ ግለሰቦች ዶክተር ተብለው መጠራት የለባቸውም ተባለ፡፡
በተለያዩ የትምህርት ስልጠና እና ከፍተኛ ማእረግ ከሚሰጣቸው እርከኖች መካከል የዶክትሬት ትምህርት ላይ አተኩረው ላጠናቀቁ ማንኛውም የትምህርት አይነት እና ደረጃ ዶክተር ተብሎ መጠራት አግባብነት እንደሌለው ፣ እና ማእረጉ የትምህርት ደረጃ ማእረግ እና እርከን እንጂ ፣በህክምና ላይ ባደረገው ጥናታዊ ስራ ላይ የተሰማራ ሰው ብቻ ዶክተር ተብሎ ሲጠራ ፣ በሃገራችን ኢትዮጵያ ለክብር ዶክትሬት እና ለተለያዩ የትምህርት እርከኖች ላገኙት […]
Read More →በ100 ሽህ የአሜሪካን ዶላር ኤክስፖርት ያደረገው እና በአዳማ የተገነባው የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ተጠናቀቀ
በአዳማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የተገነባው አንቴክስ ጨርቃጨርክ ፋብሪካ መጠናቀቁን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አቶ ፍሹም አረጋ ጠቆሙ፡፡ እንደእርሳቸው አገላለሽ ከሆነ ፋብሪካው ወደ ውጭ ሃገር ኤክስፖርት የሚያደርጉ ምርቶችን የሚያመርት እና ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ልዩ ቴክኖሎጂ የተሞላበት ድርጅት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ በዚህ ድርጅት ውስጥ ከአንድ ሺህ አመስት መቶ በላይ የጉልበት ሰራተኞችን አሰማርቶ ለመቀጠር መሰጋጀቱን የጠቆሙ ሲሆን ፣ሰራተኞቹን በሶስት […]
Read More →በሜቴክ ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠሩ ባልና ሚስት ተከሰሱ
በሜቴክ ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠሩ ባልና ሚስት ተከሰሱ በጥቅም በመመሳጠር የመንግሥትን ሥራ በማያመች አኳኋን በመምራት በመንግሥትና በሕዝብ ጥቅም ላይ ጉዳት በማድረስ፣ በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) እና በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ኃላፊ ነበሩ የተባሉ ባልና ሚስት ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡ ክሱ የተመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች ከጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በተጠረጠሩበት ከባድ […]
Read More →
