ወርቅነህ ገበየሁ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን ህወሃት ወስኗል ክንፉ አሰፋ

ወርቅነህ ገበየሁ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን በህወሃት ተሹሟል። ይህ ከታማኝ ምንጭ የደረሰን መረጃ ነው። መረጃው እንደሚጠቁመው፤  እነ ዶ/ር ደብረጽዮን  ሹመቱን ያጸደቁለት፤ አቶ

Read more

እነ ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ ፣ ንግሥት ይርጋ ፣ ብ / ጄ ተፈራ ማሞ ፣ አቶ አሳምነው ጽጌ እና ከ101 በላይ እስረኞች እንደፈቱ ተወሰነ – 

56 የግንቦት7 እና 41 የኦነግ እስረኞች ከእነዚህም በተጨማሪ ውሳኔ አግኝተው በጎንደር እና በጭልጋ ማረሚያ ቤቶች የነበሩ 55 ፍርደኞች በይቅርታ ከእስር

Read more

የኢህአዴግ ውስጣዊ ቀውስ ተባብሷል- ስራ አስፈፃሚው አስቸኳይ ስብሰባ ይቀመጣል

ዋዜማ ራዲዮ-የበረታውን የፖለቲካ ቀውስ ተከትሎ ገዥው ግንባር በተለያዩ አቅጣጫዎች እየተውተረተረ ይገኛል። መሰረታዊ የፖለቲካ ማሻሻያ መደረግ አለበት የሚሉ ድምጾች በበረቱበት በአሁኑ

Read more

ኃይለማርያም ደሳለኝ ለምን ለቀቁ? ክንፉ አሰፋ

ኢ.ቢ.ሲ. በሰበር ያስተናግደውን የኃይለማርያም ደሳለኝ መግለጫ፤ ዞምቢዎቹ ተሯሩጠው ለማጽደቅ ግዜ አልወሰደባቸውም። እሳቸውም ልክ ስልጣን እንደነበረው ጠቅላይ ሚኒስቴር “ስልጣን አስረክቢያለሁ” ሲሉ

Read more

“ጃ ያስተሰርያል!” አራት አመታት ተከልክሎ በነበረ መድረክ? ክንፉ አስፋ

            ቴዲ ወደ ባህርዳር ሲያቀና “እንዘምራለን”  ማለቱን ያስተውሏል!።  የጉዞውን አላማ እንዲያ ሲል ነበር ረቂቅ በሆነ መንገድ የገልጸው።  በመዘመር እናበመዝፈን መሃል ያለውን ጥልቅ ልዩነት የማይረዳ ብቻ ነው ለሰሞኑ “አሲዮ ቤሌማ” እጅ የሚሰጠው።  ከኮንሰርቱ ጀርባ ያለው “የፍቅር ጉዞ” የሚለው መሪ ቃልውስጥም ከውቅያኖስ የጠለቀ መልዕክት አለ። ይህንን ቃል የተረዳ ብቻ ነው የተልእኮውን ስኬት ሊያበስር የሚችለው። ዝግጅቱ ኮንሰርት እንጂ ዳንኪራአይደለም። ሁለት ወይንም ሶስት ሰዓት ብቻ የፈጀ ኮንሰርት። ጥላቻ ሳይሆን ፍቅር የነገሰበት ኮንሰርት።  ትንሳዔን አብሳሪ ኮንሰርት። መዝሙር ውስጥ መልዕክት አለ። የሚያንጽ፣ የሚያነቃቃ መልዕክት። መላው በጠፋበት በዚህ ወቅት፤  ኢትዮጵያ የምትሻው የተስፋ ቃል ብቻ የሚደሰኩርላትን ሳይሆን ድልድይ የሚዘርጋላትን ሰው ነው።  ጥላቻነግሷል። በሃገራችን ስር ሰድዶ፤ ቤተ እምነትን ሳይቀር አምሶታል፤  ጥላቻ – ጥላቻን ይወልዳል እንጂ ችግርን አይፈታም።  እሱን ለማንገስ ላለፉት 27 ዓመታትብዙ ድንጋይ ተፈንቅሏል። አዎ ጥላቻ በሽታ መሆኑን አይተናል። ይህን ክፉ በሽታ ለማርከስ  የፍቅርን ዳገት መውጣት ግድ ይላል። ጉዞውን ቴዲ ጀመረው። ጥላቻን የሚያከስሙ ዜማዎቹን የሰሙ …  እነ ለማ መገርሳእነ … ዶክተር አብይ ተከተሉት።  ለማ መገርሳ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ማለቱ  የቴዲ “ሲንድረም” ስለመሆኑ የሚጠራጠር ይኖር ይሆን?             ጎበዝ፣  ዘመኑንም እንቃኘው እንጂ!   ሰው ለታቦት ንግስ ወጥቶ በዚያው የሚቀርበት ዘመን እኮ ነው ያለነው። ወገን የእሬቻን በዓል ለማክበር ሄዶእስከዘላለሙ የማይመለስበት ወቅት ላይ ነን።  ልቅሶና ሃዘንን ሰብሰብ ብሎ በጋራ የማይካፈሉባት ምድር፣  ምእመናን ለጸሎት ወጥተው የሚታፈኑበት ሃገር ላይእንደተቀመጥን ለአፍታም አንዘንጋው።  ኮንስርት ማድረግ  ብርቅ የሆነበት ሃገር። ዳር ድንበር እንዲያስከብር የተላከ ወታደር  መሃል  ከተማ ገብቶ የወገን ደምየሚያፈስስበት ምድር!  በዚህች ያልታደለች ሃገር፣ በዚህ አስከፊ ዘመን፣   “ጃ ያስተሰርያል”ን  አጥንት ይዘን ስንጓተት አጃኢብ አይሆንም?             ይህ እሰጥ እገባ  ልብ ላለው ሁሉ ቅንጦት ይሆናል።  ነገሩን በደንብ የተረዳው ወገን፣  ከ 50 ሺህ ሕዝብ  በላይ በታደመበት ዝግጅት ላይ  “ምንይፈጠር ይሆን?”  እያለ የልቡ ትርታ ከፍ እና ዝቅ ይል ይሆናል እንጂ፣  ቀሪ ሂሳብ አያወራርድም።  ጥሩ ዜና በሚናፈቅበት በዚህ ቀውጢ ሰዓት፣  ሰማይ ላይየወጣን የሕዝብ እምቅ ስሜት ተቆጣጥሮ በሰላም ማጠናቀቅ መቻል እጅግ የሚደነቅ ነገር  ነው። ስለዚህም ጉዳዩ የገባቸው ዝግጅቱ  “እንኳን በሰላም አለቀ!” ይላሉ።  ሻንጣ በጀርባ ሸክፎ ማራቶንን መሮጥ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ የሚያውቀው ሯጩ ብቻ ነው።            እርግጥ ነው ሕዝብ ፍላጎቱን ገልጿል። የሕዝብ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ማግኘት ነበረበት።  የሕዝቡ ጫና ቀላል አልነበረም።  ይህንን በተመለከተ ከቴዲአካባቢ የሚሰማው ነገር የህዝብ ስሜትን ያለመረዳት ጉዳይ አይደለም።   ስሜትን መረዳት እና ስሜትን መንዳት ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው።   26ኛውየአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ቴዎዶር ሩዝቬልት በአንድ ወቅት ሲናገሩ “በመሪዎች እና በአለቃ መካከል ያለውን ልዩነት ሰዎች ይጠይቃሉ።  መሪ ይመራል።አለቃ ደግሞ ይነዳል” ብለዋል።  መንዳት እጅግ ቀላል ነው። ውል ለማስያዝ መምራቱ ነው ከባድ።         አራት አመታት ሙሉ ተከልክሎ የነበረ መድረክ፣  በሰላም እንዳያልቅ፣   እንከን የሚያሸትቱ ተንኳሾች  አሰፍስፈው የሚጠብቁት ነገር ነበር። የጌታቸውማንጉዳይ ጣልቃ መግባት ነገሮችን አስቀድሞ የመረዳት፣ አርቆ የማሰብ እና የመብሰል ውጤት ነው።  በዚህ ፍቅር ጉዞ እቅድ ላይ  “ጃ ያስተሰርያል”አልነበረም።  ጉዞው ለመዝፈን ሳይሆን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው።  የሰላም እና የፍቅር መልዕክት።  በዚያ ውስጥ ሃዘን አለ። በዚያ ውስጥ ብሶት አለ። በዚያውስጥ ቁጭትም አለ።   በነገራችን ላይ በኮንሰርቱ ላይ ባለስልጣኖቹ በይገኙም ልጆቻቸው እና ሚስቶቻቸው በሙሉ ስቴዲየም ገብተው ከሕዝቡ ጋር ሲደሰቱነበር። ሕዝብ በአንዲት ቃል ብቻ ማነሳሳት እጅግ ቀላል ነው።  በረጅሙ የሚያይ ሳይሆን አጭሩን አላማ የመረጠ ይህንን ማድረግ ይቀልለዋል። ከዚህ ግፊትየሚገኘው ውጤት፣  ኪሳራ እንጂ ትርፉ ሚዛን ሊደፋ አይችልም።  ጥይቱንም፣ ቀለሃውንም የያዙ ሃይሎች ሰፍ ብለው ይህችን ወቅት እንደሚጠብቁአንዘንጋ።

Read more

ናይጄሪያዊው ሰባት ዓመት ፅኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ተወሰነበት

ሪፖርተር ፡ ታምሩ ጽጌ እንዳይመረትና እንዳይዘዋወር ክልከላ የተጣለበትን አደንዛዥ ዕፅ (ኮኬይን) ይዞ ለማለፍ ሲሞክር ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገ ፍተሻ

Read more

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar