ዶክተር አብይ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጡ
ለአራት ወራት በስልጣን ላይ በነበሩበት ሰአት ለጋዜጠኞች ያሉበትን የስልጣን ሂደት ላይ ምንም አይነት መግለጫ ያልሰጡት ጠቅላይ ምንስትር አብይ አህመድ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው እለት የሰጡ ሲሆን በተለያዩ ሃሳቦች ላይ መግለጫቸውን ሰጥተዋል፡፤ ሆኖም ግን በሃገሪቱ ውስጥ ያሉት ጋዜጠኞች በጥያቄ የጎለእተ እና መጠየቅ የሚገባቸውን ጥያቄዎች ከመጠየቅ ይልቅ የእራሳቸውን ህይወት ያማከለ እና ጊዜዊ ህይወታቸውን ያንጸባረቀ (የተንዛዛ ጥያቄዎች ሲጠይቁ የታየ […]
Read More →የሃገራችን የኢኮኖሚ ጉዞ እና የአሊባባ ከፍተኛ ፍላጎት
እርግጥ ነው በአሁኑ ሰዓት “አንዳች ነገር” ውስጥ ስላለን እንዲህ አይነት እውነት ለማስተዋልና ለመመርመር ዝግጁም ፈቃደኛም ላንሆን እንችል ይሆናል።ሆኖም ሌላ ጊዜ መለስ ብለን ልናስተውለው እንችላለንና ይህን መረጃ በወቅቱ መለጠፍን መርጫለሁ። “አሊባባ ግሩፕ” የዓለማችን ትልቁ የንግድ ተቁዋም ነው። ባለቤቱም ከዓለማችን ቢሊየነሮች ውስጥ አንዱ የሆነው ቻይናዊው ጃክ ማ ነው። የ Jack Ma ‘Alibaba group” የዓለማችን ግዙፉ የኢንተርኔት ገበያ […]
Read More →በዓለማችን ታሪክ ከፍተኛ የሆነው የገንዘብ በጀት ኢትዮጵያ ላይ ተመድቦዋል! ለምን ሚስጥሩን ዳንኤል ቶማስ እንዲህ አስናድቶታል።
አስተዋይ ኢትዮጵያውያን ሆይ!አስተውሉ! ኢትዮጵያ ብታድግና ብትሰለጥን የሚጠላ ዜጋ አይኖርም።ከዚህ አንጻር የዓለም መንግስታትና የዓለማችን ቢሊየነሮች ይህን ከፍተኛ ገንዘብ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚሰሩት ስራ በመመደባቸው ሊደሰት የሚችል ኢትዮጵያዊ በርካታ ሊሆን ቢችል አይገርምም!ሆኖም በዚህ የገንዘብ በጀት ከመደሰት ይልቅ መደንገጥ የሚቀድማቸው አስተዋይ ዜጎች ብዙም ባይሆኑ እንዳሉ አውቃለሁ።ምንም ይሁን፤ለምን?እንዴት?ብሎ መጠየቅን ማስቀደም ተገቢ ነው። ትናንት ይፋ ከሆነው ዜና ጀምሮ ከወራት በፊት ለጥናት […]
Read More →ለለማ ቡድን ትንሽ ማሳሰቢያ ብሥራት ደረሰ
ወዳጅ ሊሆን የማይችልን የለዬለት ጠላት በመለማመጥ ጊዜ ማባከን አያስፈልግም፡፡ ከንቱን ሰው ሲለማመጡት የፈሩት ይመስለዋል፡፡ ራሱን በጠባብ ዓለም ከርችሞ የሚኖር ሰው በውጭው የሚከናወነውን የመረዳት አእምሯዊ አቅምና ፍላጎትም የለውም፡፡ የዚህን ዓይነቱ ሰው ጋር ኅብረትና ሰላም እፈጥራለሁ ብሎ መታገል ኃይልንና ጊዜን በከንቱ ማጥፋት ነው፡፡ የነለማ ቡድን – የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጎራ – እየወደቀ እየተነሣ አሁን ላይ […]
Read More →ሀገራችን ከገባችበት አዘቅት እንድትወጣ ከሚያግዙ ነጥቦች ጥቂቶቹን እነሆ!
ምሕረት ዘገዬ (አዲስ አበባ) ከአሁኑ የሕወሓት/ኢሕአዴግ መንግሥት ጋር ሲወዳደሩ የደርግና የቀ.ኃ.ሥላሤ መንግሥታት በአጋጣሚ ካልሆነ እንዳሁኑ ዘመን በመርህ ደረጃ በጎሣና በነገድ የተዋቀሩ እንዳልነበሩ ብዙዎች ይመሰክራሉ፡፡ ስለዚህ ከነዚህ ያለፉ መንግሥታት በሕይወት ያሉ የልዩ ልዩ ሙያ ባለቤቶችን አሁን ከያሉበት ጋብዞ ለውጡን እንዲቀላቀሉና እንዲሣተፉ ቢደረግ ሀገር ትጠቀማለች፡፡ ሙያቸውንና ሀገር ወዳድነታቸውን እያጣሩ በአግባቡ ቢገለገሉበት ሀገራችን አንድ እርምጃ ወደፊት […]
Read More →ዓቃቤ ሕግ በቀድሞ የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተር ላይ ክስ መሥርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠው
Source The Ethiopian Reporter የቀድሞ የኢንሳ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ተወልደ ታምሩ ጽጌ ዓቃቤ ሕግ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ በሚገኙት የቀድሞ የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር ላይ፣ ክስ እንዲያቀርብና ውጤቱንም እንዲገልጽ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ትዕዛዙን የሰጠው፣ የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን በተጠርጣሪ አቶ […]
Read More →በግማሽ አቅሙ ሥራ የጀመረው የረጲ የደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ውዝግብ ፈጥሯል
#source reporter የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ሲመረቅ ከግራ ወደ ቀኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አዜብ አስናቀ (ኢንጂነር)፣ የውኃ ኤሌክትሪክና መስኖ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) እና ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ይታያሉ ዳዊት እንደሻው በ2.6 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባውና ማለቅ ከነበረበት በሁለት ዓመት ዘግይቶ ለአገልግሎት የበቃው የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ በግማሽ አቅሙ […]
Read More →አርቲስት አለምጸሐይ ወዳጆን ለመቀበል በአዲስ አበባ ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን አዘጋጅ ኮሚቴው አሳወቀ
አርቲስት አለምጸሐይ ወዳጆን ለመቀበል እየተሰራ ነው የአንጋፋዋ አርቲስት አለምጸሐይ ወዳጆን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ተከትሎ የተቋቋመው ኮሚቴ ዝግጅቱን አጠናክሮ እየሰራ ነው።ከ27 አመታት በኋላ ወደ አገሯ የምትመለሰው አለምጸሐይ ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ማለዳ 1፡00 ሰአት አዲስ አበባ ስትገባ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ቤተሰቦቿ፣የሙያ አጋሮቿ እና የመገናኛ ብዙሐን ባለሙያዎች በተገኙበት በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት […]
Read More →ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ በሀገር ቤት እና ከሀገር ውጪ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቼ፤ በመላው ዓለም በሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት በየዓመቱ በክብር ለሚነሳው እና ዘንድሮም ለ1439ኛ ዓመተ-ሂጅራ ለሚከበረው የኢድአል አድሃ አረፋ በአል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ- አደረሰን! ኢድ ሙባረክ !!! በፆም፣ በፀሎትና ክፉ ምግባርን በሚኮንን […]
Read More →በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተወሰደ እርምጃ እስካሁን 171 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።
በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተወሰደ እርምጃ እስካሁን 171 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ። source Siyum Teshome የኦህዴድ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንዳስታወቁት፥ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በተለያዩ ህግ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው ሲንቀሳቀሱ ነው። በዚህ መሰረትም ሱሉልታ ከተማ በቄሮ ስም በመንቀሳቀስ የግለሰብ ሰዎችን ቤት በማፍረስ የቤት ክዳን […]
Read More →
