በአዲስ አበባና በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የመንግስት ታጣቂዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ እየፈጸሙ ያሉትን ግድያ የአለም አቀፍ ሚዲያዎች በሰፊው እየዘገቡት ይገኛሉ። በአቤኔዘር አህመድ ከጀርመን
በአፍሪቃ መዲና በአዲስ አበባ የጎንደርንና የኦሮምያን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ በ30/11/2008 ዓም(06 Aug 2016) እና በ ቀን 1ነሃሴ 2008 ዓም (07Aug 2016) በተደረገው መንግስትን የመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በመንግስት ታጣቂዎች የንጹዋን ህይወት ማለፉንና በብዙ የሚቆጠሩ እንደታሰሩ የተለያዩ አለም አቀፍ የዜና አውታሮች ዘግበውታል። አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) መንግስትን ለመቋወም የወጡ ሰዎች ታሰሩ “Dozens arrested in Ethiopia anti-government protest” […]
Read More →በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በንጹሃን ሰልፈኞች ላይ መንግስት እየፈጸመውን የሚገኘውን ግፍ ለማውገዝ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በበርሊን ለማድረግ ወሰኑ።
ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኑረምበርግ በምትባል ከተማ ነሃሴ 1 2008 ዓም ባደረጉት ታላቅ ስብሰባ በመላው የኢትዮጵያ ክፍል እየተቀጣጠለ ባለው የሀዝብ ለአምባገነናዊ ስርአት አልገዛ ባይነት ምክንያት በመንግስት ታጣቂዎች እየተፈጸመ ያለውን ግድያ እስራት እንዲሁም ድብደባ አውግዘዋል። በተጨማሪም በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ ሁኔታ በንጹሃን ኦሮሞ እና አማራ ህዝብ የመንግስት ታጣቂዎች እየፈጸሙ ላሉት የነፍስ መገደል እና እስራት በመቃወም በጀርመን […]
Read More →ወያኔ በባሕርዳር፣ ጎጃም ዐማራ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ በቃን
በሙሉቀን ተስፋው የቆሰሉና የሞቱ ሰዎች ቁጥር አይታወቅም፤ ዓባይ ማዶ ኮበል በቃጠሎ ወድሟል • ከጎንደር የሚሔዱ ዐማሮች ዘንዘሊማ ላይ መታገዳቸው ለግጭቱ መንስኤ ሆኗል በጎጃም እምብርት ባሕር ዳር ዐማሮች በጠዋት ነበር ወደ ተጋድሎ ሰልፍ የወጡት፡፡ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ በዐማራ ወገኖቻቸው ላይ የሚደርሰውን በደል እና የጅምላ ግድያ በማውገዝ ወደ መስቀል አደባባይ ሕዝቡ በአንድነት ሔደ፡፡ በዚህ መካከል […]
Read More →ሰበር ዜና ወያኔ በግልጽ በዐማራው ላይ የጅምላ ግድያ አውጇል!
በወረታ ከተማ ከባድ ተኩስ ተከፍቷል ዛሬ ከሰአት በኋላ 7፡30 ላይ የጀመሩት የፎገራ ዐማሮች ከወያኔ ቅጥረኞች ጋር ከባድ ተጋድሎ እያደረጉ ነው፡፡ ከቦታው በስልክ ለማረጋገጥ እንደሞከርነው የወረታ ከተማ ሙሉ በሙሉ ቀውስ ውስጥ ገብታለች፡፡ ዐማሮች ላይ የጥይት ዶፍ እየወረደ ነው፡፡ እስካሁን አንድ ሰው ሲሞት ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ቆስለዋል፡፡ የፎገራ ዐማሮች የተሰዋውን ዐማራ አስከሬን ይዘው በመዞር ከቅጥረኛ ወታደሮች ጋር […]
Read More →በሃገሪቱ ላይ የተነሳው ቀውስ በጭቁኑ ህዝብ ብሶት የወለደው እንጂ ከሰሜን አሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያኖች አይደሉም ሲሉ ወያኔ ተቃዋሚዎች ናቸው ሲል አትቶአል
በአዲስ አበባ ናዝሬት ጎንደር እና ዝዋይ የተካሄደው አገር አቀፍ ተቃውሞ በየክልሎቹ መዛመቱ እንደማይቀር እና ጥሪው ከሰሜን አሜሪካ የሄደ ሳይሆን እዚያው ያለው መንግስት በፈጠረው አፈና እና የጭቁኑ ህዝብ ብሶት ነው ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ሲናገሩ ፣መንግስት በበኩሉ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ አሸባሪዎች ናቸው ይህንን ችግር የፈጠሩት ሆኑም ግን ችግሩን በቁጥጥጥር ስር አውለነዋል ሲል በመረጃ ማእከሉ ለመናገር ችሎአል። […]
Read More →በአዲስ አበባ ከተማ በጨለማ ተገንን በማድረግ ህዝቡን ለማፈስ መዘጋጀታቸው ተሰማ
በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት በተቀሰቀሰው ነውጥ ፣በመንግስት ታጣቂዎች ክፉኛ የሆነ ድብደባ በንጹሃን ዜጎች ላይ ተፈጽሞአል። በተለይም በብሄራዊ ቴአትር አካባቢ በአንድነት ወደየቤታቸው ሲጓዙ የነበሩ ጓደኛሞችን በመደብደብ እራሳቸውን እንዲስቱ አድርገዋቸዋል ። ቀሪዎቹም በከፍተኛ ጉዳት ወደ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን ፣ከማእከላዊ የመረጃ ማእከል ለወታደራዊ ሰራዊቱ የተላለፈው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ በአዲስ አበባ ከተማ በጊዜ የማይገቡትን ወጣቶችንም ሆነ በጋራ […]
Read More →በጎንደር እና አውዳይ የሞቱት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ፣ህዝቡም ለለውጥ ተዘጋጅተናል ብሏል።
በጎንደር ቆላድባ ሕዝብ ከሕወሃት ወታደሮች ጋር እየተዋደቀ እንደሚገኝ የሚደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል:: በአወዳይ የሕወሃት ሰራዊት በንጹሃን ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ባወረደው ጥይት 70 ሰዎችን ሲያቆስል 3 ሰዎች መገደሉ ተዘግቧል:: የጎንደር ቆላድባ ከተማ በአሁኑ ወቅት የጦር አውድማ ትመስላለች የሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ሕዝቡ ቁጣውን ለመግለጽ ፍርድ ቤት; የክልሉን የመንግስት መስሪያቤቶች እና ከ14 በላይ የመንግስት መኪኖችን በማቃጠል ተቃውሞውን ገልጿል:: በተለይም […]
Read More →ወያኔ ሆይ ልብ ግዛ! … ሕዝብም በእምቢተኝነቱ ይግፋበት! ያሬድ ኃይለማርያም
ከብራስልስ፣ ቤልጂየም ነሐሴ 06፣ 2016 እ.አ.አ ኢትዮጵያ ዛሬ መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች፡፡ የወያኔ ግትርነትና መረን የለቀቀ አንባገነናዊነት፣ በሥርዓቱ ተስፋ የቆረጠና የተበሳጨ ሰፊ ሕዝብ፣ ለ25 ዓመታት የተጎነጎነ የጎሣ ፖለቲካና ጥላቻ፣ መገለጫ የሌለው ድህነትና ችጋር አገሪቱን ሰንገው ይዘዋታል፡፡ በአገዛዝ ሥርዓቱ በኩል የሚታየው ሕዝብን የመናቅና ከሕግ በላይ የመሆን ዝንባሌ እየከፋ መምጣቱ በሥልጣን ላይ ያሉት ሰዎች አንድም ልባቸው […]
Read More →የጎንደር አማራ ሰላማዊ ሰልፍ፣ (አስተያየት) ከዶ/ር ከፍያለው አባተ
በቅርቡ የጎንደር አማራ ሕዝብ በጎንደር ከተማ ያካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ (በኔ እይታ) የአማራን ታላቅነት፣ የማያወላውል የኢትዮጵያዊነት ስሜት የሚያረጋግጥ እና በራሱ በአማራ ሕልውና ላይ የተነሳውን (የመኖርና ያለመኖር) ጥያቄ የመለሰ ይመስለኛል። የኢትዮጵያን መንግሥት በበላይነት የሚቆጣጠረው ታሕት፣ 1) ትግራይን ከኢትዮጵያ ገንጥሎ ራሱን የቻለ የትግራይ መንግሥት ለማቋቋም ሲታገል/ሲዋጋ የነበረ በመሆኑ፣ 2) ኤርትራን፣ ኦሮሚያንና ኦጋዴንን እንገነጥላለን ብለው ከተነሱ ገንጣይ […]
Read More →ጀግናው የጎንደር ህዝብ የወያኔን ባንዲራ አውርዶ የህዝብ ባንዲራን በአደባባይ ሰቀለ!! በአዘዞ ከፍተኛ ተኩስ መቀስቀሱም እየተሰማ ነው በጎንደርም ከተማዋን የከበቡት የመከላከያ ሰራዊቶች በህዝቡ ተከበዋል
በዛሬው እለለት በኮሎኔል ደመቀ ፍርድ ቤት አለመቅረብ ቁጣውን የገለጸው የጎንደር ህዝብ በአደባባይ ላይ የወያኔ ባንዲራ የሆነውን ባለ ኮከቡን (ኢሉምናቲ)የሰይጣን አምልኮ ምልክት እየተባለ የሚጠራውን እና በኢትዮጵያ ህዝብ እውቅና ሳይሰጠው ፣በትግራይ ተወላጆች ብቻ በጦር መሳሪያ ግፍት በህዝብ ዘንድ እንዲሰቀል የተደረገው ይሄው ባንዲራ በጎንደር ከተማ ወርዶ ትክክለኛውን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ሰንደቅ አላማ ለመስቀል ችለዋል። የጎንደር ህዝብ በመከላከያ ሰራዊት […]
Read More →
